በሰፍነግ የሞላ ሆምጣጤ መጎንጨት ዳገተኝ ፡፡


  
በሰፍነግ  የሞላ  ሆምጣጤ  መጎንጨት  ዳገተኝ   ፡፡
   የቀሬና ሰው ሆይ መስቀሉን  አግዘኝ  ሉቃስ 23፣26-27
                                                   ቦሎኮሮይ አዲሱ
 ሚስቴ  ከሰሜን ኢትዮጲያ ከተወለዱ  አቶ ታደሰ ታረቀኝ  የምትሆን ወ/ሮ እስራኤል ታደሰ ስትሆን እኔ ደግሞ ከደቡብ ኢትዮጲያ አርብቶ አደር የሚሆን የደምሴ ቦሎኮሮይ ልጅ ነኝ አያቴ ዘላን ነበር አባቴ ግን ለእናት ሀገሩ የሚዋደቅ ጀግና ወ/ር ነው ልጁ ደግሞ የህግ ባለሙያ ውዷ ሚስቴ የቤት እመቤት ነች ፡፡ ከሰሜን እና ከደቡብ ከሆኑት አባቶቻችን የተወለድነው ተያየን ተዋደድን ተጋባን ደቡብ ምዕራብ ቤ/ማጂ ላይ ከተመናል ከሁለታችንም አብራክ እንደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ አንድነትን የሚሰብኩ ዥንጉርጉር ዛፎች የመሰሉ አራት ህጻናትን  በእግዚአብሔር ምህረት አፍርተናል  ነብር ዥንጉርጉርነቱን ኢትዮጲያ መልኩን እንዲል ታላቁ  መፀሐፍ ቤታችን ዥንጉርጉር ነው፡፡ ቤተ -ኢትዮጵ ይሉሀል ይኼ ነው፡፡
 ግና ምን ያደርጋል  የቤተ -ኢትዮጵ አባወራው አያት አቶ ቦሎኮሮይ ኮያ / የነገደ መኤን አባት/ባላባት ፣ቀኝ-አዝማች /  የፋሺስት ጣሊያንን ወረራ ለመመከት አርበኞች በዱር በገደሉ ሲፋንኑ  እሱም  በረት ሙሉ ከብቶቹን ከበረት ትቶ ከጥቃት የሚከረፋ ነገር የለም ብሎ የፋሺስትን ጥቃት ለመመከት ከኢትዮጲያ አርበኞች ብጣሽ ማስታወሻ ሲደርሰው ከጎልዲያ ወረዳ / ማጂ አውራጃ ዉስጥ የሚገኝ / ተነስቶ እንደሱ ካሉት ሀገር ወዳድ አርበኞች ጋር ከወር ጊዜ በላይ የእግር ጉዞ ወደ ሱዳን /የአሁኑ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ የሆነችው ቦማ/ በመጓዝ እዛ ከሚገኝ የኢትዮጲያ ወዳድ ከነበረቸወና ኋላም ፋሺስት ከሆነችው የኢንግሊዝ መንግስት ከጃንሆይ ጋር ባለቸው ወዳጅነት የነፍስ ወከፍ ጦር መሳሪያ በመታጠቅና ተመልሶ በመምጣት ማጂ ላይ ከትሞ በሐይማኖትም በባህል ነዉር የሆዉን የግብረ ሰዶማዊነትን ወሮን ሲያካሔድ የነበረዉን ወራሪውንየ ጣሊያንን ሀይል ‹‹ ሞጢት ››፣‹‹ ኮቺት ››፣ ሌምጤክ››  እያለ እየወጋው  ቁም ስቅሉን እያሳዬ እንደ እነ አበበ አረጋይ /ራስ/ ቁም ስቅሉን ያሣዬ  ተጋድሎ እየፈጸመ ጠላትን ከሀገር አስመርሮ ካስወጡት  ኢትዮጲያዊያን ወዳድ አርበኞች ዉስጥ አንዱ መሆኑን ባይጻፍለትና ኢንግሊዝ ላይ ሎጅ ለሎጅ /ሪዞልት ለሪዞልት/ ይዝናኑ ከነበረው ጃንሆይ የራስነት ማዕረግ ባይሰጠዉም በራቡ ጊዜ ከጎተራው