ከዜሮ ዉጭም ሌላ ቁጥር አለ

እነዛኛዎቹ ሀገራት እንደሀገር ህልዉናቸዉን ለማስቀጠል በርካታ ነፃና ገለልተኛ ተቋማትን በሙሉ ፍላጎታቸው አስበው ገንብተዋል በእነዚህ በአለት ላይ በተገነቡ ነፃ ገለልተና ሰባዊ ተቋሞቻቸው ዜጎቻቸው ብቻ አይደለም ምድራቸዉን የረገጠ ሰው ሁሉ እምነት አድሮባቸው  በልበ ሙሉነት ‹‹ በህግ አምላክ ›› ሲሉ እኩያንን ከእኩይ ድርጊታቸው ያስቆማሉ ፡፡ በተቃራኒው እነዚህኛዎቹ ኋላ ቀርና ደሀ ሀገራት በሰባዊ ተቋማቱን  በነፃና  ገለልተኛ ሁኔታ እንዲቆሙ የአርዳታ መዳፋቸዉን ስለማይዘረጉላቸው ተቋማቱ በእከክልኝ ልከክልህ / የእከካሞች / ሽርክና ተደቁሶ ስለሚገነባ ተቋማቱ የግለሰብ ህልዉና በላይነት ተጭኖት በሰባራ እግሩ የሚያነክስ ሲሆን  ዜጎች ‹‹ በህግ አምላክ ›› የማይደፍሩበት ቢኖሩም   ብዙዉን ጊዜ በዳይ ተበዳይን ‹‹ በህግ አምላክ ›› ፀጥ ረጭ ብለህ ግባልኝ(ተገዛልኝ ) የሚልባቸው እንጂ ተበዳይ በዳይን በድፍረት ‹‹ ህግን ፍራ ›› ለማለት ማገዶ ፈጂ እንጂ ማገዶ ቆጣቢ አይደለም ፡፡ እነዚህን ለብልፅግናና ርቱዕ አዕማድ የሆኑ ሰባዊ ተቋማትን ነፃነት ገለልተኛነት ማድረግ ቀኖና አድረገው  የሚተገብሩ ሀገራት በእነዚህ ተቋማት ላይ የሚሰሩ መኳንንትም ሆነ ሹማሙንት የሚቆሙበት እግር እንዲሆራቸው  የገዢው ፓርቲ አካል ‹‹ የነፍስ አባት ›› ስለማያደርጉና በዕውቀትም ሆነ በሞራል ብቃት ተቦክተው ስለሚገነቡ  ተቋማቱ ጥቂቶቹ ብቻ የማይፈነጩበት ግን ደግሞ ብዙሀኑ ሕዝብ ከሚተረፈረፈው ፀበል የሚራጩበትና የሚፈወሱበት ተቋማት ስለሆኑ መንግስታት ሲቀያየሩባቸው ከግለሰብ ዘመዳማቾች ህልዉና ጋር የተሳሰሩ ስላይደሉ  በብቸኝነት ጠኔ አይመቱም ለመሬት የከበዱ ስለሚሆኑ ተቋማቱ በማንም ሰራይ/መጋኛ/ ስለማይለከፉ የሁለት ሰባት ፀበል አይዳረጉም ፡፡ ይልቅስ ራሳቸው  መድህን በመሆን ለሀገራ ፈውስ ይተራፋሉ ፡፡ 
 በዚህች ፅሑፍ  ‹‹እከክልኝ ልከክልህ / የእከካሞች / ሽርክና ›› በሚለው   ‹‹ እከካም ›› የሚለዉን ቃል በዚህ ፅሁፍ ዉስጥ ፋይዳዉን የማናገኘው ቃሉ ዘይቤ ጠቀስ ምፀታዊ ንግግር ተጭኖት መቅረቡን ከግምት አስገብተን ያየነው እንደሆነ ነው፡፡ይህንን ምፀታዊ ንግግር በቀጥታ የተዋስኩት የአከኬ ቡድን የተፀናወታቸውና በሽርክና ቡድን ዋግ የመቱት ሰባዊ ተቋማት እንደሚያደቁ ‹‹የመደመር ›› መፀሐፍ ለንባብ ሲበቃ ካተኮረባቸው ነጥቦች ዉስጥ ይህንን አስመልክቶ ከገፅ 126-130 ላይ የተገለፀዉን በተመረቀበት ዕለት 4ኪሎ በሚገኘው የአንድነት ፓርክ የሚኒሊክ በርጩማ ላይ ቁጭ ብዬ ሳነብ  ያጤንኩት ነው ፡፡ስለሆነም መጤ ቃል አይደለም ፡፡ የጽሑንፉን አስፈላጊነት ለመረዳት ከዚህ ቀደም ስለ‹‹ቆንጢንጢኖስ ››ያፃፍኩትን ማንበብ ያሻል ፡፡ስለሆነም ዛሬ በዚሁ ‹‹እከክልኝ ልከክልህ / የእከካሞች / ሽርክና ›› ወይም በአሜባ አስተኔ (አሜባ ብጤ ) ሴል  ላይ በማንም መነጠቅ የማይቻለዉን ብዕሬ ዉስጥ ቀለም ደፋው እንደተከተለው አፈሳለው ፡፡  
 
