ዳኘን ዳኘን አንድ ሕልም አሳየን
  በቦሎኮሮይ አዲሱ
 ‹‹ የተናቀ ቁላ ያስረግዛል›› ብዬ ልጀምር   በተናቀ. . . . ያረገዙ ገዢዎች ብዬ አንባቢ ነጠብጠቡ ላይ የመሰለዉን ቃል አስገብቶ እንዳይደነባበር ብጠቀመው ምን ገዶኝ ግልጸኝነት በመጥፋቱ አይደለም የተደነባበርነው ስለግልጸኝነት  ሳስብ ማን ትዝ ይለኛል ብትሉኝ  ኮ/ል መንግስቱ ኃይለ ማሪያም በቴለቪዢን መስኮት ቀርበው ‹‹ ለምሳ ሲያስቡን ቁርስ አደርግናቸው ! ››ብሎ ጥር 26 ቀን 1969 ዓ.ም እኔ ከመወለዴ ሶስት ዓመት ቀደም ብሎ የዲሞክራሲ ባህሪ የሆነው አንዱ የሆነው ግልጸንነት ምንየህል ጥግ እንደደረሰ ብቻዬን ግርም ይለኛል ግና ምን ያደርጋል ከገደለ አመታትን ያወጣ ተንኮለኞች ግን እርም እያበሉ ዲሞክራሲያዊ ነን የሚሉ ተንኮለኞች ግን እንደ አሜባ አስተኔ / የጣና አንቦጭ/ ተወከልቶች   ሰው በላ መንግስት ነው ይላሉ የጥይት አምስት ብር አስከፍሎ እርም የሚያስወጣ ክፉ ሊያስብል ይችል ይሆናል እን ጂ ተንኮለኛ አያስብልም  ቁላ የሚል ቃል  በዐረፍተ ነገር ያላጓደልኩትና የተጠቀምኩት አዉቄ ነው ፡፡ይህንን ዓይነት ቃላት መጠቀም ግልጽነትም ነው  በታላቁ መጽሐፍ ላይም ካህነ ደብተራ / እንደ አባ እስጢፋኖስ አባባል የኤልዛቤል ካህናት ማለት ነው/ ያደለው ነብዩ ሙሴ  ሳይቀየር  እንዳለ  ተጠቅመዉበታል ለፈረኦንነት የታጨው ሙሴ በነበረበት ዘመን የመጸሀፍ ቀበኛ ነበር እንደዛሬው ‹‹ እዉቀትን ጠልተሀልና እኔም ካህን እንዳትሆነኝ ጠላዉህ (ሆሴ 4/6)›› እንዳለው ይህንን ጥቁር መጸሀፍ ለማንበብ ይጋርደኛል እያሉ ግን ደግሞ ቀዳሽ ሊሆኑ የሚታትሩ ነብያት ነን ባዮች/ ካህነ ደብተራ / ያይደለዉ  ነብዩ ሙሴ  በእግዚአብሔር የነበረዉ ጦርነት  የተጻፈበትን መጸሀፍ (ዣንሹዋን ) እነኳን አንብቦታል ( ዘኁ ፡-21/19) ሙሴ ፣ ቁላው የተቀጠቀጠ ብልቱም የተቆረጠ  ( በዘዳ. 23/1 ) ሲል በግልጽ ጻፈ ከሱ ለጥቀው ራሳቸዉን ሳያመናፍሱ ብቅ ብቅ ብለው ይጽፉ የነበሩት እነ  እመቴ  ሜሪ አርምዴ ጋሼ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር ፣ ጻዉሎስ ኞኞ ፣ብርሀኑ ዘሪሁን ፣በኣሉ ግርማ ነጋሽ ገ/ማሪም፣ ከበደ ሚካኤል እና የመሳሰሉት የዚህ ግልጽ አፃፃፍ አባቶችና አያቶች ናቸው፡፡ይህ ሁሉ ለማቆያ/ከረሜላ/ ያል ነው እንጂ ዋናው ሀሳቤ አይደለም ከእኔ ጋር ስትዘልቁ  ላለማፋሸግ፡፡
