ዓለም ከአፍሪካ መልካም ነገር ይወጣል ብሎ ተስፋ አይጥልበት ፡፡ አሁን
አሁንማ ስልጣን በአፍሪካ ሀብት የማጠራቀሚያ አቁፋዳ መሆኑን እንጂ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻያ ፖሊሲ የሚወጣበት የስልጣን ማማ
አለመሆኑን ዓለም በሚገባ አጢኖታል ከአፍሪካ በህጋዊ መንገድ ወደ
አዉሮፓና ወደ ምዕራቡ ሀገራት ያለ አንዳች ስደት በህጋዊ መንገድ የሚገባው የጉምቱ ባለስልጣናቱ ዘብጣ ዶላር እንጂ ዜጎቻቸዉማ ከሚኖሩበት
ሀገር ይልቅ በስደትም እንደ ለማዳ ያልሆነ እንሰሳ በርግጎ በሀገሩ ወጦ በስደት ለባህር ዓሳ ካላደረ የተወሰነዉን አካል ለደላሎች
አስቀርቶ ጎዶሎ አካል ሆኖ ወደ አዉሮፓም ሆነ ወደ ምዕራቡ ሀገራት
የሚገቡት ያ በስደት የገቡበት ሀገር እትብቱ ከተቀበረበት ሀገር የማይከፋው
በመሆኑ ነው ፡፡ስለሆነም የአፍሪካ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ሳይሆን በነፍጥ ወይም የህዝብን ድምጽ በመስረቅ የሚዙት ስልጣን ሀብት የማጠራቀሚያ አቁፋዳ የሚያረጉበትም ወደው አይደለም ፡፡ የሉዓላዊ ስልጣን
ባለቤት የሆነዉን ህዝብ ድምጽ የሰረቀ ብሩን መሰረቅ ካልሲ የመቀየር ያህል ይቀላቸዋል ፡፡ጎረቤቱን ገድሎ ስልጣን የያዘም ምን አልባት
በአንድ ታምር አቁፋዳዉን ቢጥል እትብቱ ሊያኖረው ስለማያስችለው መዝገቡን አዉሮፓና በምዕራቡ ሀገራት
ማከማቸቱ ለክፉ ቀን ስንቅ ይሆነኛል ብሎ ነው ፡፡ግን ዛሬ ዛሬ ከምዕራቡ ዓለም ብቻ አይደለም ለመሬት የከበደ ሀገር
መሪ የሆነው ትራንፕ የእነዚህን ቆሻሾች ተግባር አጢነው ገንዘባቸው ባንኮቻችንን አጨናንቀው ያለው ሳያበቃ ዜጎቻቸው ለምን ያጨናንቁናል
ቆሻሻ ብራቸዉን ወስደው ለዜጎቻቸው ችግር መፍቻ ያድርጉት ማለቱን ስሰማ አንተ ብፁህ ነህ አልኩት ብፁህስ ሰምቶ የሚጠብቅ ነው
(ሉቃ . 11፡28) የአፍሪካን መሪዎች ከዚህ አስነዋሪ የስድብ ዉርጂብኝ
እንዲያልጡ ፕሮጀክት በመንደፍ ለፕሮጀክቱ መሳካት መሳቢያ /Inecentive / ጭምር ረብጣ ዶላር ያዘጋጀው ሱዳናዊ ቱጃር/ ከበርቴ/
ሞ-ብራሂም የተባለው ነው ፡፡ ሞ-ብራሂም የአፍሪካ መሪዎች ሥልጣናቸውን በዲሞክራሲያዊ ምርጫ አሊያም በፍቃዳቸው ፓርቲያቸዉን ለቀው በሌላ ህዝብ በፈለገው ከተኩ የ5,000,000 /አምስት ሚሊዮን ዶላር / ቼክ ከአንጡራ ሀብታቸው እፈርምለታለው
በሚል ነበር ፡፡ ሆኖም ግን አንድም የአፍሪካ ገዢ የ5,000,000
/አምስት ሚሊዮን ዶላር / ከቱጃሩ ሞ-ብራሂም እጅ ቼክ አልተቀደደለትም ምክንያት አንድ ዙር የ5,000,000 /አምስት ሚሊዮን
ዶላር / ከሞ-ብራሂም እጅ ከመዉሰድ ይልቅ ከማይነጥፈው ህዝቡ በየቀኑ ምን በየቀኑ በየሰዓቱ 5,000,000 /አምስት ሚሊዮን
/ ዶላርን ወደ አቁፋዳቸው ማስገባት እየተቻለ ፡፡ ሆኖም ከሞ-ብራሂም እጅ ቼክ የማያስቆርጥ ቢሆንም አንዳንድ ፍንጮች አሁን አሁን
ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል እነሱም ህዝቡን ራቁት ያደረገ ፓርቲያቸዉን ሳይሆን የራሳቸዉን ስልጣን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቅ / ግን
ደግሞ ነው እንዳልል የታሪክ ሺሚያ እንዳይሆን ፈራው / እነዚህ ፍንጮች የህዝብን ድምፅ ከማክበር ጋር ተገምዶ ቢወጠሩ ለአፍቅሮተ
ንዋያቸው በአምስት ሚሊዮን ዶላር እና የህዝብ ፍቅርን ሸክፈው ወደ ቤታቸው ሄደው ቀሪ ዘመንን እትብት በተቀበረበት እናት ሀገር
ቤተክርስቲያን በመሳም ከረንቡላ በመጫወት ሲጋራ ሱቅ ገብቶ በመግዛት ጥላ ቤት ገብቶ ሳይሸማቀቁ በመጠጣት እና የዕድር ጸሀፊ አሊያም
ዳኛ በመሆን ቀሪ ህይወትን ማጣጣም ከፓርቲ ጋር አብሮ ከመሞት ይልቃል ፡፡ ቆርቤበታለው ማለት መጨርሻው ያለፍትሀት መቅርት ነው
፡፡ለምን ለፓርቲ ትቆርባላችው እናንተ አፍሪካዊያን ገዢዎች ፡፡

Comments
Post a Comment