እኔም የዚህ ትውልድ ልጅ በመሆኔ የአባቴን ገድል ልተርክላቸችላው ስዘጋጅ የደም ስሬ ቀጥ ብሎ ስራዉን እቁሞ ሳይሆን ከፍ ባለ ኩራት እና ደሜ እንደልብ እየተዘዋወረ በድሎት ነው ፡፡
የአባቴ “ኪስ” ማስታወሻ
ከጥንት እኛ
ኢትዮጲያን የማይፋቅ መርገምት አለብን ሲል እንድ ስመ ጥር ወዳጄ እርግማንን አጥንቶ በማዕረግ የተመረቀ ይመስል የወረደብንን መርገምት
ምንነት ከ19ኛው ምዕተ ዓመት መገባደጃ ምዕራፍ ዘመን ላይ ይጀምራል
፡፡ከነገስታቱ የእነ አፄ ቴዎድሮስን ፣ የአፄ ዮሐንስ ፣የአፄ ሚኒሊክ
፣ የአፄ ኃይለ ስላሴን ቆጥሮ ከጓዶች በሕይወት ያለውን መንጌንና የሞተውን መሌን ዘሎ ከሕዝባዊያን ዉሰጥ
አቡነ( አቡን) ጴጥሮስን ፣ በላይ ዘለቀ መንግስቱ ነዋይን
አንስቶ ጠቅሷቸው ያወረዱብንና ያለውን እርግማን መዘርዘር ጀመረ ፡፡
ቴድሮስ አገርን አንድ ላድርግ ባለው ላይ ብቻ
መለያትን የሚወድ ምኞትን ይከተላል ሲሉ የሚደሰኩሩ ካህናት ሳይቀር በህብስት ዉስጥ የእባብ ጭንቅላት አድርገው ሊገድሏቸው ሞክረዋል
፡፡ አፄ ዮሐንስንም የጠላት ጦር ( እንግሊዞች ) መቅደላ ድረስ ጮማና ጠጅ እያጠጡ ካስገሷቸው ቴድሮስ ሊያስገድሏቸው መትመማቸውን ቴድሮስ በማወቃቸው የተነሳ
“ ሀገሬ ኢትዮጲያ ወንድ አይብቀልብሽ
“ ብለው ረግመዋት ዛሬ ዛሬ አሟሟታቸውን በተመለከተ ጥርጥር ላይ የወደቀ ቢሆንም የመይሳው ካሳ (አባ ታጠቅን) ክንድ ገብርዬ እና ቀኝ እጁ ዓለሜም እንደሞተ
የመይሳው ባለቀጭን ጥለት ነጠላና ባለክፋይ ቀበቶ ያላላው የራሱ ወኔ መሆኑና ‹‹ ይህቺን ኢትዮጲያዊ ኩሩ ነፍስ የዉጭ ጠላት ኢትዮጲያ
አያደርጋትም ! ‘’ ብለው በወገባቸው ሀረር መሰዋዕት መሆናቸውን ግን ምንም መሔጃ ያላገኘውበት ሀቅ ነው ፡፡ ከእሳቸው የለጠቀው
አፄ የሐንስ የመጀመሪያው የትግሬ ንጉስ ሲሆን ከቴድሮስ በሸመተው የሕዝቡን እሳቤና ባህል በኢትዮጲያዊነት ዉስጥ ለማሰረግ ጥረት አድርገው ነበር ፡፡ኢትዮጲያ የብዙህነት ምድር መሆኗን በማሳየት
የሕዝቦቿን የቋንቋዋን ስብጥር እንዲታወቅ ጥረት አድርጎም ነበር ሆኖም ቄሶቹ ( ካህናቱ ) የሠለሞናዊ ስረወ መንግስትን ልዕልና ለመመለስና
ለአማሮቸ የበላይነት ለማሰያዝና የተጠናከረና አንዲት ሐይማኖት አንድ ብሔር የሆነ ኢትዮጲያን ለመመስረት ከመንግስት ዳቤ በልተው
ስለነበር አፄ ዮሐንስ ፖለቲካውን ለመዘወር የሚረዳው ቤተክርስቲያንን ከፖለቲካው ጋር ለማግባባት ስለዳዳው ፈተናው በዝቶበት ሲውተረተር
ኢትዮጲያን ከዉጭ ከመጣበት ወረሪ ኃይል ለማዳን ከደርቡሽ ጋር በተፋጠጡ ጊዜ የሸዋዉን አፄ ሚኒሊክንና የጎጃሙን ንጉስ ተክለሐይማኖትን
ለእናት ሀገር ጥሪ እርዳታ እንዲደርሱላቸው መልዕክት ሲልኩባቸው እነሱ ጥቁሩን ሰውዬ የዳዊት ኮኮብ ነው ብሎ በዳግማዊ ሚኒሊክነት ሊሾሙ በመመተር
ላይ በመሆናቸው አፄ ዮሐንስ ራሳቸው ብቻቸውን የጦርነት አውድ ገብተው
የጠላት ግዳይ ሳይጥሉ አንገታቸው ተቆርጦ ምርኮኛ ከመሆናቸው በፊት
“ ኢትዮጲያ ሆይ ዘር አይብቀልብሽ “ ብለው ረግመዋል ለዚህ ነው ሰው ስንፈልግ የባጀን ካለኝ በኋላ ፡፡ ደቡብ ኢትዮጲያ ድረስ
ዘልቆ የተሳካለት መካኑ ዳግማዊ ሚኒሊክም ከእቴጌ ጣይቱ ፍሬ ባያዩም እንደልጃቸው ያዩትንና የልጅ ልጃቸው የሆነው አቤቶ ኢያሱን
ለማንገስ በነበራቸው ጉጉት ጉልበታቸው ሲዝል “ ልጄን ተቃወሞ ለዙፋኔ
የማያበቃው ቢኖር ጥቁር ዉሻ ይውለድ “ ብለው በመርገማቸው ያው በእኛ ዘንድ ግልፅ እንደሆነው ተፈሪ መኮንን ኢያሱን ገድሎ ዙፋኑን
ቢወርሱም ያንን እንደ ዉሻ የሚናከስ እና ቢነኩ ምፅሐት ይሆናል የተባሉትን ለመጀመሪያ ጊዜ ካባ ዉስጥ ዘልቆ ንጉሱን ጭን የመዠለገ ደፋሩን ‹‹ደርግን›› እና ሌሎችንም እንደ ጥቁር ዉሻ የሚናከሱ ፓርቲዎች ከራሳቸው ከንጉሱ ማዕጸን ተፈለፈሉ፡፡
እሳቸውም ቢሆን ከነሽበታቸው በክብር ወደ መቃብር እንዳይወርዱ ጊዚያዊ ወታደራዊ
ደርግ መንግስት ከሞቀ ዙፋናቸው አውርደው 4ኛ ክፍለ ጦር አስረዋቸው ጣታቸውን በመያዝ ዳዴ ያስተማሯቸው ልጆቻቸው ይህንን በማድረጋቸው
አንጀታቸውን አላውሶት ምግብ ቀርቦላቸው ተመግበው ከጨረሱ በኋላ
ጣት ዉሀ ቀርቦላቸው ታጥበው ለጣት ማድረቂያ ፎጣ ሲሰጣቸው አሽከራቸውን
አይሆንም አይሆንም ብለው በመከላከል በዉሀ የተነከረውን ጣታቸውን ወደ ታች( ወደ መሬት) በማዘቅዘቅ የታጠቡበትን ዉሀ በማንጠባጠብ “ጣቱን ያዤ ወፌ ቆመች አልወደቀች እያስተማርኩት ያሳደኩት አስተምሬውና የከዳኝን ትውልድ