  ቤተ-ክርስቲያን/እምነት/ እና  መንግስት ሰማንያቸዉን ሳይቀዱ በፊት በሁሉም ሀገሮች ማለት ባይቻልም ይበልጥ በኢትዮጲያና በአውሮፓ ማህበረሰብ የስልጣኔ ምንጭ እግዚአብሔር ነው የሚል እምነት ጎልቶ ይታይ ነበር ፡፡ የአውሮፓ ማህበረሰብ በእውቀት እያደገ ሲሔድ እግዚአብሔርን/ እምነትን/ የስልጣኔ ምንጭ ማድረጉን ተፋታና ሕዝብን የስልጣኔ ምንጭ እንዲሆን በትግልና በስምምነት ወሰነ አሰወሰነ ፤ስለዚህ ለስልጣናቸው ለዕልና ህዝብ እንጂ አጼዎቹ አይደሉም፡፡ በኢትዮጲያ ግን ከእምነት ጋር መፋታት የአገዛዛቸውን ህልዉና ፈተና ላይ ስለሚጥለው የጥንቱን እምነት ይዞ በመቀጠል እግዚአብሔር ከጉልበተኞች ጋር አንድ የሆነ ምስለኔያቸው እየመሰለ መጣ ሀገሪቱ የሀይማኖት ሀገር እንጂ የማኞች ሀገር ሳትሆን ከረመች፡፡ ይህ ሁኔታ ማለትም መንግስታትን በእግዚአብሔርን ሥም የስልጣናቸዉን ምንጭ በማመናፈስ ለብዙ መዕተ -ዓመታት ሲሰራበት የቆየ አሁንም ቢሆን አልጋ ቢለያዩም ሰማንያ ያልተቀደደ አሰራር ስለመኖሩ በነብይ ስም   ወይም  ምሎና ተገዝቶ መናገር አይጠበቅም  ፡፡
 ስልጣናቸዉን ያመናፈሱም ሆነ ያላመናፈሱ /ጎዳዎቹ/ ገዢዎች  የመጡበት መንገድ እጅግ የሚያሳዝን ደግሞም ጸሀይ የሞቀው ቢሆንም ለአገዛዛቸው ሲሉ ስላጣናቸዉን በእግዚያብሔር  ወይም በህዝብ  ስም    መለኮት አድርገው  ወደ መንበረ ጸባኦት ከወጡት ዉስጥ ተጠቃሾቹ የተሌለ ቢሆኑም ንጉሰ ነገስቱ ጥቁሩ ሰው ዳግማዊ ሚኒሊክ እዚህ ጋ ላንሳ እሳቸው በበዓለ ሲመታቸው የነበረው የመዋለው  ዜና ዘጋቢው አለቃ አጽሜ እንደ እሳት ላንቃ በሚጠብስ በዕሩ ሲዘግብ ቀልብን /ሩሁን/ የሚያስተው ትዕይንቱ አነሆ ‹‹ በ1871 ዓ.ም በዘመነ ሉቃስ በወረኃ ጥቅምት የሸዋ ሰው ካህናቱም ሁሉ በክተት ልቼ/ ፊቼ/ ከከተማው ተሰበሰበ በየመንደሩ ለሹል /ለጦር/ የደረሰ መንድ ልጅ እስከ ሽማግሌው እንድ አልቀረም ፡፡ሁሉም በክተት ተሰብስቦ በገባ ጊዜ ንጉስ ሚኒሊክ ከልቼ ተነስተው ደብረ ብርሃን ወርደው አደሩ ፡፡ ከዚያ ከሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን ከዐጼ ዮሀንስ የተቀበሉትን ዘውድ ሲጭኑ፤ ከሺ የሚበልጡ ቀሳዉስት በዙሪያቸው እጣን እያጠኑ፤ካህናቶችና ደብተሮች በፊታቸው እየረገጡ ፣ ወታደሩ እየጨፈረ የደጃች ጎበና ( የኦሮሞው ) ሠራዊት በፈረስ ጉግሳ እየተጫወተ፣በቀኝና በግራ ሆኖ እየጋለበ፣ሴቱ እልል እያለ፣ከደብረብርሀን ጀምሮ እስከ ልቼ፤እስከ ቦሎ ወርቄ እስከ ሳሪያ በሰራዊት ተመላ/ተመራ / ፡፡ሜዳው ሁሉ ጠቦ ነበር ፡፡ ንጉሱም ህዝቡም በደስታ በክብር ልቼ ገቡ ፡፡ ታላቅ በአል ተደረገ ፡፡ ታላቅ ምሳ ተሰናዳ ፡፡ ከምሳ በፊት ራስነት