በኢትዮጲያ በነበረው የአምስት ዓመት የፍሺስት ጣሊያን ወረራ ወቅት እትዮጲያ
ዉስጥ ሆነው ያልተወረሩትና እንግሊዝ ሀገር ለአምስት ዓመት በተንደላቀቀ ሎጆች የከረሙት ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ መያዚያ 27 ቀን
1933 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድል በተጎናጸፈፈ ግርማ ግልጽ በሆነ ፎርድ ኦቶሞቢል ከሜጀር ጄኔራል ካኒንግሃም ጋር ሆነው የኢንግዝን
ጦር ግራና ቀኝ አሰልፈው በታማኝ አርበኞች በተያዘ ባንዲራ ታጅበው
ዝግ ባለ ንጉሳዊ ግርማ ታጅበው አዲስ አበባ በድል አድራጊነት ገቡ ፡፡ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ በሰላም ከሚኖሩበት
እንግሊዝ በሰላም ሀገር ቤት በመግባታቸው ችር እግዚአብሔር በመካከላችዉ
እንድገኝ ስላበቃኝ በሰው አፍ የሚነገር ምስጋና የሚበቃ አይደለም ብለው ቡራኬ አሰምተው ለአምስት አመት ወደ ተለዩት ገነት ልዑል ቤተ-መንግስት መያዚያ 28 ቀን
1933 ዓ.ም ሲገቡ ጣሊያኖች ለኢትዮጲያዉያን ባላቸው ንቀት ለአምስት አመት ሲያውለበልቡ የነበረዉን ባንዲያቸዉን አውርደው እንኳን
በገነት ልዑል ቤተ-መንግስት በሰማይ ላይ የሚውለበለበዉን የኢትዮጵ ባንድራ በሰንደቁ ላይ ለሚያውለበልቡት አርበኞች አስረክበው ተክተው
መዉረድ ዉርደት መስሏቸው ያደረጉት ለገር ቢኖር ጃንሆይ ያጅበው የነበረው ሜጀር ጄኔራል ካኒንግሃም እዝ ስር የነበረዉን ሜጄር ጄኔራል
ዊዝሮል በሜጀር ጄኔራል ካኒንግሃም በተላከለት ቀጭን ትዕዛዝ የኢንግሊዙን ሰንደቅ ዓላማ /ዩኒየን ጃክ / በገነት ልዑል ቤተ-መንግስት
ከፍ አደረጉት የጃንሆን በእንግሊዞች በቀኝና በግራ መታጀብ ከሱልልታ እሰከ አዲሳባ ብቻ ሆነ ቤተ መንግስት ግን ከፍ ማለት አልቻሉም
ከፍ ያለው ዩኒየን ጃክ ሆነ ፡፡ምን ያድርጉ ጃንሆይ በኢንግሊዝ ባሉት
ሎጆች ሲዝናኑና ሲመለሱም ሆሳዕና የዳዊት ልጅ እየተባለላቸው ነበር
ለባንዲራ የተዋጉ አልመሰላቸዉም ጃንሆይ ሆኖም ሀገር ወዳድ አርበኞች ላባቸው ፣ ደማቸው፣ እንዲሁም የሰማዕታ ሕይወት
የዩኒየን ጃክ እንዲውለበለብ ባለመሆኑ ለባንዲራው ሲሉ ለኢትዮጲያ
ነፃነት በጣሊያን የተገደሉትና የተሰዉት ኢንግሊዛዊያን አፅም በከርሰ መቃብር ትኩስ ሬሳ ሁኖ በሚገኝበት ሰዓት ጃንሆይ ጠራርገው
ከሀገር ያስገቧቸው የወዳጅ ጠላቶች ሆነዋል ፡፡መጡብን እንጂ አልመጡልንም
ልያወጡልን ሳይሆን ሊያስወጡን ማን ሞኝ ነው ፈረንጅ አስክሬኑን ሳይሸጥ