ደሙን እንደዚህ አንጠብጥብልኝና አጥንቴ ትውጋችው “ ጭምር የእርግማን ናዳ አውርደውብን ለሚዘክሩት ጊዮርጊስና ለቢሾፍቱው አሳጥተው
እንደሞቱ ነገረኝ ፡፡ እንዲሁም አባታችን አቡነ ጰጥሮስ “ለጠላት ጣሊያን የሚገዛ ዉግዝ ይሁን መሬቷም እሾህ አሜኬላ ታቅል” ብለው
ሊረሸኑ አቅራቢያ ተራግመዋል ፡፡በላይ ዘለቀም ቀራኒዮ እንደዋለ “ አንቺ አገር ወንድ አይብቀልብሽ “ ማለቱንና ጀኔራል መንግስቱ
ንዋይም “ አንቺ ሀገር አንቺ አገር እያለ የሀገርን ጆሮ በሚያዶናቅር ጩኽት በማማረር እያጉተመተመ ተራግሞ መሞቱን” ከአንድ ክፍለ ጊዜ በላይ አስረድቶኝ እኔም
ራሴ የተራገምኩት ካለ ሚስጢር ሳያወጣ ተው ተው ብዬ አሰቆምኩት ፡፡
ኢትዮጲያ ዉስጥ አንድ ጀግና ሲሞት ሌላው ሰው ለአስክሬኑ መቀበሪያ ሳይሆን
ኢትዮጲያ የምትቀበርበትን ጉድጓድ የሚምስ ይመስል እንደ በለዓም ሳይራገን የሞተ የሌለ መሆኑን በእኔና በወዳጄ ውይይት ተገንዝቢያለው
፡፡ የአዛውንቱ ጃንሆይ አፅማም ጣቶች ያንጠባጠቡት ወሀ ጠብታ ወደ
ደም እንዲቀየር ከራማቸው የተላመናቸው ይመስላል ፡፡ ክቡርነታቸውን ከአልጋቸው አውርዶ ወደ 4ኛ ክ/ጦር የሸኛቸው ጊዚያዊ ወታደራዊ
ደርግ አንደመንግስት ማስተዳደር ከጀመረበት የአብዮቱ አጥቢያ ጊዜ ጀምሮ እርስ በርስ እንደዉሻ እየተናከሱ ደም መፋሰስ የጀመረው
በዛው በ4ኛ ክፍለ ጦር ዉስጥ በተጠነሰሰው የለውጥ ሂደት ደርግን መስረተው የንጉሱ ሥርዓት እንዲፈርስ የግንባር ቀደምትነት ሚና
ከተጫወቱት መካከል የደርጉ ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት ኮሎኔል አጥናፉ አባተን ደም በመንጠባጠብ ነበር፡፡በሌላ መልኩ ደግሞ ከሁሉም አቅጠጫ ደም ለመፋሰስ ፍጥጫ የነበረበትና ከጎረቤት አገርም ሳይቀር
ጦርነት የተከፈተበት ጊዜ ነበር ፡፡ ከዉጭ ወራሪ ከከፈቱበት ጦርነቶች
ዉስጥ እንደ ምስራቁ የጦር ክፍል ግን ወደ ዉስጥ ዘልቆ የገባ የዉጭ ጦር ወራሪ ባይኖርም በምስራቁ የአገራችን ክፍል 700 ኪ/ሜትር ዘልቆ የገባው የተስፋፊው የዚያድባሬ ጦር ቀድሞዉኑም ጃንሆይ በዙፋናቸው በነበሩበት ጊዜም አጉል ድንፋታ
የነበረ ቢሆንም በደርጉ መባቻ ላይ ግን የባለከራማው ሰውዬ እርግማን
ታክሎበት ድንበራችን አዳማ ነው በማለት ዚያድባሬ አቅራርቷል ፡፡ጊዚያዊ ወታደራዊ ደርግ አስተዳደር የሱማሌን ተስፋፊ ጦር ከአገራችን
ድንበር ለማስወጣት፣ ጦርነቱን ለመከላከል ፣ አባቶች ያስከበሩትን ዳር ድንበር ለማስከበርና አንድ አጥቅ መሬት ላለመማቆረስ ባለው
እምነት መሰረት መፍትሔውን በድርድር ካልሆነም በጦርና ጋሻ ለአገር ልዕልና ለመቆም ባሳየው ቆራጥነት ‹‹ በጦርነቱ የሚያሸፍ የኢትዮጲያ
ሕዝብ እንጂ እኛ አይደለንም ›› ብለው በኩባው ፊደል ካስትሮ የተሞከረው የሰላም ወይይት ወደ ጦር መማዘዝ እንደሚያመራ የተረዳው ጊዚያዊው አስተዳደር ደርግ ለዚያድባሬ ጦር ምልሽ የሚሰጥ አብዮታዊ ሰራዊትን በአጭር ጊዜ አሰልጥኖ ለማብቃት ለመዲናችን
አዲስ አበባ ቅርብ የሆውን የሥጋ ሜዳ ተብሎ የሚታወቀውን ለተፈለገው ዓላማ ታጠቅ የጦር ሰፈር በማለት ለድንበር ተጋፊዎችን በንጉሱ
እርግማን መሰረት እርስ በርስ እንደ ዉሻ ለመነካከስና ደም ለመፋሰስ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ለሚንቀሳቀሱ ኤርትራን አስገንጣይ
ወንበዴዎች ጭምር በአጭር ጊዜ አገራዊ ሕልውና ላይ ለሚንቀሳቀሱ በሙሉ
መፍትሔ ለማሰጠት ለኢትዮጲያ ሕዝብ በሙሉ ከዳር አስከ ዳር ላሉ አዋጅ
አስነገሩ እንዲህም በማለት “ የኢትዮጲያ ሕዝብ ሆይ በአጣዳፊ ተንቀሳቅሰህ የአገርህን ከዉጭ ወራሪና ከገንጣይና አስገንጣይ ቡድን
ሕልውናህን ታደግ “ በማለት መያዚያ 4 ቀን 1969 /ም ለመላው
የኢትዮጲ ሕዝብ “ የእናት አገር ጥሪ አቀረቡ “ የ1953 አስከ 1970 ዓ/ም የነበረው ትውልድ የቄስ ትምህርት የቀመሰውም የአባቴ
ቢጤም ሆና አስኳላ ዘላቆ የቀለም ቀንድ የተንጠፈጠፈበት ጭምር ትልቁ
ግቡ ለውጥ ማምጣት ነው ፡፡ፍርሐቱም ድፍረቱም አኔ ለሀገሬ ምን ሰራውላት በሚለው ጥያቄ ላይ የተመሰረተ በመሆኑና ዕውቀቱም እውነቱም
የሚመነጨው ሌሎች አገራት የት ደረሱ በሚል ቁጭት በመሆኑ ለቀረበው የእናት አገር ጥሪ ያወላዳ አልነበረም ያወላዳ ሰው ካለም ኤርትራን