ለራስ ዳርጌና ለራስ ጎበና ተሠጠ፡፡››  የሚገርም ምስር ብላ የሚያሰኝ ዜና/የምስራች /   አማራነት ፣ ኦሮሞነት የሚባሉ ባህል ወለድ ስሞች ከኢትየጲያዊነት ጋር ያልተጣሉበት ይልቁንም በተዋህዶ የተሰለፉበት የለበጣ ሳይሆን የእዉነተኛ ፌዴራል አገር ስርዓት  የኅብረ ብሄራዊ ሀገረ ኢትዮጲያ መሰረት የጣለው  ዘመነ ሉቃስ እንደ አበው ከሆነም ዘመነ ላም / በረትን  ያስታወሱታል የሉቃስ ጸሐፊ  ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ወደመንበረ ፀባዖት የወጣዉን የሚኒልክን ስልጣን ያዳብርህ ብሎ በንጉስ ነገስትነት ያልተቀበለው የለም ሺ ካህናቱ ቀላድ ከመዉድ ጋር ተያይዞ እስከ ግባተ መሬቱ ድረስ ቅባ ቅዱስ እየረጩለት አመናፍሰዉታል ንግስናዉን  ፡፡ ቢሆንም የጥቁሩ ሰው ቁንጥጫ ከዘንባባ ዝንጣፊ ቀጥሎ እንጂ በመጀመሪያ አይደለም  በንጉሰ ነገስቱ በቁንጥጫ ለመመዝለግ  ምንአልባትም ለንጉሰ ነገስትነት መወዳደር መሻት እንጂ ለንጉሰነት ለመታጨት ቁኝጥጫ አሊያም ኩርኩም አያስበላም  ከ26 ዓመተ የጥቁሩ ሰው  ንግስና በኋላ በ1897 በመጀመሪያ በራስ ጎበና ፣ንጉስ ተክለ ሀይማኖት ተሰማና ዳምጠው  የሚኒሊክን የዘንባባ ዝንጣፊ  አልፈልግም ብሎ  በራስ ወ/ጊዮርጊስ የምትገለባበጥ ሰይፍ እንደ ተራ ገባር በመምሰል ሊያመልጥ ሲል  ታግዞ እርሶ የወንዶች ሁሉ ወንዶች ነዎትና  ስልጣን ያዳብር ብሎ እንደ አመሉ ካደረው ጋኪ ሼርቾ / ጭንቶ ጋሊቶ/ ሻዎ ቻራሻ/  የአያቴ ቦሎኮሮይ መገኛ ከፋ ከ/ሀገርን ላውጋችው አንዳንዶች እንደሚሉት አነዚህ አከባቢ የሚኒሊክ ዉልዶች ሆነው የኢትዮጲያዊነት ልደት ካከበሩ 110 ዓመት ገደማ አይደለም ፡፡ ብዕሬ ሌላ ቦታ ረግጦ እንዳይሸት ይህንን ነጥብ  በተገቢው ቦታ እመለስበታለው ፡፡ሚኒሊክ የማይበገሩትን ክልሎች ከሺ የሚበልጡ ቀሳዉስት እጣን እያጠኑ ካህናቶችና ደብተሮች በፊታቸው እየረገጡ/ ጠበል እየረጩ / ከአማራ ፣ በፈረስ ጉግሳ የታገዘ ነፍጥ አንጋች /አበጋዞች / ከኦሮሞ  ይዞ ደብረ ብርሀን አድሮ የተነሳው የእምዬ ሚኒሊክ ደንገጡሮች ስብጥር መንዝና አከባቢዋን ህዝብ እንዳይቀናቀኑትና ቅባ ቅዱስ እንዳይጋሩት ለእርሻና ለክህነት/ለለዋዊነት/ ገዳም ዉስጥ ትቶ ከቀዳማዊ ሚኒሊክ ጊዜ ጀምሮ ‹ኦቼ› ተብለው የሰራዊት ልምድ ካላቸው የሸዋ ህዝቦች ከሆኑት ብሔረ ኦሮሞና ብሔረ ጉራጌ ጎበና ዳጨ ፣ ኃብተጊርጊስ ዳንጋዴ ፣ባልቻ አባ ነፍሶን መሰለኔ አድርጓቸው ከበታቻቸው ብዛት ያላቸዉን የኦሮሞ እና የጉራጌ ተወላጆችን ነፍጥ አንጋች አድርጓቸዋል ፡፡እነዚህ ነፍጠኞች በወቅቱ የነበሩት የየአካባቢው አበጋዞችን የሚኒሊክን የዘንባባ ዝንጣፊ እያሳዩ ሆሳዕና ያለዉን እውቅና እየሰጡ በንጉስነታቸው ግዛታቸዉን እንዲስተዳድሩ ሲደረጉ የዘንባባ ዝንጣፊን ሳይቀበል ያናናቀና ያጣጣለ ከሆነ ደግሞ ነፍጠኞቹ እጃቸዉን ሰደው ንጉሶቹ የተጀቦኑበት ቡሉኮ ስር ዘልቀው የመቆንጠጥ ባለሙሉ ስልጣን/እንደራሴዎች / ነበሩ  ይህ ቁንጥጫ የቀመሰው የሀረሩ  አሚር አብዱላሂ ፣የአሩሲው ፣ የወላይታው ጦና ፣የከፋው ጋኪ ሼርቾ ብቻ አይደሉም ‹‹ ተተገባህ ተተገዛህ ሀገር አልነሳህም በኋላ ይጠቅምሀል›› ተብሎ የመዉጊያዉን ብረት ተቃዉመው የባሰባቸው የሰሜኖቹ እነ ራስ ዓሊ/ ሚካኤልም/ በንጉሱ ቁንጥጫ መዥለግ እየተደረጉ ነው የገቡት፡፡   አንቱ የተባሉ ደብተሮች  በተባ ብዕራቸው ያስታወሱን ሳልደግም ወደ ደቡብና ደቡብ ምዕራብ ከፋ  በኋላም እሰከ የኦሞ ወንዝን በማቋረጥ እስከ ስጢፋኒ /የሩዶለፍ/ ሀይቅ ድረስ ያሉ ትናንሽ ቁጥራቸው በዛ ያሉ ያሉ ህዝቦችን በራስ ወ/ጊዮርጊስ ( በኋላም የከፋ ሀገረ ገዢ ) ፊት አዉራሪነት   የሚኒሊክ መልዕክት የሆነው ‹‹ተተገባህ ተተገዛህ ሀገር አልነሳህም በኋላ ይጠቅምሀል›› የሚለዉን የዘንባባ ዝንጣፊና እምቢተኛነት ያስከተለዉን ቁንጥጫ በወፍ በረር ላስቃኛችው የመኤኒት ህዝብ ተወላጅ የሆነው ባላባቱ አያቴ ቦሎኮሮይ ኮያ ተተገባህ ተተገዛህ እንዳባትህ ታድራለህ መፎክር እና የአርንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ትውውቅ  በእነዚህ ዉስጥ የሚጠቀስ ነው የሱ የመኤኒትነት/ቲሻናነት/ና የኢትዮጲያዊነት ተዋህዶም አስቃኛችዋለው  ተከታተሉ ፡፡
 እምዬ ሚኒሊክ የትም ሲደርሱ ተበቃይ አልነበሩም ይቅር ባይ በተጨባጭ እውነታ ላይ የተመሰረተ አተያይ አላቸው ብል ያንስባታል እንጂ አይበዛበትም ኢትዮጲያዊነትን እያበራየው ስለሆነ አፌን የሚያስረኝን አልሻም አፌን ከምታስሩኝ ዘብጥያ ብታስሩኝ እመርጣለው ለዛ የሚሆነኝ የሻማ ብር ይዣለው ፡፡ዛሬ በሀገሪቱ ሕግ ብታሰርም ነገ ጉዳዩ በምርመራ ላይ እያለ በሀገሪቱ ህግ እፈታለው ምን ገዶኝ    እሩሩው ጥቁሩ ሰው  ደቡብ ላይ ንጉስ ጦናን ደም ማፍሰስን አስቀርተን ተተገባህ ተተገዛህ ሀገር አልነሳህም በኋላ ይጠቅምሀል ሲል ላቀረበለት የሠላም ጥሪ ጦና የጦርና የጦርን ወሬ ስለመረጠ  ግሳጼ ደርሶበት ዳግማዊ  ራስ ሚካኤል ጦና የደረበው ቡልኮ ስር ገብቶ እንደ ጉንዳን ነክሶ ስላልለቀቀው ጦና ሊነቅለው ሲል ጭንቅላቱ ዉስጡ ቀርቶ ቆስለውና አመርቅዞ መማረካቸዉን ከነ ተዋጊዎቻቸው