ቦንጋ ከተማ
በሰሜን፣ በምስራቅ ፣ በምዕራብ ተዘዋውሬ አንዳንድ ከተሞችን ለማየት ሞክሪያለው ቦንጋ ከተማ ግን የተፈጥሮ ድንግልናዋን ሳታረክስ የቆየች ዉብ ከተማ ስለሆነች በቅንዝራም አስተያየት ነው የምገረምማት የቦንጋ አየር ንብረት ፣ ጥቅጥቅ ደን እንኳን እኔ አገር በቀሉን ቀርቶ መጤዎቹን ጎብኚዎችን ያስገረመማቸወ መሆኑን ስለ ‹‹ መኤን ›› ሳጠና ቃኘት ቃኘት ካደረኳቸው ፀሐፍትና ጎብኝዎች ዉስጥ ሊኦን የተባለው ‹‹ የኢትዮጲ ዕንቁ ›› ሲል ማክስ ግሩል ደግሞ ‹‹ማራኪና ያልተበረዘ የተፈጥሮ ዉበት ባለቤት ›› በሌላ በኩል ዳርሊ የተባለው ‹‹Lovely wilderness›› ሲሉ ያሞካሹትን ላንጌ የጠባለው ኦስትራሊያዊ ባየው ነገረ ተደምሞ ‹‹ሥያሜ አጣውላት ›› ሲል የተፈጥሮ ፀጋ ባለቤቷን ቦንጋ ዘፍትረት መፀሐፍን መጀመሪያ ከተጠቀሰች ከተማ ጋር ለማስተያይ ከጅሎም ነበር፡፡ የዛኔ አዳምና ሔዋን በ6ኛ ቀን በገነት ሲፈጠሩ መብል ይሆን ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ የበቀለው ዛፍ ሰባዊው ፍጥረት በአብሶው ምክንያት ሲወጣ አራዊቱ ግን ዛሬም ድረስ ለፈጣሪያቸው ምስጋና የሚያቀርቡ በመሆናቸው ፈጣሪ መብል ይሆን ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ ያበቀለው ዛፎቹ ግን ያው እንዳሉ በሚታዩት ደኖች መካከል በጉሬዛዎችን ማህሌታዊ ጩኽት የሚወጣዉን ዝማሬ ሰምቶ ልቡ የተመሰጠበት ጉብል እኔብቻ አለመሆኑን አረጋግጫለው ፡፡
ቦንጋ ከተማ ላይ ሆነህ የምትደመመው በእግዚአብሔር ሰራሽ (ጥቅጥቅ ደን፣የተፈጥሮ ድልድይ፣ባርታ ፏፏቴ ፣ማኪራ ቡና ወዘተ) ተፈጥሮ ብቻ አይደለም ይልቁኑም በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የታነፁ ዕድሜ ጠገብ አብያተ-ክርስቲያናት አስከአሁን መስቀልን እንደያዙ መቆየታቸው ነው ፡፡ ከእነዚህ ዉስጥ በሃ ጊዮርጊስ የተባለውን እጅግ የገነነ ደብርን ላስቃኛችው ፡፡ይህንን የጊዮርጊስ ደብረን ለማየት የወሰወሰኝ ምክንያት ከነበሩት አንዱ ድብሩ የተገነባው በመለክ ሰገድ (በአፄ ሠርፀ ድንግል ) የተተከለ መሆኑን ታቦቱ በሳቸው ዘመነ መንግስት እንደተቀረጸ አንብቤ ስለነበረ ነው ፡፡ እኒህ አፄ በነገሱበት ዘመን ፤ ከምፅዋ ወደብ እስከ ቦንጋ ከተማ እስከ በሃ ጊዮርጊስ ድረስ ያለውን የመንገድ ርዝመት ስናስተውልና አፄው የምስራቹን ወንጌል ለማዳረስና ለኢትዮጲያ የዋሉትዉለታ ሳስታውስ ቀጥሎ ያለውን ሐተታ ለማድረግ እንነሳለን ፡፡

በአፄ ስርፀ ድንግል መልክ ሰገድ (ነገስታቱን ያሰገዱ) የነገሱበት ዘመን ከ1553 እስከ 1587 ዓ.ም ነው ፡፡በዚያን ጊዜ መንገድ ወይም ሌላ የመገናኛ ዘዴ አልነበረም ፡፡ ከምፅዋ አስከ ቦንጋ መራራቅ ስንት እንደሆነ ቀደም ባለው ላኬት ልዘረዝረው እፈልጋለሁ ፡፡ ከምጽዋ እስከ አስመራ 116 ኪ/ሜ ፤ ከኣስመራ አዲስ አበባ 180 ኪ/ሜ ፣ከአዲስ አበባ እስከ ቦንጋ 450ኪ/ሜ ከቦንጋ እስከ በሐ ጊዮርጊስ ከግማሽ 20 ኪ/ሜ እንገምተው የርዝመቱ ጠቅላላ ድማሬ 1666 ኪ/ሜ ነው ይህን ያህል ርቀት ሳያግዳቸው ወንጌል ለማስተማር ፣ለማጥመቅና ደቀ-መዝሙር ለማድረግ ያሰቡት የትግሬ ቡሻሽ ጎሳና ነገስታት ዝርያን ለማጠናከር አለመሆኑን የሚያጠናክረው በ18ኛ መ/ክ/ዘመን አጋማሽ ላይም በካቶሊኩ ካፑቺን የሐይማኖት መሪ በመሆነው አቡነ ማሳያ የተገነቡትን አብያተ ክርስቲያናትን ስንቆጥር የዚህ ዉብ ምድር ፍጥረት የምስራቹን ወንጌል ለማሰማት የቆረጡ እንጂ ሌላ ተልዕኮ አይታየኝም ፡፡ አፄ ስርፀ ድንግል የአያቶቹን የባሕረ ነጋሽ ፈለግ የተከተለ ነው ፡፡ ቅድመ አያቱ አፄ ናዖድ በዘመነ መንግስታቸው በአረቦች የሚደገፉ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚያነሱባቸዉን ጦርነቶች ድል እያደረጉ ሀገርን ስለሚጠብቁ ፤ ወልዳቸው አፄ ሰርፀ ድንግል ወራሪውን ቱርክ ምፅዋ ላይ ድል ነስተው እንዳባረሩት ታሪክ የሚነግረብ ሲሆን በደቡብም ቱርኮች እንዳይገቡና ለዛሬዉን በወንጌል መጥለቅለቅ በአደራ ይቀመጥ ዘንድ የበሐ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ማሰራታቸውንም ዛሬ እኔ በልዩ አስታውሳለው ፡፡ የዚሁ ስራቸው መዘከሪያ ከታቦት የበለጠ ሌላ የታሪክ ቅርጽ የለምና እሱን ማየት ፤ የሱን መጽሃፍ ማንበብ ፤ ድብሩን መጎብኘት የገሩን ታሪክ ለሚወድ ሰው እጅግ አስፈላጊና አስደሳች ነውና እንድንጎበኘው አደራ ፡፡
በአጼ ሠርጸ ድንግል ታሪክ መንግስት የሚነግሩን ፅሁፎች በአውሮፓ ቤተ መፅሀፍት ተሰማርተው ይገኛሉ ፡፡ የፅሁፎቹ መዘራት ለሐገራች ታሪክና ስነ ጽሑፍ በአለም ላይ መታወቂያ ሆኖ ብዙ ፍሬ እንዳፈራ የግእዝ ቋንቋን ያጠኑ ሊቃውንቶች እነዲልማን ፤ እነዞተንበርግ ፤ እነጎልድ ሽሚድ ያጤኗቸው መሆኑን መጥቀስ በቂ ነው ፡፡ የአፄ ሰርፀ ድንግል ታሪክ ነገስት ቅጂዎች አንዱ ቦድልያን ቤተ መጽሐፍት በኦክሰን ከተማ በቁጥር 29 የተመለከተ 1585 ባለው አመት የተፃፈ ነው ፡፡