አስገንጣይ የወንበዴ ቡድንና የዚያድባሬ ቅጥረኛ የሆነ ኢትዮጲያዊ ሳይሆን ኢትዮጲያዊ የሚመስል ብቻ በመሆኑ መያዚያ 6 ቀን
1969 ዓ/ም በመላው ኢትዮጲያ ከአ/አደር እስከ የቀለም ቀንድ የተጠፈጠፈበት ድረስ ከከቤቱ ንቅል ብሎ በመውጣት በአገሪቱ ታሪክ
ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከየአቅራቢያው ባለው የገጠር መንደር ጀምሮ
አስከ ትልልቅ ከተሞች አደባባዮች እና ጎዳናዎች እየፎከሩ እያቅራሩ ለመተመም እኔን አሳልፉኝ በማለት ለተከበረው የእናት አገር ጥሪ
መልስ የሰጡ እልፍ እልፍ ሰዎች መንስሔው የወታደራዊ መንግስት አለንጋ ፍራቻና ደሀነት አዳልጧቸው የመንግስትን ረሽን ለመቀራመት ከጅለው አይደለም የተመሙት ይልቁኑም ከራስ በፊት ለአገር
ብለው ወሰነውበት ነው ፡፡ለዚህም ማሳያ በዚህ ክተት አዋጅ ከ14ቱ ክፍላተ ሀገራት ዉስጥ ታጠው የጦር ሰፈር ቀድመው ገብቶ አይደለም
የወያኔንና የዚያድባሬን ፈንጅ ቀርቶ የጦር ሰፈሩን ዙሪያ እሾህና አሜኬላ የለቃቀሙትና ከእነሱ ቀጥሎ ለከተሙት ከጎጃም ክ/ሀገር
ለመጡት ጓዶች የጠረጉት ከአርንጓዴው ፈርጥ ከሆነችው ከከፋ ክፍለ አገር ከተመሙ አምስት ሺ ወታደር የቀደመ ክ/አገር እንደሌለ የአባቴን
ማስታወሻ ሳጠና ታሪክ ያስታወሰኝነው ፡፡ለዚህ ለተቀደሰ ዓላማ ለሚከፈል መሰዋዕትነት ዉድ የሆነውን ሕይወቱን መሰዋዕት አድርጎ ለመክፈል
የጻፊው አባት ሚሊሻ ወታደር ደምሴ ቦሎኮሮይ ዝግጁነታቸውን ካሳዩት ውስጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው ፡፡ህዝቡ ምላሽ በመስጠት የፈጠረውን
ማዕበል ወታደራዊው መንግስት ባይሆን ኑሮ አደራጅቶ ለጦርነት ለማብቃት ፈተናው ቀላል አይሆንም ነበር ፡፡ ለአገራዊ ሕልውና መከበር
ላቡን ፣ ደሙን ፣ አጥንቱነና ዉድ ሕይወቱን ለመሰዋት የተመመው ሕዝባዊ
ሰራዊት በቁጥር 300,000 ( ሶስት መቶ ሺ ) የሚልቁ ሰራዊትን ለሶስት ወራት ብቻ ስለመሳሪያ አያይዝ ፣ የአካል
እንቅስቃሴ ብቃት አሰልጥኖ በሶ ያስጨበጠበት ጊዜ አጭር ስለነበር በድል የተወጣው ጊዚያዊው መንግስት ወታደራዊው መንግስት በመሆኑ
ብቻ እንጂ ሲቪል ቢሆን ያዳዳው ነበር ፡፡
ከአስራ አራቱም ክፍላተ ሀገራት ፣አውራጃዎችና
ወረዳ እንዲሁም ቀበሌዎች እኔን አሳልፉኝ እኔን አሳልፉኝ ብለው የተመሙት የሕዝባዊ ሰራዊቶች የሆኑት ሚሊሻ ወታደሮች በብዛት አርሶ
አደሮችና አርብቶ አደሮች ሲሆኑ የሱማሊያው ወረራ በመጧጧፉ አስከ ሰኔ ወር 1969 ዓ/ም አጋማሽ ድረስ ሰልጠናውን ፣ትምህርቱን
እንዲሁም አካላዊ እንቅስቃሴውን አጠናቀቁ ፡፡የዘማች ጦር ሰኔ 18 ቀን 1969 የተጠናቀቀ መሆኑን የሚበስር ዝግጅት ከጊዚያዊው
ደርግ ሊቀመንበር ጓድ መንግስቱ ኃይለማሪያም አንስቶ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣የጦር አዛዦች ፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች
አደባባዩ ድጋፍ ሊሰጡ በመጡት የሕብረተሰብ ክፍሎች ለጠጠር መጣያ የሚሆን ቦታ በሌለበት ሁኔታ ለአገር አሌንታ ሊሆን የተዘጋጀው
ሕዝባዊ ወታደር ( የሚሊሻዎች ) በምስርቁ አቅጣጫ በአስመራ መንገድ ( ኃይሌ ገብረስላሴ) ጎዳና ሰፍረው የደንብ ልብሳቸውን ለብሰው
ከነፍስ ወከፍ አስከ ከፍተኛ የጦር መሳሪያቸው አንግበው አርንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንዲራቸውን እያውለበለቡ “ ይህ ነው ምኞቴ እኔ
በሕይወቴ፣ ከራስ በፊት ለኢትዮጲያ እናቴ “ የሚለውን አገራዊ መዝሙር
ጮኽ ብለው እየዘመሩ በሶ እየረገጡ ወደ ሻለቃ መንግስቱ ኃይለማሪያም ሲቀርቡ ከሊቀመንበሩ ጀምሮ በበዓሉ ላይ የታደሙት በሙሉ ከመቀመጫቸው
ተነስተው የሚሊሻ ወታደሮቹ በጭብጨባ ሲቀብሏቸው ሚሊሻ ወታደሮቹም “ ማን ይፈራል ሞት ማን ይፈራል ፣ ለእናት አገር ሲባል “ ብለው እየዘመሩና እያጨበጨቡ በተራቸው ምላሽ ሲሰጡ በዕለቱ በዛው የሽኝት
ስነስርዓት ላይ የነበሩት በሙሉ ሸኚና ተሸኚ የሌለ ይመስል ሁሉም ለእናት ሀገሩ ሔዶ ለመሞት ተንቀልቅሎ ሁሉም በሞራሉ ተሸኚ ነበር
፡፡ይህ ዕለት የሰኔ ክረምት የነበረበት ወቅት በመሆኑ በዕለቱ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ የዘነበ ቢሆንም ሕይወታቸውን ለእናት አገራቸው ለይተው የሠጡት እነ ደምሴ