አይቀጡ ቅጣት ከተቀጡ በኋላ መንግስቱን አሽቀንጥሮ ጥሎ ሥልጣኑን ለጦር አበጋዞች ሰጦ ከመሔድ  ይልቅ በታላቅነት ፍቅሩ እቅፍ ድግፍ አድርጎ እንደ አባቱ አድሮ እንዲገብርለት አድርጎ ጦር በሰበቀበት እጁ ላይ ብትረ ስልጣን አስጨብጠው ሥልጣኑን እንደ መለሱለት እንደ እምዬ ሚኒሊኒክ ያለ ከዚያ ወዲህ በእጥዮጲያ ከቶ አልተነሳም ሰው ሲፈለግ ባጀን እንጂ ! እዉነት እንዲነገር የእምነት የባህል ግዴታ ባለበት በዚያ ዘመን ስለወላይታው ነገር በኮንታ ወሬ ነጋሪ  ለከፋው ጋኪ ሼርቾ  ሹክ ሳይባል ቀርቷል አልልም ፡፡ግና ምን ያደርጋል የከፋዉ ንጉስ ህዝቡ ለእርሱና ለሀገሩ ያለዉን ታማኝነት ስለሚያውቅ ( የኋላ ኋላ የገዛ ወገናቸው በድለዉናል ጨቁነዉናል በማለት መክዳታቸዉን በምን አውቆ  ) የንጉስተ ነገስቱን እውቅና መሻትን ከቁብ ሳይቆጥረው የዋዉ ንጉስ  እንደ  እምነቱንህዝቡ ላይ ጥሎ በቦንጋ ገኖች ዉስጥ ለመመሽግ ቢልም ከማይመጥነው ንጉስ- ነገስት ጋር ለአንድ ዓመት ያህል ጊዜ ተፋለመ በመጨረሻም ሸንተረሩን በሚያውቁ ገባሮቹ ተጠቁሞ ተማረከ ፡፡ አንድ ሀኪም ነኝ ባይና የጦር አማካሪ የሚሆን  ከሩሲያ የቋጠረዉን ቆሎ እየቆረጠመ የጥበት ሀዋሪያ ለመሆን የመጣው ወዶ-ገብ በሚኒሊክ ፊሽካ ነፊነት ተፈጸመ የተባለው  የአሩሲው ጭፍጨፋ ወሬ ፍርፋሪም ከሻገተ ከአስር ዓመት በኋላ አሩሲ የገባው አሌክሳንደር ቡላቶቪች    ያልተቀበረ አስከሬን ላይ ቆሞ  እንደጻፈ ያህል  የብዕር ቀለም በደረቀበት ሀገር ብዕሩ አረፋ እስኪደፍቅ ድርስ የባጡን የቆጡን ያወረደበትና በአኬጦፌላዊ ምክሩን ሲያወረድ የሚኒሊክ ወታደር በአሩሲ ብቻ አምስት ሚሊየን/massacred half of the oromo population /5 million/ ጨፍጭፏል ብሎ አሉባልታ ጥሎ ስለሄደ የእኛው ስመ- ደብር (ድንቄም)   ይህንን አሉባልታ ከመሬት ላይ አንስተውት ከመሬት ይዞት የተነሳበትን ቆሻሻ እንኳን ሳይራግፍ እንዳለ በኢትዮጲያ ላይ ለመጫን ለየካቲት 12 ቀን 1929 .ም ለሞሶሎኒ እንኳን የማይሰራዉን አኖሌን ሐዉልት ካሰሩት ዉስጥ የሩሲያዊው ምንጭ እየቀዱ መራራ ፅዋ የሚያጠጡ የተሌሌ ናቸው ቀድሞዉንም በየመጻፎቻቸው መሀል ትንንሽ የአኖሌ ሐዉልት የገነቡ አሉ የአኖሌ ሐዉልት እንደ መራራ ጉዲና በህዝብ ጩኽት ሊፈታ ያችላል በየመጻፍት ገጽ የተወሸቁት ግን ማን ይፍቀዋል  ፡፡ አሩሲ ላይ 5 ሚሊየን ህዝብ አፈር ከድሜ ከበላ ከዚህ ወረድ ብለን ስናይ ደግሞ ሩሲያዊው ወዶ ገብ   በራስ /ጊዮርጊስ የተመራ ጦር ከፋንና ትናንሽ ቁጥራቸው በዛ  ያሉ ህዝቦችን