ሰፍሮ ላበላው እምዬ ሚሊኒክ / ኢትዮጲያ / ግን ፍጹም ባንዳ እንዳልነበረ  የአይን እማኞች ነግረዉኝ የሞቱ ወዳጆቹ / ኮዳ ያዦቹ / አመታት ገና እየወጣ ነው፡፡  አባቴ አቶ ደምሴ ቦሎኮሮይም እናቴ  አንቀልባ ላይ ሆኜ የሰማዉትና  ዛሬም የማነበው እዉነት በጅጅጋ በኩል የሱማሌ ተስፋፊ ጦር ኢትዮጲያን ሲወር ከኢትዮጲያና እትዮጲያዊነት ዉጭ ሌላ ዕርዮት እንዳለ እንኳን የማያውቀው ደምሴ ለሱማሌ ወራሪ ወደ ምዕራብ ኢትዮጲያ ዘምቶ የዉጭን ወራሪ ኃይል አፈር ከድሜ አስጊጦ በሚያውቀው የአርብቶ አደር ቀብር  ስነ-ስርዓት መሰረት ጠለቅ አድረጎ ቆፍሮ እንዳይነሱ የድንጋይ ማዐት ከምሮበት  ቀብሮት ከቀብር ተመልሶ  እህል ዉሀ ሊቀምስ ቁጭ ሲል  ወደ ሰሜኑ የኢትዮጲያ ክፍል የተሰማው የጦር ወሬ ቀብሩን ለማሰለስ እንኳን ፋታ ስለነሳው ወደ ሰሜን ዘምቶ ከባዕድ ክላሽኮፕ  የተወነጨፈችው ጥይት ያልደፈረችዉን  ገላውን በዉጭ ጠላቶቻችን ተቀባብሎ ለወገን የተሰጠች ጥይት ተወንጭፋ ተሰንጥራበት ችንካር በመሆን ለህልፈተ ዳርጋው በአባቱ መቃብር በከብቶች ቆዳ ተከፍኖ ከመሬት በታት 3 ሜትር ከመቀበር ይልቅ በአርንጓዴ ፣ቢጫ ና ቀይ ባንዲራ ተከፍኖ  በሰሜኑ ኢትዮጲያ በአስመራ ፣ሀድጓዳ ፣ደቀመር ልዩ ስሙ ሳላዶሮ ላይ ሐይማኖቱም፣ ርዕዮቱም ፣ ሀገሩም ፣ከብቱም/ሚስቱም/ ሁሉም ለሆነችው ኢትዮጲያ ልክ እንደ ነገደ ኤርትራዊያኑ / እንደነ ብላታ ገ/እግዚአብሔር ፣ብላታ ሀጎስ / ከአፈር በላይ ህይወቱን ለሀገሩ አኑሮላት ከዚህ ዓለም የኩሩ ኢትዮጲያዊ ጀግና ሞት ሞተ ለሀገራ ዋለ ፡፡ አትዮጲያን ላለ የሚጨክን አንጀት የለም እንኳን ያኔ ዛሬም ቢሆን በሜድትራኒያንና በቀይ ባህር የሁለቱ ሀገር ነገዶች አብረው ተቃቅፈው እንዲወድቁ ያደረጋቸው የደምሴና የብላታ ሀጎስ ለኢትዮጲያ ሀገር መዋላቸው ነው ፡፡ኢትዮጲያ ሰላሟ ፣አንድነቷ ፣ኃይማኖቷና ህልውናዋ እንደ  ሀውልቱ  ሆና ይቆም ዘንድ አባቴ ሞተ ሞትማ አይቀርም ሰው ጠላ ቤት ሔዶም ይሞት የለ ለሀገር  ብሎ መሞት የጅግና ሞት ነው፡፡
የደምሴ ልጅ አዲሱ አባቱ ህይወቱን ባኖረላት ሀገር ወፌ ቆመች አልወደቀች  እየተባለ  በደርግ በዘማች ቤተ- ሰብ አስተዳደግ ዘይቤ አድጎ ለአካለ መጠን ደረሰ ትምህርቱን እሰከ ኮሌጅ በጥሶ የህግ አዋቂ ሆነ ግን ወፈ - ህጉን አላስፈጽምም ወይም አልተረጉምም ጫኝ አውራጅነት ነው ባይሆን ባይሆን  በጥብቅና ሙያ ለመሰማራት አሰብኩ  ይሻላል በማለት ግና ምን ያደርጋል ጃንሆይ ባቋቋሙት የጥብቅናም ሙያ ቁመናው ለጥብቅናም አይበቃም ተባልኩ  ቁመና ማለት   ጥበትን/ዘረኝነትን/ና ተንኮልን ሲያምጡ  ማሪያም ! ማሪያም ! ማለት  ነው    ኢትዮጲያ ! ኢትዮጲያ ! ያለማ ዕድል ፈንታው ጋግራን ደሴት ዉስጥ መጣል ነው እኔ ደግሞ በአርብቶ አደር ቤት ተወልጄ የወይፈን ደም ተነድፎ ከወይፈኑ እናት በታለበ ወተት ተቀላቅሎ ጠጥቼ ያደኩኝ በዘማች ቤተ-ብነት ኢትዮጲያ ያሳደገችኝ ቁመናዬ በእርግጥም ምቹ አይደለም   ስለዚህ  ያለ በደሌ በሰፍነግ የሞላ ሆምጣጤ በጋግራን ደሴት ዉስጥ  እየተጎነጨው እገኛለው  ምክያይቱን በማላውቅ የፖለቲካ መስቀል ስቸነከር በኢትዮጲያ ዉስጥ ዛሬ ዛሬ በህግ አምላክ የሚባልበት ሰባዊ ተቋም እንደሌለ እያወኩኝ  ለምንአልባት ያገር ያለህን ጩኽት ሳሰማ ፈረንጆቹ CONSTRUCTIVE DISMISSAL እንደሚሉት በዚህ ቀመር የሙያ ላይሰንሱን /የጥብቅና ፈቃድ/ ከወሰድኩኝ በወራት ዉስጥ የ 99 000/ ዘጠና ዘጠኝ ሺ /ብር ግምት ቢሮዬ በባለጊዜዎቹ ቱባ ባለስልጣናት ወደመብኝ ተሸሮ ወደ ቅርጫት የተጣለዉን ህግ ከቅርጫት ዉስጥ አውጥተው ትቢያዉን እንኳን ሳያራግፉት በሰበብ አስባቡ የሚደርስብኝን በደል እንጃ  ቤቴ ይቁጠረው ፡፡
  አዲሱ ደምሴ ቦሎኮሮይ አባቶቹ ላብ ፣ደምና ሕይወት ለግሰውላት የማሷት ቀደም ብለው አለቆች የቆፈሯት ነብያትም ( የክርስቲያን ፣ሙስሊም እንዲሁም ሀገር በቀል ) ትንቢት የተናገሩላት  ኢትዮጲያ ላይ  ዛሬ እንኳን ሰላሳ ካሬ ሜትር አግኝቶ ሊኖርባት፣ ሶስት ክንድ መሬት አግኝቶ ሊቀበርባት ቀርቶ ሶስት ስንዝር መሬት ላይ ቆሞ እንዳይሄድባት  ኢትዮጲያ ዉስጥ ባለ ገዢ/ ወያኔ መራሹ/ ፖለቲካ መስቀል እየተቸነከርኩኝ  ቁም ስቅሌን  እያየው  መሆኑን በሀገር ዉስጥና ዉጭ ሀገር ላላቸው ኢትዮጲያዊያን በሙሉ ላስታውቃችው እወዳለው ፡፡ ይህንን በኢትዮጲያ ዉስጥ ሆኔ ሳሳውቃችው  የሻማ ብር በእጄ ይዤ ነው የሻማ ብር ብቻም አይደለም የነፍስ/ንሰሀ/ አባትን ጎብኝቼ በንሰሀ ታድሼና የዕድር ዉዝፍ ከፍዬ ጨርሼ ነው ፡፡ይህንን የምለው መታሰር ወይም መሰወር  ዕጣዬ በመሆኑ ነው ጎረቤት ሀገር ኤርትራና ሱማሊያ ብሰደድ እናት ሀገሬ ሆና ዕትብቴ የተቀበረባት ሀገር ከምታደርስብኝ ግፍና በደል የከፋ ስለማይሆን የምጠብቀው ቢደርስብኝም የኢትዮጲያ ህዝቦቼ ለቀሪዎቹ ልጆቼ ከእግዚአብሔር ጋር እድትደርሱላቸው ነው፡፡
ጉዳዩ ወዲህ ነው  ጎምቱ ባለጊዜዎቹ / ባላባት ገዢነት ደረጃ ላይ ደርሰዋል/  የግል ቤት ደረጃዉን በጠበቀ ሁናቴ ሰርተዋል ግን ለማከራየት ሲሉ አይኖሩበትም ለጥሩ ተከራይ ወይም ለዉጭ NGO በጥሩ ዋጋ  አከራይተዋል ፣የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ለእነሱ ብቻ በሁለት በሁለት ዕጥፍ ስላደገላቸው ከሚከፈላቸው ሌላው ዜጋ በዕቁብ መልክ ከሚያገኘው ጋር