ቦሎኮሮይ ሶስት መቶ ሺ ሰዎች ራሳቸው በበረዶና በዉጭ የሚንቀጠቀጥ ማንነት ስላልነበራቸው የሚያሰሙት ሽለላ ፉከራና ቀረርቶ ጠላታቸውን
ለማጥቃት እንደ ግንድ አንሳው የባቹማ ጊዮርጊስ ለአገር እምነታቸው ለሰማዕትነት ያረጉ ነው የመሰላቸው ፡፡ሰውነታቸው አልታያቸውም
፡፡ከእናት አገር ጥሪ ምላሽ ከመስጠት ጀምሮ የአገር መደፈር እንደ እግር እሳት አንገብግቧቸው መተኪያ የሌለውን ሕይወት ለእናት
አገር ፍቅር ለማኖር በድምቀት ሲዘምሩ እውነትም ኢትዮጲያዬ የጀግኖች
መፍለቂያ አገር ስለመሆኗ ነቃሽ አያስፈልግም ፡፡እኔም የዚህ ትውልድ ልጅ በመሆኔ የአባቴን ገድል ልተርክላቸችላው ስዘጋጅ የደም
ስሬ ቀጥ ብሎ ስራዉን እቁሞ ሳይሆን ከፍ ባለ ኩራት እና ደሜ እንደልብ እየተዘዋወረ በድሎት ነው ፡፡
ሕዝባዊ ሰራዊት ( ሚሊሻ ሰራዊት ) የተዘጋጀላቸውን
ስልጠና እንዳጠናቀቁ ለአውደ ዉጊያ የተዘጋጁት 1ኛ. ለምስራቁ ግንባር ወጊያ 100,000 ( አንድ መቶ ሺ ) ተሰማራ 2ኛ . በመጀመሪያ
ዉጊያ በኤርትራ ዉጊያ ምዕራፍ በኤርትራ የሚታገለውን መደበኛ ሰራዊት አጠናክሮ ከኤርትራ
አስገንጣይ የወንበዴ ቡድን የመከላከል ዉጊያ ለሚያደረገው 20,000 ( ሀያ ሺ ) ወታደር 3ኛ .ከአዲስ አበባ በጅቡቲ መንገድ አስከ ደዋሌ ፣ ከአዲስ አበባ አስከ
አሰብ ወደብ ድረስ ፣ ከአዲስ አበባ አስከ አስመራ ያለውን ዋና ዋና መንገዶችን ጥበቃ የሚሰማራ 30,000( ሰላሳ ሺ) ወታደር
እንዲሁም ተጠባባቂ ወታደሮች በነፍስ ወከፍ ጠብመንጃ መሳሪያ ተሰጧቸው ነው የተሰማሩት ፡፡ ወደ ምስራቁ በዘመቱት ዘማቾች ደም ፈሶበት፣ አጥንት ተሰብሮና ነፍስ ተሰውቶ ዚያድባሬ ያሰበበት አዳማ ወይም ዝዋይ( ሽንብራ ኩሬ ) ሳይዘልቅ ካራማራ ላይ በአገሬ ጀግና የበላይነት ተጠናቀቀ ፡፡ ትውልዱ ከዘረኝነት ፅንውት አባዜ የነፃ መሆኑን ከአባቴ ኪስ ማስታወሻ ላይ አቶ አየነው
ደጉን ጠቅሶ በቀለ ጉርሜሳአልተወም ሾሉዋንና ሉቃስ ወቸኮሪ ጠቅሶ ደምሴ ቦሎኮሮይን ማስታወሺው ሲዘክር ዘማቾቹ ሐይማኖታቸው ኢትዮጲያ
የምትባል ፅንውት መሆኑን ብቻ ያስረዳል ፡፡ ለዚህ ድል መቀዳጀት ጉልህ የሆነ አስተዋፅኦ ካበረከቱ ሕዝባዊ ሰራዊት ( ሚሊሻ ሰራዊት ) ጀግኖች ዘመን አመጣሹ ዘረኝነት አደብዝዞ ከተረሱት ዉስጥ(አባቴ የተጋደለበት ርዕዮት
አንድና አንድ ብቻ ነው ‹ኢትዮጲያ› የሚባል ለዚህም ማሳያ ተከትቦ በቀረልኝ ማስታወሻ ላይ መስከረም 8 ጓድ አየነው ደጉ ፣መስከረም
20 ቀን ጓድ በቀለ ጉርሜሳ፣ መጋቢት 10 በቀን ጓድ ሾሉዋ፣የካቲት 8 ቀን ሉቃስ ወቸኮሪ ተሰዋ ሲል መስከረም 20 ቀን ደምሴ
ቦሎኮሮይ ተሰዋ ሲል ኢትዮጲያዊነት ርዕዮት በጓድነት እንጂ በነገድ የማያስተሳስር መሆኑን አስምሬበት ዛሬ ላይ ቢሆን ይህንን ማስታወሻ
የማላገኝ መሆኑን ስገምት የትግሬ ማህፀን ካፈራችው ጀግኖች የእማማ ኢትዮጲያ ቁርጥ ቀን ልጆች በቀድሞ አጠራር ትግራይ ክፍለ-አገር
አምባላጌ ወረዳ አደሽ ቀበሌ የተወለደው የጦር ሜዳ ጀግና ሜደይ ተሸላሚ ጀግናው ሚሊሻ ወታደር በላይ ሚሊዮን አምባዬን ብዕሬ ከረሳው
የአባቴ አጥንት በከንቱ የተከሰከሰ ያህል ይሰማኛል ፡፡ይህ ጀግና የካቲት 06 ቀን 1970 ዓ/ም አራቢ በተባለ ስፍራ ከወራሪው
የዚያድባሬ ተስፋፊ ጦር ጋር በተጧጧፈ ዉጊያ ላይ እያለ ጀግናው ሚሊሺያ ወታደሩ ለነፍሱ ሳይሰስት በስልት ከጠላት ጀርባ በመግባት
የጠላትን መትረየስ ተኳሽ በመግደል መትረየሱን በመረከብ በጠላት የጦር መሳሪያ 14 የጠላት ወታደሮችን ደምስሶ ብዙዎችን በማቁሰል
የቀሩትን የበታተናቸው ጀግናው ለወገን ጦር ሰራዊት የወኔ ስንቅ በመስጠት በምሰራቁ ክፍል ለተቃጣብን ወረራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቶ
በዚህም ተጋድሎው የህብረተሰባዊት ኢትዮጲያ የ2ኛ ደረጃ የጦር ሜዳሊያ ሽልማት በጓድ መንግስቱ ኃ/ማሪያም ከምስጋና ጋር የተበረከተለት
ከሰሜኑ ክፍል ተጠቃሽ ሲሆን ከምዕራቡ የአገሬ ክፍል ደግሞ የተሰጠውን ግዳጅ እንደ በላይ ሚሊዮን በድል አጠናቆ የኢትዮጲያ ጀግኖች
ማዳሊያ የተሸቆጠቆጠው የሚሊሻ ወታደር ከወለጋ ክፍለአገር ቤጊ አውራጃ ተወላጅ የሆነው መጋቢ ሃምሳ አለቃ በርኬ ቱቾን ባላነሳው በእጅ ያለን ወርቅ ዋጋ እንደመንፈግ ያስቆጥርብኛል
፡፡