በበጋው መጋቢት ወር 2010 ዓ/ም አበባ ፈነዳ ! አበባ ፈነዳ !አበባ ፈነዳ! የሚል ወሬ ከገጠር አስከ ከተማ ተሰማ ለእኔም ጆሮ ጠገብ ሆነ ለምናልባት  ቀረብ ብዬ ሳስተውለው  የፈነዳው ለዉጥ ለወዲያው በቃልም ሆነ በተግባር የአቦሸማኔነት ፍጥነት ነበረው ፡፡አንዳድ ነገሮች ላይ የወሰደው የልጅ እርምጃ ብጤ ቢሆንም በሒደት ጣት መጥባት ከተወ የተሸለ አበባ ያፈነዳልናል ብዬ በግሌ  የለግላጋ ምኞቶችና ተስፋዎች ባለፀጋ ለመሆን ነፍስም አልቀረልኝም ፡፡ የጉርምስና ልሳኑ በሆነው ‹‹መደመር›› ለሀገር ብልፅግና የሆነው  ሰባዊ ተቋማት የደቀቁት እና የሚያነክሱት ‹‹ የቤተ-ዘመድናና የጥቅም ሸሪኮች መረብ የወለደው ‹‹ፖሊዮ ›› ነው›› ሲል  በግልፅ ተዘባበተ  እነዚህን ተቋማት በልከክልህ እከክልኝ የጥቅም ሽርክና ላዳሸቁት መፍትሔ ጠንካራ የቅርብ ክትትል ፣ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን አስፍኖ ከግለሰብ የበላይነት ለማላቀቅ የተግባር ዕርምጃ መዉስድ ነው ብሎ  ቀደም ብሎ አንዳንዱ እኔም ጭምር የማከብራቸው በአንድ ሁለቱ ሰዎች ቁምጣ ዉስጥ ዘልቆ በቁንጥጫ መዥለግ ያደረገበት ጣቱ ከደም ንፁሕ መሆኑን ቀየደ፡፡ቁንጥጫው  እላይና  ፀሐይ መዉጫ አከባቢ በመሆኑ በሚያሰሙት ማንቋረር አታችና ፀሐይ መጥለቂያ  ያሉት በርካቶቹ ከአንቋራሪዎች የከፉቱ  ደግሞ ያ ጣት ጭናችን ዉስጥ ትገባለች ብለው ባደረባቸው ስጋት  ለምናልባት ያሉትን  የሻማ ብር( ለእስር ሲዳረጉ ለእስረኞች የሚከፈል) በኪሳቸው ይዘው የሚዉሉ የሚያድሩ በረካቶች የነበሩ መሆኑን የዓይን ምስክር ነኝ ፡፡ ግና ምን ያደርጋል ይህ ተስፋ ያደረግነው የበጋ አበባ ያፈነዱት የለዉጡ ሐዋሪያት( እንዲሁም  ቀማሪ ) ነበርን ባዮች መካከል አስማሚ የሆነ የፖለቲካ ትንተና እና ተግባር በመታጣቱ ሁሉንም ግራ አጋባ በሰበቡ የሻማ ብር ቋጣሪዎች ብሩን ከመቀነታቸው ፈተው ‹‹ ለዚህ ለውጥ አሰራለታለው እንጂ  አልሰራም ›› ባዮች በአንዳንድ ቦታዎች በተለያ እኔ ባስተዋልኩበት ያለስጋት ለዉጡ ያለጭድ እንደመረጉት ጭቃ እንዲፈረካከስ  እየተጉ ዛሬም ድረስ አሉ ፡፡ ለውጡ በአንዳንድ ቦታ በግለሰብ ጥንካሬ  በአለት ላይ እንደተሰራ ቤት የጠነከረ መሆኑ ባይዘነጋም  ፡፡ አነዚህ እንደ አሜባ-አስተኔ( አሜባ ብጤ ወይም ሴል ) በለዉጡ አከርካሪ ዉስጥ ተቆራርጦ በመግባት ለዉጡን እንደ ደሀ አደግ ልጅ እያደር እየዋለ እንዲከሳና እንዲኮሰሰ ሲያደርጉትና