ተመጣጣኝ  ከሆነው ዳጎስ ካለ ደመወዝ ላይ አርባ በስልሳ የሚሆን ኮንደሚንየም ቤት እንዲከራዩበት የቤት ክራይ አበል አላቸው ዕድገቱ የፈጠረው የኑሮ ዉድነት ስላለባቸው የኪራይ ብር ለጤፍ መግዢያ እንዲያደርጉት በሌላ በኩል የመንግስት የኪራይ ቤቶች / የቀበሌ ቤት / በቅናሽ ኪራይ ተመቻችቶላቸዋል ፣ በመንግስት መኪና ከሰላቸዉን ሚስቶቻቸዉን ልጆቻቸዉን ያምነሸንሻሉ እንደዚህ እነሱ በንዋይ  ቁንጣን እየተንቆራጠጡ  የእኔን አንደዬዋን ኖሬበት ሰርቼበት ቤተሰቤን የማስተዳድርበት የኦርዮ ሚስት ቤርሳቤዬን አይነት ቤት  እንደ የሺ ቁባት ባል የሆነው ዳዊት የነጠቁኝ ፡፡  ለዘመነናት ቤተሰቤን ይዤ ስጠለልበት የነበረዉን ቤት ለማፍረስና ቤተሰቡን  ለቁር ለሀሩር ለመዳረግ የተጉት ፡፡ያገር ያለህ !!! የጋግራን እሪታ  ጩኽቴን ስማ በኢትዮጲያ ዉስጥ በህግ አምላክ የሚባልበት ሰባዓዊ ተቋም የለም ሲባል እንደ አሊሆይ አላሊሆይ /አለ ወይ አላለም ወይ / እቆጥር ነበር ይቅር በለኝ ሀገሬ !!! ጩኽቴን ስማ  ፡፡ እስቲ ልብ በሉና ተመልከቱ  ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ  በተገበረበትና እየተገበረበት ባለው ህጋዊ  ይዞታ ላይ  ፣ 1280 ካ/ሜ ይዞታነቱ ተረጋግጦ የቋሚ ይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጠበት ይዞታ ላይ በ2002 ዓ.ም በቤንች ማጂ ዞን በመኤኒት ሻሻ የአርብቶ ወረዳ ላይ የተገነባ ቤት እንደ ከጫካ እንደወጣው  መጽሀፍ ከሆነ የጠቅላይ ሚኒስተሩን እጅ አስጨብጦ ከሳር ቤት ወደ ቆርቆሮ ቤት የተቀየረ ልማታዊ ባለሀብት ያስብልና የወረቅ ሜዳሊያ ያስጠልቃል/ በቁመና ምክንያት / እንጂ ቆርቆሮ ቤት ማየት ብርቅ በሆነበት የገጠር  ከተማ በበርካታ ገንዘብ የተገነባ ቤት አንድ ጎምቱ ባለጊዜ ከስምንት ያላነሱ አንጋቾችን ይዞ በግብር ሀይል ስም በጠራራ ፀሀይ  ንብረቱን ድምጥማጡን ሲያጠፉት የፈለጉት እኔን እንጂ የአፈር ቤቱን አይደለም ፡፡ስለዚህ በገዛ ሀገርህ  ከዚህ በደል በላይ የሚከረፋ  አድሎና መድሎ / ጥቃት /  የለም ንብረት ማፍራት የህግ መብት ከሆነ ጡንቸኞችን በህግ ጉልበት በሕግ አምላክ ለማለት እስከ በሀገሪቱ ጉዳይ ላይ የበላይና የመጨረሻ የዳኝነት  ሥልጣን ወደተሰጠው /የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት 80(2) / ፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት ድረስ ደጅ ጠናው ግና ምን ያደረጋል የደረሰብኝ መድሎና መገለል የወ/ፍ/ቤት በመ/ቁ 03631፣የከፍ/ፍ/ቤት