አባቴ ሚሊሻ ወታደር ደምሴ ቦሎኮሮይ እንደጀግኖቹ
ሁሉ የተሰማራው በመጀመሪያ በኤርትራ ዉጊያ ምዕራፍ በኤርትራ የሚታገለውን መደበኛ ሰራዊት አጠናክሮ ከኤርትራ
አስገንጣይ የወንበዴ ቡድን የመከላከል ዉጊያ ለሚያደረገው ከተላኩት 20,000 ( ሀያ ሺ ) የሚሊሻ ወታደር ዉስጥ አንዱ ሆኖ ነው ፡፡
ሚሊሻ ወታደር አባቴ ደምሴ ቦሎኮሮይ ከመኤን
ነገድ የኮያ ጎሳ አባል ከሆነው ከአባቱ ቀኛዝማች አቶ ቦሎኮሮይ ኮያ እና ከአናቱ ከወ/ሮ ወ/ሮ አርጌሊ ዳማይ በቀድሞው ከፋ ክፍለ አገር ማጂ አውራጃ በጎልዲያ ወረዳ ቢያጌሌች ቄንሳ ( ጨበራ ) ቀበሌ ተወለደ ፡፡ አባቱ ቦሎኮሮይ የጠገበ አርብቶ
አደር በመሆኑ ባለበርካታ የከብቶች በረት ጌታ በመሆኑ በከብቶቸ ብዛት
ጥሎሽ እየጣለ በቁጥር 30 ሚሽቶች ( ሚስቶች ) አባወራ
በመሆኑ ሚስቶቹ ራሳቸው የሚኖሩበት ግቢ ከልጆቻቸውና ከልጅ ልጆቻቸው ጋር አንድ በረት በሚሞሉ ቤተሰቡም ይታወቃል ፡፡ ቦሎኮሮይ
ኮያ እሰከ ዕለተ ሞቱ ከ30 ሚስቶቹ ጭን ዉጭ ባለመግባትም ያታወቃል ፡፡ አፄ ዘድንግል የምድረ ባሪያ ሰው አናሪያ ይሁን ብሎ ባሪያ
ይሰኝ የነበረው የደቡብ ምዕራብ አከባቢ አፄ ሚኒሊክ በተደገጋሚ ባደረገው ቅኝነትና የአቅም ሙከራ ከአሕዛብነታቸው በቀር የከፋዎች
ሥርዓት የማረ መሆኑንና በዛን ሰሞን በሰሜን ለተከሰተው ርሐብ እህል ለመሸከፍ ለዘጠኝ ወር በአንድራቻ ላይ በነበረው መራራ ትግል
መያዚያ 14 ቀን 1987 ዓ/ም ከፋ የገባው የሚኒሊክ የጦር አዝማች
የሆነው ራስ (ደጃች) ወልደጊዮርጊስ የከፋውን ንጉስ ጨኒቶን ለጥ አሰኝቶ መሬት በመሳም እጅ እንዲነሱ ካደረጉ በኋላ የጨኒቶ እጅ የነበረውን
ሶስት የወርቅ አንባሮቸን ተቀብሎ በሰንሰለት አስሯቸው ወደ አንኮበር ሸኝቷቸው ቦንጋ ላይ ያለው ገበሬዎችን ካስገበሩ በኋላ ቀሪሁን
አገር ለማቅናት ጉዞዉን ወደ ፊት ያደረገው ወታደር በጫራጎባ( ጎባ
ጫራ) በኩል አሁንም በደጃች ወልደጊዮርጊስ ፊት አዋራሪነት የዘመተው ነፍጥ አንጋች ጨበራ(ቢያጌሌች) ከዛም ወደ ማጂ ነበር ጉዞ
ያደረገው ፡፡ ሰጥ ለጥ አስደርጎ ለማስገዛት ፡፡በመኤኒት ሰማይ ስር ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው ወታደር በደጃች ወልደጊዮርጊስ የተመራው
የሚኒሊክ ወታደር የሆኑኑ የአባ ጅፋር ልጆች የሆኑ ናቸው እነሱም ከፋ ላይ የሆነው ክፉ ነገርም ሆነ ጋሞዎቹ ደግሰው የሚኒሊክን
ጦር የተቀበሉበት ደግ ነገር እና በሚኒሊክም ፖሊሲ መሰረት ከነፍጥ ባሩድ ሽታ ይልቅ የዘንባባ ዝንጣፊ ስላሳዩ እና መሬታችውና የጎሳ
መሪነታቸው በእጃችው ይሆናል በዓመት አንዴ ብቻ በመካከለኛው ለሚኒሊክ ትገብራላችው ብሎ ከአሕዛብነትህ በቀር የጎሳ መሪነትህ ሸጋ
ነው ስላሉት አያቴ ቦሎኮሮይና ጎሳዎቹ በኩርማን እራፊ ጨርቅ አፍረተ ስጋቸውን ሳይሸፍኑ መላ መላቸውን ወገባቸው ላይ በቋጠሩት ቀጭን
የለፋ ቆዳ ነበር በደዳች ፊት የቀረቡትና ስብከቱን የሰሙት የጎሳ
መሪው እንዳባቱ እንዲያድርና ‹‹እኔ የእምዬ ሚኒሊክ ›› አሽከር እያለ እንዲምል አግባብተውት ከሱዳን ከሚመጣውን የእንግሊዝ ጦር
እና ከኡጋንዳ ከሚመጣው የፈረንሳይ ሰራዊት ቀድሞ አርጓዴ ቀይ ቢጫ
ባንዲ በሩዶልፍ አይቅም በታች ለመስቀል በችኮላ ከትርማና
ጥድ (ሱርማ) አሽቆልቁለው በትላቅ አለት ላይ በዚህነኛው ወገን ሚኒሊክ(ኢትዮጲያ) በዛኛው ደግሞ ኢንግሊዝ ( ሱዳን ) በማለት
ለኢትዮጲያ አንድነት ድንበር ለመከለልና ይሕቺን አገር ለማቅናት ሲጣደፉ ጨበራ( ቢያጌሌች) መኤን ነገድ ወገባቸው ላይ የቋጠሩት ቀጭን የቆዳ እራፊ ፈተው በምትኩ ሜትር ተኩል ሜትር ተኩል አብጆዲ ለወንዶች ሽርጥ “ ማርጫ ›› ለሴቶች ደግሞ
ለሚያሸርጡት ከፍየል ወይም ድኩላ ቆዳ የለፋ መታጠቂያ “ ታሹት ” ምትክ ሁለት ሜትር ተኩል ከወታደሩ እግር እግር ተከትሎ
የመጣው አማራ አብጆዲውን እየሰነዘረ ቆርጦ አልብሷቸው በጨበራ( ቀበሌ ) ላይ አርንጓዴ ቢጫ ቀይ ስንደቅ ዓላማ ሰቅሎ ሰንደቅ አላማውን
አነ ወ/ር አባ አጋ አባሙራ ፣ ማሞ ቀኔኔ ፣ ማሞ እጅጉ ፣ ገርባ ወልቀባ ፣ ወዘተ የተባሉ የአባጅፋር ልጆችና የራስ ወልደጊዮርጊስ
ወታደሮች በሆኑት እንዲጠብቁ እና ቦሎኮሮይ ደግሞ ሹመት፣ ሽልማት እንዲሁም ግዛቱን ተመርቆለት እንዳባቱ እንዲያደረ ተደረገ እምዬ
ሚኒሊክ እንደ አፄ ዮሐንስ ግራኝና አባ ጅፋር ህዝቤን