ሥራዓቱን ሸጠው ያለ ፀፀት ሲሸረምዱት ከልካይ የላቸዉም እነዚህ ናቡከደፆሮች  ሕዝቡ ከለዉጡ የተቸራቸው  የመንግስታዊ መዋቅር ላይ ተፈናጠው እንደ ዱራ ሜዳ በሥማችን ላቆሙት ምስል የማይሰግዱት ላይ የእቶን እሳት ሰባት እጥፍ ሲያድዱበት አይ ሁለት እጥፍ ይሁልኝ ተብሎ አቤት የሚባልበት ሰባዊ ተቋም አለ አግኝታለው የሚል ይጦቅመኝ ፡፡አጥቻለው ፡፡ ይልቁኑም የፖለቲካ ችንካር ተቸንክሮበት ቀራኒዮ የሚዉል ፣ በሰፍነግ የሞላ ሆምጣጤ የሚጋት ለዓይንም ሆነ ለጆሮ ጠገብ ነው ፡፡እነዚህም የቀረናው ስምኦን ያለህ ይላሉ ፡፡  ባራንባራሶቹ   የግል ኬላቸዉን ዘርግተው   የለዉጡን አባልም ሆነ ደጋፊ ፈትሸውና አስፈትሸው ወደመጣበት ለመመለስ ደፋሮች ናቸው  ነገ እሱን አስከ ኪሱ እንደሚፈትሽ ዘንግተው ዛሬ ራሳቸዉን በራሳቸው ላይ አክሊለ -ስልጣን ጭነው ( መንግስት ባያውቅም ቅሉ) ይዞታቸዉን እያስፋፉ  ታዘብኩት ቦታ ህዝብ ከለዉጡ በፊት የነበዉና ያወገዘዉን ስርዓት ‹‹ ማረኝ ›› ያለም አልታጣም ፡፡ እነዚህ የአሜባ ብጤ ሴል/ህዋስ / በልከክልህ እከክልኝ የጥቅም ሽርክና ተቧድው የለዉጡን አበባ እያራገፉ የዛገዉንና የሚራገፍን ነገር እያደሱት አሮጌዉን ስርዓት ከለዉጡ በፊት ከነበረው በከፋ እያደነደኑት እየወፈሩት መሆኑን ለዶክተር ልንገረው ወይ ንገሩልኝ፡፡ በእርግጥም  አንዳድ ቦታዎች ለለውጥ የቆረጡና ሕዝቡ ለዕድገት ስተጉ እኔ በታዘብኩትና መረጃ ባለኝ ቦታዎች መንግስት እቁብ የሆነ ደመወዝ እየሰፈረላቸው ለዉጡን እንዲቀለብሱ ዕድገቱን እንዲያቀጭጩ እንዲያደናቅፉለት የመደባቸው ይመስል  አንባገነንነት ሕጋዊ ሆኖ  መድሎ ተቋማዊ ሆኖ ፋፍቷል ሀይ ባይ ካልፈጠነ ፡፡በአንድ የሰው ( የግለሰብ ) የአዕምሮ ዉጤት እንደ ተራ ልፋት ቆጥረው በጀብደኝነት ዜሮ ያደረገ ‹‹ ዜሮ ጭንቅላት የሆነ  ሰው ›› የለዉጡን አንድ ከፍተኛ ስራ ይመራል ሲጀምር  እንደዚህ ዓይነት ሰው ከዜሮ ዉጭ ያውቃል ቢባል ይደንቀኛል የሚያሳዝነው ሕዝቡን ከግብፅ ወደ ከነዓን ለማሻገር ስንት ሙሴዎችና አሮኖች እያሉ ከባህር ራሳቸው መሻገር የማይችሉትን ፈረኦኖችን የሚያድቀድም ለዉጥ መታዘቤ ነው  ፡፡ ይህ ደግሞ በለዉጡ ኃይል ትኩረት ከተነፈገው የዚህ ዉጤት ደግሞ ሁሉም ከሁሉም ጋር አሸናፊ የሌለው ግን ፈጣሪ ብቻ አሸናፊ የሚሆንበት( የአርማጌዲዮን አይነት ) ጦርነት  እንደሚጠብቀን ለመተንበይ አዋቂ መሆን አያሻም ፡፡ ስለሆነም  ለውጡ ተቋማዊ ሆኖ ከጉለሌ ወደ ባሌም ወደ ቦሌም ይገባል እያልኩኝ ዛሬም  የምርጡ ጦማሪ የሙሉጌታ ሉሌ ‹‹ሰው ስንፈልግ ባጀን›› መፀሐፍን አንብቡ እያልኩኝ ለዛሬ አበቃው ቸር ያገናኘን ፡፡   
አዲሱ ደምሴ( ቦሎኮሮይ ) መያዚያ ወር 2012 ዓ/ም  

Comments