በጦርና በእሳት  ያንበረከካቸው መሆኑን ሲደሰኩር  <<……እነዚህ ወታደራዊ ሀይሎች አገሪቱን በሙሉ አወደሙ፡፡ጫካ ዉስጥ ተደብቀው የነበሩ ሴቶችንና ህጻናትን በእሰረኝበት ወሰዱ፡፡ መቃጠል የሚገባዉን በሙሉ አቃጠሉ( Alexander Bulatovich. www.samizdat.com) ከከፋ ዋና ከተማ ከተቆለለው ሬሳ የሚመጣውን ሽታ መቋቋቀም አዳጋች ሆነ …ያልሰለጠኑ ህዝቦች / Savages/ በጥይት ከተመቱ በኋላ አንገታቸው በሰይፍ ይቀላል እያለ ሰለ  የከፋው ጭፍጨፋ ከወላይታው የበዛ ቁጥርም ሆነ እልቂት እንዳለው ሲወተዉት ደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ህዝቦች በብዙ የተለያና በአንድነት ችፍግ ብለው አንድነትን ፍቅርን በሚሰብኩ ደኖች ዉስጥ ሰለበቀሉና ስላደጉ በፊደል ብቻ ሳይሆን በተፈጥሮአቸው ጠባብ ስላይደሉ እንጂ የሰዉየው አሉባልታ ያራገበው አፍቅሮ ፈረንጅ የተጸናወተው ደቡብ ላይ የበቀለ ስመ -ደብር ልለው ስደፍር የነበረ ሰዉዬ በዚህን ግዜ ዉስጥ አንድ ሚሊየን አምስት መቶ ሺ የሆነው የከፋ ህዝብ ወደ ሁለት መቶ ሺ ህዝብ ዝቅ ብሏል ሲል በተልያዩ ምክንያች አንድ ሚሊየን ሶስት መቶ ሺ ህዝብ እንዳለቀ ጽፏል ወላይታ ላይ ተገደለ ሲል ካረዳው 118 987 / አንድ መቶ አስራ ስምንት ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሰባት/ ሟቾች አኳያ ሲታይ የከፋው ህዝብ  ‹‹ግዳይ ለፈለመ ዉሀ ለቀደመ ›› ያሰኝ ነበር፡፡ የአሩሲዉንና የከፋዉን እንደዚህ የወላይታውን በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ዕውቀት ባለው ህጻን ከደመርን  የሰሜንና ሌሎችም  የተፈጸሙ ጭፍጨፋ ሲደመሩ   አሁን እንኳ የኢትዮጲያ ህዝብ እንደዚ በጨመረበት ጊዜ የዚህ አከባቢ ህዝቦችን ዘኁልቅን ለመቁጠር  ማሀከላዊ መረጃ ክፍል ብሔድ  የቁጥር ልዩነት ነው የምናገኘው ያን ያህል ህዝብ ከየት መጦ ተጨፈጨፈ ማለቴ ዛሬም እንኳን የአንዳንዱ ህዝብ ያኔ የተባለዉን ያህል ዘኁልቅ የላቸዉም ማለቴ ነው ፡፡
 ያም ሆነ ይህ የካፋው ጦርነት የተጠናቀቀው ሀምሌ 14 ቀን 1897 ዓ.