ሁለተኛው በፓሪስ ከተማ በሚገኘው በብሔራዊ ቤተ መጽሐፍት (ቢብሉይቲክ ናስዮናል) በቁጥር 143 የተመለከተ ነው ፡፡ ሶስተኛው የሩፔል መፅሐፍ (ኮዴክስ ሩፔሌንሲስ) ተብሎ በፍራንክፋርት ከተማ ይገኛል ፡፡ ፋራንክፋርት ከተማ አሁን የኢትየጲያ አየር መንገድ መነሻውና መድረሻው ያደረገው የጀርመን ከተማ መሆኑን ማስታወስ ይጠቅመናል ፡፡ የአጼ ሠርጸ ድንግል ታሪክ የኮሎኒያሊስቶች እና እነርሱን የተከተሉ የሚሲዮናውያን ባህልን ከሰሩ የሚነቅል ነው ፡፡ ኮሎኒያሊስቶች የሚሉት ከአጼ ሚኒሊክ በፊት የኢትዮጲያ መንግስት ግዛት ከሸዋ አያልፍም ነበር ይላሉ ፤ ከዚያ ወድያ ያለው ሐገር ግን አፄ ሚኒሊክ መንግስታቸውን ያስፋፉቡበት አዲስ ገዛት ነው ይላሉ ፡፡ ይህን ተንኮለኛ ባህላቸውን ከ ቦንጋ ወዲያ በከፋ ሐገር የሚገኘው የበሐ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በጨለማ ላይ በርሐንን እንደሚሰራው ትርእይት ሆኖ ሐሰታቸውን በትኖ ያጠፋቸዋል ፡፡ ሚስዮናውያን የተባሉትም ኢትዮጲያን ለሁለት ለመክፈል ታጥቀው ኢትዮጲያን ሰፊና ለም አውራጃዎች በድሮ ዘመን ክርስትና አልነበራቸውምና እኛ ሚስዮናውያን ለመጀመሪያ ጊዜ ብርሀነ ወንጌልን ገልፀንላቸው ፡፡ ስለዚህም ለፀሎት አደራረስ ፤ በቅዳሴ አቀዳደስ እና ለማህሌት አቋቋም ቱባ ባህላቸዉን ትተው ቋንቋቸውና ባህላቸው የኛው የሰባክያን መሆን አለበት ፡፡ የመጥሪያ ስማቸውም በኛው ሀገር ስም እንዲወጣላቸው የጾም ስርአታቸውም የበአል አከባበራቸውም ፤ የዘመን አቆጣጠራቸውም የኛው የራሳችን እንዲሆን ብለው የወሰኑት ኢትዮጲያውያን እርስ በርሷ ለማከፋፈል የሰሩትን የተንኮል ስራ ቀደም ብሎ የሀገር ቤት መጠሪያ መጠራት እንገ ፋራ የዉጭ ቋንቋ አለማዉራት እንደ ማሀይም አስቆጥረዋል ( ይህ ሴራቸው የአዛዉንቶች ተረት ብቻ አይደለም ዛሬ በወንጌላዊያን አማኖችም ስነ መለኮት ሊህቃን ጭምር የሚወገዝ ቢሆንም ) ይበልጥ የበሐ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ታሪክ አበነነባቸው ፡፡ ይህን የመሳሰሉ ስሜቶች በልቤ ውስጥ ሲቆሮቁሩኝ ኑሮ ፤ ቦታውን ሳልጎበኝ ደብሩን ሳልሳለም ተመለስኩኝ ፡፡ ለቦታው መሪ እንድሆን አጥኚዎች የፃፉትን በማንበብ ፤ ታቦቱ እንኳ ከእየሩሳሌም የመጣና ፅሁፉን በአጼ መልክ ሰገድ ዘመን መሆኑን በዋናው ደጃፉ ላይ ኢትዮጲያ የብር ገንዘቦች ፤ የብር መስቀሎች ፤ የብር ስእለቶች ገፀበረከቶች የተለጠፈበትን ፤ እንዲሁም መቅደሱ በር ላይ የብር ገንዘቦች እንደተለጠፉበት ይነገራል ፡፡
የበሐ ጊዮርጊስ ደብር ከባሕር ላይ ከፍተኛነቱ 2200 ሜትር ነው ፡፡ የአየሩ ውበትም በዚሁ ሊገመት ይችላል ፡፡ ሌላው የሸፓ ገብርኤል ቤ/ን እና የሽፓ ማርያም ቤ/ን የነገሰባቸው ቦታዎች እንደ በሐጊዮርጊስ ባይወሩም ቅሉ ፤ በጥንትነታቸው ረገድ ተመሳሳይ ጊዜ ሳይሆኑ አይቀርም ያሰኛል ፡፡
መያዚያ 2012 ዓ/ም
አዲሱ ደምሴ ( መሪራስ )

Comments
Post a Comment