በመ/ቁ17290፣ የክል/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/መ/ቁ 05493 እና የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ 151199 ሆነው  ህጋዊ ቤቱ በአገዛዙ ቱባ ባለስልጣኑ መዶሻ ያዥነት በአንጋቹቹ በጦር መሳሪያ አስፈራሪነት መዉደሙ  ትክክል ነው በማለት በየደረጃው  ለፍትህ ጥማቴ በሰፍነግ የሞላ ሆምጣጤ  እያጠጡኝ የሰባዊ ተቋም /ፍትህ/ ደጀሰላም የማሰማው ይግባኝ የጋግራን እሪታ ሆኖ ፍርድ ቤቶች ስንጥር ቁስሌ ዉስጥ በማስገባት ይበልጥ ያሳመሙን ነው ፡፡እስከ ዙፋን ችሎት /ሰበር/ መንከራተቴ   የፍርድ ቤቱን  ሂደት /ሥነ-ስርዓት / ለማሟላት ወይም ለማሞቅ ካልሆነ በቀር ፋይዳ አጣው ህጋዊ መብቴ በጠራራ ፀሀይ ተነጠቀ ጩኸቴ የጋግራን ዕሪታ ሆኖ ሰሚ አጣ እንዲያው ለፈረሰው እያንዳንዱ ቅጠል ለአፍራሽ አናጢ 40 ብር እንድከፍል ከአቅም በላይ ብር እየተጠየኩ ነው ይኼ ድረጊት ክፉ መንግስት ነው ከተባለለት ደርግ ኢትዮጲያን ለሚገድልና ለሚያስገድል በአንድ ጥይት ሰይፍ ገድሎ ለጥይት ከሚያሰከፍለው 5 ብር ይበልጣል እንጂ አያንስም ደርግ አንድ ሰዉን ብቻ ከብዙዎች መካከል ነጥሎ ፖለቲካዬን ደም በለበሰ አይንህ አይተሀልና  የዐይንህ ቀለም ስላስጠላኝ ዉጣ  እንደማይል  በማንበብም በጆሮ ጠገበም አውቃለው ፡፡ የንብርት ማፍራት መብት ይከበርበታል በተባለው በአገሬ እንደዚህ በደል ከደረሰብኝ የሌላው ሀገር ስርዓት ከዚህ የከፋ ምን ሊያመጣብኝ ይችላል ከባዕድ የተሸለ እናት ሀገሬን  አሳዩኝ አባቴ የተቀበረበት ሀገረ ኤርትራ ወይስ አባቱ ደቡብ ላይ ከተቀበረው ኤርትራዊው ወገኔ ጋር ተያይዘን ቀይ ባህር ወይም ሜድትራኒያን ባህር ለዓሳ እንደር እባካቹ ሀገር ዉስጥና ዉጭ ሀገር ላላቸው ኢትዮጲያዊያን በሙሉ( ያገር ያለህ !!!) የማሰማችው የጋግራን እሪታዬን ስለፍትህ እኩልነት ለእውነት ሰላም ግልጸኝነት እንደ አባቴ ቅዱስ ዲዩስቆሮስ ስጮኽ ባዕድ ሀገር እንኳን የሚያደርግልኝን የሚያደርግ ሀገሬን አሳዩኝ  ህዝቤ ግን ሀገሬ ነው !   ይህንን ቤተሰብ ከፈጣሪ ጋር በመሆን ታደጉ ፡፡ እኔ እንኳን በነፍስ አባት ስር ሆኜ ኮሽ ባለ ቁጥር የማሪያም ብቅል እየፈጨው ነኝ በሀገሬ የድንጋጤ ኑሮ ቁመናዬ በዚች ሀገር እንዳልኖር የሚያደርግ /እንደ ወያኔ አባባል / ስለዚህ  የሆነ ስዕል ነገር አይተሃል ወይም ድምጽ ነገር ሰምተሀል ተብዬ እንደ ዮሴፍ ወደ ግዞት አሊያም ወደ ላይ ወደ ኢየሱስ መሸኘቴ አይቀርም  ግን ኢትዮጲያዊያን ለቤተ- ኢትዮጵ እንደ አባታችን አብረሀም ችርነትን አታጓድሉባቸው ፡፡


Comments