አሰልሞብኝ ነበርና ምንም ሐይማኖት የሌለውን ይህን አርብቶ አደር በግዳጅ ክርስትና ተነስተው የስጋ ቁልፈቱን በአዛውንትነታቸው ይቆለፉ
ብሎ የማስገድድ ሃሳብ ስለሌለው ባያስገድድም ደጃች ግን ከግዳዩ መሬት ላይ መታሰቢያ ይሆን
ዘንድ ቤተክርስቲያንን ማስተከል አንዱ ስእለት በመሆኑ በወቅቱ የመንግስት ሐይማት የሆነው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሆነው
የቅዱስ ሚካኤል ደብር በጨበራ (ቢጌሌች) ቀበሌ አስተክሎ ጨበራን
ወረዳ አሰኝቷል ፡፡ ቦሎኮሮይ እንደ ኃይማኖቱ ቢያድርም ልጆቹ ግን
በመጤው ኃይማኖት ተጠምቀው መጤው ሐይማኖት ከአባታቸው ስርዓት ጋር
ሳያጣላባቸው ሲኖሩ አያቴ ግን የጎሳ መሪነቱ የፖለቲካና የአስተዳደር ሥልጣኑ ኋላ ኋካ እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም የባላባትነት ጥቅሙና
ክብሩ ግን እስከ ዕለተ እልፈቱ ድረስ አጣጥሞ ከነክብሩም አሸልቧል ፡፡የደምሴ ታላላቆች የአባቴ አምላክ የማይሉትን የኦርቶዶክ ቤተክርስቲያን
አማኖች ሆነው አስከ ዛሬም ድረስ ዘልቀው ልጆቻቸውና ልጅ ልጆቻቸው በሚኒሊክ ጊዜ የገባው የጨበራ የቅዱስ ሚካኤል ታቦት የአባታቸው
አምላክ ወደ መሰኘት ደርሷል ፡፡ደምሴም በ40 ቀኑ የክርስትና ባይነሳም በአንዱ ጥር 11 በጅምላ የጥምቀት ስርዓት ተቀላልሎ የተጠመቀ
ሲሆን የክርስትና አባቱም ነፍሰ ሔር የጎጃሙ መምህር ተክሌ ልጅ ሽፈራው
የተሰኘው ሲሆን አባቴ ከአያቴ ቢላዋ ለይቶ ቅዱስ ቁርባን እየቀመሰ
አደገ ፡፡ በትንሽነቱ እህቱን ወ/ሮ ኮያ ካንጋጂን ለልጁ አቶ ወርቄ ዘውዴ የዳረለትና መሸሻ የሚሆን ልጅ ወልዶ በ69 ዓ/ም በነበረው
የደርግ ተቃውሞ ጦርነት የቦሎኮሮይ ቤተሰብ የሸሸጓቸው የዘውዴ ግዛው ልጆች ጋር ቤተክርስቲያ አቅራቢ የተመላለሰ በመሆኑ ቄስ ትምህትና
የካህን ኩርኩም ቀምሶ ነው ያደገው፡፡ ዕድሜው ለአቅመ መጠን ሲደርስ ለትዳር አጋሩ በመጀመሪያ በመኤን አርብቶ አደር ማህበረሰብ
ባህል መሰረት ሥሟ ወ/ሮ ዛኩ ወልደማሪያም የተባለች አባቷ ፀበል
የቀመሰ ራሷም ዮርዳኖስ የዋለች ኮረዳ በባህል ጥሎሽ ተዳረችለት፡፡ቀጥሎም
ከአባቱ ሀብት ላይ የድርሻውን ለትዳር ጥሎሽ ወጪ መቀራመትና የአባቱን ጎሳ የማበርከት ፅንውት አባቷ
ከከፋ ነገድ የሆነ ወ/ሮ ቦኒ ( አልማዝ ) በየነ ጋዎን 2ኛ ሚስቱ አድርጎ አገባ በቢያጌሌች ቀበሌ ጎጆ ቀልሶ ከመጀመሪያ ሚስቱ ገዛኽኝ ደምሴና ጋባጌ ደምሴ የሚባሉ ሁለት ልጆችን
ወለደ ከ2ኛ ሚስቱ ደግሞ እቴነሽ ደምሴ እና ማሚ ደምሴን ወልዶ በዛች የሳር ኪዳን ጎጆ ቤት ሆና ዙሪያዋን በከብቶች በረት በታጠረች
ጊቢ ዉስጥ አሪያም ጥግ ድረስ የሚሰማ ሳቅና ከእንጨት በተሰራ ገበታ መሶብ ዉስጥ የምትወጣ ምግብ በፍቅር ተቆርሳ ለሰባት ሰው ሆድ የሚበቃ የአንድ ባል
ሁለት ሚስቶች ሆነው አንቺ ቅደሚ አንቺ ቅደሚ የሚል መከባበር ባለበት የፍቅር ጎጆ ዉስጥ እያለ መያዚያ 6 ቀን 1969 ዓ/ም በመላው
ኢትዮጲያ ሕዝብ የቀረበው የእናት አገር ጥሪ ጆሮ ሰጠ ስለ ሰሜኑ የሰሜኑን ኤርትራ አስገንጣይ ወንበዴ ቡድን የተነገረው ነገር ባኖርም
ቅሉ ግን ተስፋፊው የዚያድ ባሬ እብሪት ዳር ድንበራችንን አልፎ ሰባት መቶ ኪ/ሜ አልፎ ድንበሬ አዳማ ነው ብሎ በእብሪት መወጠሩን
ከቄስ አሰከ ደቂቅ ድረስ የሚያወራው በመሆኑና የራዲዮም ሆነ የወታደሮች
ሽለላና ቀረርቶ በሚገባ የሰማ በመሆኑ ይህ ተስፋፊ ካልተገታ እሰከ ጨበራ (ቢያጌሌች) መድረሱ እንደማይቀር ሲያጤነው ተሸንፎ ከመገዛት
የዉጭ ወራሪን ለማራቅ በሚደረግ ትግል ዉስጥ የራሱን አስተዋፅኦ ለማበርከት ቆርጦ ተነሳ ፡፡ ደምሴ ከዉሳኔው እንዲቋረጥ ከሁለቱ
ሚስቶቹ ያላሰለሰ ምክር እንደተለገሰው እናቴ ከአንቀልባዬ ላይ ጀምሮ ስለምትወደው አባቴ ነግራኛለች ሆኖም ግን “አባትህ ለሀገሩ
እልከኛ ነበር ”ትለኛለች ፡፡ስለሆነም ወደ ጦር ግንባር ለመዝመት ቆርጦ ስለተነሳ በጨበራና በባቹማ ከተማ ጀምሮ ወታደራዊ ስልጠና
እየተለማመደ “እንሞታለን ለአገራችን አናስነካም ድንበራችንን” እያለ እየዘመረ አስከ መያዚያ 15 ቀን 1969 ዓ/ም ባቹማ ከተማ
ላይ ስልጠና ላይ ቆየ ፡፡መያዚያ 15 ቀን 1969 ዓ/ም ቤተሰብ
ተሰናብተው ወደ አዲስ አበባ ታጠቅ የጦር ሰፈር እንዲሔዱ ለመጨረሻ እራት ወደ ቤተሰብ ቢያጌሌች የደረሰው ቀኑ ሲያጋድል ነበር ፡፡ደምሴ የተወለደበትንና