ም  ጋኪ ሼርቾ / ጭንቶ ጋሊቶ/ ሻዎ ቻራሻ/ ይባሉ የነበሩ ዶኖው / አንበሳው / በእጁ ያለዉን ሶስት የወርቅ አምባሮችን ራስ ወልደ ጊዮርጊስ እንዲቀበሉት ካደረገ በኋላ ሲሆን እንደ አጋግ ( 1ኛ ሳሙ 15 ያስታዉሰዋል)  ተግዞ የጨው ሀዉልት ለመሆን ወደ ኃላም ዞር ቢሉም እንደ ሎጥ ሚስት ወደ  ዙፋኑን ወደ ተቆናጠጠው አንድራቻ እንደ ዞሩ ሳይቀሩ ወደ አዲስ አበባ እጃቸው በሰንሰለት እንደታሰረ   አንድራቻ ላይ የሰሙት አንድ ጥይት ተተኩሶ፡፡ ቀጥሎ በአምስት ሺ ጠመንጃዎች ተኩስ ታጅቦ አርንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራው ተሰቀለ ፡፡ከበሮ ተጎሰመ፣ዕምቢልታና ዋሽንት ተነፋ፣ ቀጥሎም ወታደራዊ መዝሙር ተዘመረ ታሪክ በፈጸመው ኩነት ጭፍጨፋው ተጠናቆ ራስ ወልደ ጊዮርጊስ እትብታቸው የተቀበረበት አካባቢ ያህል ተሰምቷቸው የከፋና አከባቢው የሚገኙ ትናንሽ ቁጥራቸው በዛ  ያሉ ህዝቦች ሀገረ ገዢ ሆነው አርብቶ አደሩ ቦሎኮሮይ ገመናዉን ከሸፈነበት ዕራፊ ጨርቅ ዉጭ ያለው አካሉ  ከተነደፈ የወይፈን ትኩስ ደምና በወተት የደደረ   መላመላዉን/እራቁቱን/   ከከብቶቹ በረት ወጦ ከዚህ ቀደም በሰማይ ላይ ቀለሙን ያይ የነበረዉን ቀስተ ደመና ህዝቦች ላብ ደምና ነፍስ የከፈሉላት መሆኑን ከሀገረ ገዢው ራስ ወልደ ጊዮርጊስ በኩል ተረክቦ ኢትዮጲያን ሀይማኖቱ አድርጎት የክፉ ቀን ረሀብ ሲመጣ እምዬ ሚኒሊክ ከጎተራው እህል አውጥቶ በወተቱ   የሚምገዉን ምግብ ስላበላዉ ኢትዮጲያን ወዶት ጠላት ለአምስት አመት ማጂ ላይ ከትሞ ሲቆጣጠራት ከአርበኞች ጋር አብሮ ዛሬ ሰዎች በተገዛላቸው አውሮፕላኖች ተጓጉዘው ከጎረቤት ጠላት ጋር ሀገርን ለማጥፋት እንደሚማከሩት ሳይሆን ሀገርን ከሚታደጉቱ ወገን ጋር እስከ ደቡብ ሱዳን በማ ድረስ ከወር በላይ በእግሩ በመጓዝና እዛ ያለው የኢንግሊዝ መንግስት ያስታጠቀዉን መሳሪያ ይዞ በመምጣት ሞሶሎኒዎችን ቁም ስቅል በማሳጣት በኬኒያ በኩል እንዲወጡ ካደረጉት ዉሰጥ ተጠቃሹ በኋላ ቀኝአዝማች ቦሎኮሮይ ኮያ ነው የእኔ አያት ላብ ፣ደምና ህይወት የምትሻው ሀገርም ከፈለችው   እስከ 1966 ዓ.ም ድረስ በእምዬ ሚኒሊክ  ከረሳም በጃንሆይ   እንደ ማለ  በከርሞ ለጥቃቅን አጼዎች / አሜባ አስተኔዎች / አስረክቦ ሞተ መቼም መቼም ቴዎድሮስ ሀገርን አንድ ላድርግ ብለው ቢነሱ ካህናት ሳይቀሩ በመሰዋዕት ዉስጥ የእባብ ጭንቅላት አድርገው ሊገድሏቸው እንደሞከሩና በተለይም ለመንገስ ሲሉ የራሳቸው ሀገር ሰው የሆኑት አፄ ዮሀንስ የጠላት ጦር / እንጊሊዞች / መቅደላ ድረስ እየመሩ  አምጥተው ሊያስገድሏቸው ሲዘጋጁ በማወቃቸው ‹‹ ይህቺን የኢትዮጲያ ኩሩ ነፍስ የዉጭ ጠላት አይገድላትም ! ›› ብለው ራሳቸው ሽጉጣቸዉን ጠጥተው ሌሎች እንደሚሉት በጠላት ተገለው ሳይሆን ሊገደሉ ሲሉ ‹‹ ኢትዮጲያ ወንድ አይብቀልብሽ ›› ብለው ረግመዋት ሞተ፡፡ ይቀጥላል ..


Comments