የሚሔድ ሲሉ ታዘቡት አበሾች፡፡ ዉለታ የሚከብደው የኢትዮጲያ ህዝብ ለባንዲራ ይሉንታ የሌለው በመሆኑ በይሉንታ ላለማለፍ ሲያቅማማ
ጃንሆይ ለነፃነት መረጋገጥ ሲባል በዲፕሎማሲው መንገድ እንዲፈቱና እንዳስገቡ እንዲያስወጡ ኃላፊነት ተሰጠው ፡፡በዚህም መፍትሔ ያደረጉት
ለአንድ ቀን በድጋሜ ሀገርን ጥለው ወደ ንስርን/ግብፅ / ሲዊዝ ካናል በስዉር በለሊት እንደ ኒቆዲሞስ በመሔድ የአሜሪካን ፕሬዝዳንት
ፍራንክሊን ዲ.ሩዝቬልት በ1934 ዓ.ም ወደ መካከለኛ ምስራቅ በመጡበት ወቅት ማልዱኝ በማለት በአዛዉንቱ ዲ.ሩዝቬልት ኢንግሊዞች
የኢትዮጲያን ህልዉና መቀናቀን እንዲወገድ እንዲማልዱ ተማጽነው አሜሪካን ኢትዮጲያን ከባቄላ ፍላት እንዲያተርፍ የህግ ባለሙያ ሚስተር ጆን ስፔንሰር በሁለተኛ የአለም ጦርነት አዉሮፓ ዉስጥ ከሚገኙበት የጦር ግንባር ተፈልገው ወደ ኢትዮጲያ በመምጣት በሳቸው
( በ3ኛ የፋሺስት ሀገር ጉልበት ) በ1934 ዓ.ም ጥር 23 ቀን በኢትዮጲያና በኢንግሊዝ መካከል አዲስ አበባ በተረቀቀና በተፈረመ
ስምምነት መሰረት አሜሪካን ከጉድ አወጣን ጣሊያን ከኢትዮጲያ ጫንቃ ላይ ወረደ በአሜሪካን የበላይ ጠባቂነት ኢትዮጲያ አግአዚት ሀገር ሆነች ተባለ ፡፡ጥንትም ነፃ ሀገር
ነበረች ይባላል ፡፡በዉኑ ነፃ ሀገር ነበረችን ???ኢትዮጲያ በአውሮጳ
ቀኝ ግዛት መዳፍ ዉስጥ ያልወደቀችው ሀገራችን አባጣ ጎርባጣ ስለሆነች ወይሰ አውሮጳዊያን የሚፈልጉት አንዳችም ጠቃሚና ማራኪ ነገር
ስለሌለን ነው ፡፡ሆኖ ሆኖ ግን ከጃንሆይ ይልቅ አያቴ ቦሎኮሮይ ፍሺስት ጣሊያንን ከሀገሩ ለማስወገድና በምትኩም አርንጓዴ ቢጫ ቀይ
ባንዲራ ለማውለብለብ እስከ ደቡብ ሱዳን ቦማ ድረስ በእግሩ ተጉዞ ነፍጥ አንግቶ በማምጣት የጣሊያንን ግባተ መሬት በአባቱ መኤኒት
ደንብ መሰረት ጠለቅ አድርጎ ቀብሮታል የጣሊያንን ሰንደቅ ከዓላማው ላይ መዉረዱን ያውቃል ሆኖም ግን የኢንግሊዞቹ ሰንደቅ ዓላማ የሆነው /ዩኒየን ጃክ / በገነት ልዑል
ቤተ-መንግስት መሰቀሉን ኢንግሊዝና አሜሬካ ካሉት ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴሎች ወርደው መጠው ስልጣን የያዙትም ሆኑ በጣሊያንም እቁብ
የሚሆን ደመወዝ እየተከፈላቸው ከርመው ኋላም ከባንዳነት ወደ አርበኝነት በአንድ ጀንበር ተቀይረው ስልጣን በያዙ ጉምቱ ባለስልጣናት
ይህንን የታሪክ ሽሚያን አላረዱትም ፡፡ እኔ ግን ተረዳዉት ፡፡ እባካችው
ተረዱት ፡፡

Comments
Post a Comment