ያደገበትን ሰፈር ላይ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ጎን አማትሮ አስከ ጥጋቱ ወረወራቸው በመኤን ሰማይ ሰር ሁሉም ነገር የተዘረጋ ዉብ ተፈጥሮ
ድግልናዉን ያላስገሰሰ የሕይወት ዑደት አለ ፡፡ የተፈጥሮ ሥርዓት አንዱ በአንዱ ላይ ሳይደራረብ አንዱ የአንዱን ሕልውና ሳይፈታተነው
በሰው ልጅ የግል ፍላጎትና ሩጫ ዑደቱ ውስብ ስብ ግዴታ ዉስጥ ሳይገባ ሁሉም በተፈጥሯዊ ቅድስናና ምንኩስና ካለበት ሕይውት በራሱ
ዉሳኔ ድንግልናው ለተሟጠጠ ገለሞታ አፈር መሆኑን ለሰማ ምድር (ዳር
ድንበር ) ለማስለቀቅ ለመሄድ መከጀሉ መንፈሱን ቀስፎ ሲያዘው ወደየበረታቸው እምቧ እምቧ እያሉ የልጆቻቸው ድምፅ እየሠሙ በሚገቡት ከብቶች
ሁኔታ ተገርሞ ጥጃ እንኳን የእናቷን ድምፅ ከሰማች ብሎ ክፉ ያሳሰበውን ጋኔን በስማም ፣በስማም ብሎ አማትቦ እንደምን ከረማችው
ብሎ ለስንብ መምጣቱን ሰምተው አንዷ ጎመን እየቀቀለች ሌላኛዋ የገንፎ ዱቄት እያመሰች አራቱ ልጆች የጉልቻዉን ጥግ ጥግ ይዘው በተቀመጡበት
ጎጆ ቤት ዉስጥ ገባ ፡፡የሚታመሰው የገንፎ ዱቄት እያወደው ቁጭ ባለበት ማራኪውን የዱቄቱን ሽታ አንዴ ማግ ማግ ካደረገው በኋላ
ከገዛኽኝ ጋር ስለ ነበረው ወታደራዊው ስልጠና ጥቂት ካወራ በኋላ ሰው ዘንድ በብድር ስለሰጣቸው ከብቶች ፍንጭ ሰጦት ከተመለሰ አሰየው
ካልተመለሰ ደግሞ ዕድሜው ሲደርስ ጥሎሽ ከፍሎ ሚስት እንዲያገባበት
ስሙን እንዲያስጠራ ለአንድ ብቸኛው ወንድ ልጁ ገዛኽኝ ምክር ሲሰጠው በተንተባተበ አንደበት አንዳንድ ጥያቄዎችን እየጠየቀው
እሱም ለልጅ በሚመጥን መልኩ እየመለሰ እራት ደርሶ ስለነበር ለቀረበው የመሰናበቻ እራት ሁሉም ተሰብስበው በሉ ፡፡ ከእራቱ በኋላ
ክፉንና ደጉን የማይሉት ልጆች አባታቸው የመጣላቸው እንጂ የማይለያቸው መሆኑን ሳያስቡት “ጪሊሊ “ የተባለውን የሕፃናት ጫዋታ ጥቂት
አንደተጫወቱ በተዘጋጀላቸው መደብ ላይ ፍንግል ፍንግል ብለው ተኙ
ደምሴ በተቀመጡበት መሐል ጭል ጭል ሲል የነበረው የእሳት ብርሀን
ሁለቱንም ሚስቶቹን ጎን ለጎን አስቀምጦ በስስትና መለያየትን አምርሮ በሚጠላ እይታ እየተመለከታቸው ሳለ የመጀመሪያዋ እና አመሉን
የማታጣዋ ዛኩ ስለተረዳች ከመኝታው በዳር በኩል የለሊት ልብስ በሆነው ፎጣ ተጠቅልላ ተንሰቅስቃ ማልቀስ መያያዟን ደምሴ ያላወቀው
2ኛ ሚስቱ አልማዝን (የእኔ እናትን) እንደጅል በፍቅር እንስፍስፍ አይኑን አይኗ ላይ በስስት እያንከራተተ ፈዝዞ
ሲያያት ቦግ እልም እያለ ልዩ ዉበት ሲያጎናጽፍ የነበረው የጎጆ ቤቷ የእሳት ላንቃ በሒደት እያጠረ እያጠረ ወደ ፍምነት ሲቀየር አልማዝም አይኗን እያስለመለመች በእሳት
ፍሙ ጭልጭልታው ብረሃን ከንፈሩን እየፈለገች ስትጠጋው የእሳቱ ተዳፍኖ የፍቅር ዛራቸው ፍሞ እቶን ሊመሰል ነፍስም አላቀረለት ሲል
ደምሴ በአንዳች የፍቅር መትሐት ታግዞ ከንፈሩን ከከንፈሮቿ ላይ ሊዶላቸው ያሞጠሞጠው ከንፈር እያቀረበ ሲደርስ በመጀመሪያ አፍንጫዋ የቅቅል በቆሎ እሸት ዓይነት ጠረን ካወደ
በኋላ የደምሴን የፍቅር ሲቃ የሰማው የአልማዝ የምራቅ ዕጢዎች የቀረበ
ምግብ እንዳዬ ህፃን ወደ ዉስጥ የሚዋጥ ምራቅ እንዳመነጩ አንዳች
የጨበራ ማር ወለላ የመሰለ ፈሳሽ ፈልቆ ከከንፈሯ ዳር ዳር ሊንጠባጠብ ሲል አባቴ(ደምሴ) ተንሰፍስፎ በከንፈሩና በምላሱ ታግዞ በአየር
ላይ ቀልቦት ወደ ዉስጥ መጠጣቸው አሁንም ማመንጨቱን ያላቆመው ወለል
እንዳይባክን ከንፈሩን በከንፈሯ እንደጣደ ምላሱን ወደ ዉስጥ አስገብቶ
የእናቱን ጭልፋ እንደሚልስ ህጻን ጥርግረግ አድርጎ አፀዳው ፡፡ ነፍስ ያልቀረለት የአንገት በላይ የፍቅር ገበጣ ጫዋታ ስጋቸው ዉስጥ የተደበቀችውን ነፍስ ገለጧት ነፍሳቸውም
እግር ሳይሆን ክንፍ አውጥቶ ከነፉ ቦኒ ለደምሴ ሁለት ልጆችን የወለደችለት
አልመሰለችውም አባቴና እናቴ ካጋዙት የፍቅር ምርኮ ጀግንነት ይኼ አዲሱ ደምሴን ከአሪያም ለመረከብ አስከ ሰባተኛው ሳይሆን እስከ ሶስተኛው ፆባኦት ደርሰው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ይህንን ገድል የሚተርክ አዕምሮ ይህንን
ብዕር የሚይዝና የሚከትብ እጅ በመጨረሻዋ እራት በኋላ በተነሳ የፍቅር ፅዋ ወንድ ልጅ ከነቃጭል ድምፁ መጣ እርሱም ጦር ሜዳ እያለ
በሰማው ዜና ለሚወለደው አዲስ ልጅም ሰላምታዬን አቅርቡልኝ ሲል በፃፈው ደብዳቤ እንደተወለድኩኝ አባትየው አዲስ ያለው ልጅ እየተባልኩ
አዲሱ ደምሴ ተሰኘው ፡፡ እንኳንም ከጀግናው ደምሴ ተወለድኩኝ ፡፡የሆነ ጀግንነት ጀግንነት ይሸተኛል እንዲሁም ይታየኛል ፡፡ ለሊት መነሳትና ወታደራዊ ልምምድ በቀየው ማድረግ የለመደው አባቴ ሁለቱም
ሚሽቶቹን በመኝታቸው ላይ እንዳሉ መያዚያ 15
ቀን 1969 ዓ/ም ከለሊቱ 10 ሰዓት ተነስቶ ለወታደራዊው ቆጠራ የ2 ሰዓት ርቀት ወዳለው ወደ ባቹማ ከተማ ሄደ ዕለቱም ደግሞ ሚሊሻ ወታደሮቹ ከጎልዲያ ወረዳ ባቹማ ከተማ ተነስተው በተዘጋጀላቸው ትራንስርት ወደ አዲስ
አበባ የሚሔዱበት በመሆኑ ጨለማውን ዕትብቱ የተቀበለችበትን ቢያጌሌች ቀበሌ እያረቀ እየራቀ ተጓዘ ከቆጠራ በኋላ ቀጥታ ወደ አዲስ
ሰለዘመቱ ዛኩና ቦኒ ለሰነፍ ወንድ የሚዘጋጅ የአልጋ መውረጃ ቁርስ
አዘጋጅተው ባቹማ ሲደርሱ የሰሙት ጀግናው ወደ ጦር ግንባር ዘምቷል የሚለውን ሰው ብቻ ነው ፡፡ ዘማቹ አዲስ አበባ ስልጠናውን እንዳጠናቀቁ
የሰሜን
ኢትዮጲያ ተወላጅ የሆነውና በስነ-መለኮት የትምህርት ዘርፍ የዶክትሬት ድግሪ ምሩቅ የሆነው ዶክተር ተስፋዬ ደበሳይ ከአዲስ አበባ
ከተማ ተነስቶ በኤርትራ ክፍለአገር ሰሜናዊ ምስራቅ አከባቢ በሚገኘው የሳልህ በረሀ የጥፋት ተልዕኮ ከጎረቤቱ ፕሬዝዳንት ዚያድባሬ
በከፋ መልኩ ለማሳካት ሔዶ ከተገንጣይ ድርጅቶች ጉያ ስር ተሸሽጎ
ከሌሎች ጋር በመሆን እዛ ላለው መደበኛ ሰራዊት አበሳ ስለነበሩ ደምሴ የተመደበበበት 1ኛ ሚሊሺያ ክፍለ ጦር 71ኛው ብርጌድ
711ኛው ሻለቃ 4ኛ ሻምበል ሐምሌ 9 ቀን 1969 ዓ/ም ከታጠቅ የጦር ሰፈር ቀጥታ ወደ ኤርትራ ተጉዘው ከኤርትራ ደግሞ ሐምሌ
13 ቀን 1969 ዓ/ም ከቀኑ 9 ሰዓት ጉዞ ወደ አሰብ አድርገዋል ፡፡ሐምሌ 14 ቀን 1969 ዓ/ም ከአሰብ ወደ ምፅዋ የባህር
ወደብ ደርሰው አዛው እንዳሉ ሐምሌ 20 ቀን 1969 ዓ/ም ከምፅዋ ወደ ግንዳ ተዛወሩ ጊንዳ ላይ አስከ ሐምሌ 25 ቀን 1969
ዓ/ም የቆየው ደምሴ በዚሁ ዕለት ወደ አስመራ ተቀየረ አስመራ እያሉ በኤርትራ አስገንጣይ ቡድኖች በተፈጠረው የውንብድና ተግባር
መስከረም 16 ቀን 1970 ዓ/ም እነዚህ ወንበዴዎችን መፋለም ወደ ግዳጅ ተላከ ፡፡የተላከበት ግዳጅ በኤርትራ መንገድ ደቀ መሐሪ
ላይ ሲሆን መሰከረም 20 ቀን 1970 ዓ/ም ከጠዋቱ አንድ ሰዓት
አንስቶ አስከ ምሽቱ 12 ሰዓት በነበረው እልክ አስጨራሽ ዉጊያ ደምሴ ቦሎኮሮይ የወንበዴው አስገንጣይ ጦር የወገንን ጦር እዳያጠቃ
ሲፋለም ዉሎ በዕለቱ ከወገን ጦር ጋር ተመሳስሎ የተሰለፈው የወንበዴው
አስገንጣይ ቡድን አባል የነበረው በቅንነት አገርን ከጠላት ወረራ እና ከተገንጣይ አስገንጣይ የወንበዴ ቡድን ለመታደግና የወለዳቸው
ልጆች የሚያድጉበትን አገር ለማቅናት የሚያሳየውን ተጋድሎው ያላማረው
የሻዕቢያ(ወያኔ) በቅርበት
በተኮሰበት ጥይት ደምሴ በዚሁ ዕለት ‹‹ ዘራፍ ›› የሚል የጀግንነት ሽለላ ድምፅ ብቻ አሰምቶ ዉድ ሕይወቱን ለኢትዮጲያ አገሩ
አኑሮ ተሰውቶ እንደ አባቱ ቦሎኮሮይ በከብቶች ቆዳ ሳይሆን በአርንጓዴ
ቢጫና ቀይ ስንደቅዓላማ ተከፍኖ ታሪኩ እስከ ዛሬ ሲወሳ ይኖራል ፡፡ ይቀጥላል …
የአባቴ ኪስ ማስታወሻ ዉስጥ የተገኘ የልብ ዝማሬ
ለኢትዮጲያ
በመኽር ፣በፀደይ፣ በክረምት በበጋ ፣
በገፀ-ምድርሽ፣በቆላሽ በደጋ
ዉጋትሽን ልውጋ፣ውጋትሽን ልዋጋ
ስወጣና ስወርድ ስለፋ ስተጋ
ለዓመታት ኖሪያለው ከጠረፍ ከድንበርሽ፣
ዘላለም ላፀናሽ ዘላለም ላኖርሽ፡፡
ምጣተ-ጥፋትሽን ላጠፋ ፣ ልገራ
ስንክ-ሳር፣ሳንካሽን ላፀዳ፣ ላጠራ
ሕመምሽን ልታመም፣ስቃይሽን ልጋራ
ከጉዳትሽ ቦታ፣በሕመምሽ ስፍራ
ኖሬ ተገኝቼ ታምሜልሻለው
አፍላነት ዘኔን ገድየልሻለው ፡፡
አፍን ለሚቆልፍ -ለዉሀ ለጥማት
አንጀትለሚቋጥር-ለረሀብ ለርዛት
አካል ለሚነድፍ-ለተባዮቸ ዉጋት
እራሴን ፣መንፈሴን፣ሕይወቴን ሰጥቼ
አንቺው ታዢበት ዘንድ ላንቺው አስረክቤ
ለሳንካሽ ታጥሬ ለሳንካሽ ተሰጣሁ
ስንክሺን ላርመው ፣ለሳንካሽ ተዋጋሁ፡፡
የጨቅላነት ቤቴ ናፍቆት እየበላኝ
የአናቴ ፣ያባቴ ትዝታ እየጠራኝ
ጎንበስ ቢሊ ምንም.፣ቀና ቢሉ ሰማይ
በምድር-ብረሃሽ ምቾት ድሎት ሳላይ
ጥቃትሽን ላጠቃ ለዘመን ኖርኩልሽ
በሜዳ ፣ በገደል፣በዱር ከተምኩልሽ ፡፡
.
.
.


Comments
Post a Comment