‹‹ የአበሻ ጠረፍ የሆነውን የሹሮን ወሰን አልፎ አልፎ ለመግባት ተወስኖ ነበር በቤንችና በሹሮዎች አገር መካከል ያለውን ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ አቋርጠው የሚያልፉ መንገዶች በጣም ጠባብና አስቸጋሪ በመሆኑ ጫካዉን እየመነጠሩ ሰፊ መንገድ የሚያወጡ ሰራተኞች በአስቸኳይ ከጦሩ ምልመላ እንዲሔዱ ከራስ ወ/ጊዮርጊስ ስለታዘዘ መቶ ሰዎች ተመደቡ ….አክለውም፡-ሹሮዎች ምን እንደሚጠብቃቸው ያውቃሉ

ታሪኩን ላውጋችው አንዳንዴ የማሰቢያ ጊዜ አግኝቼ ሳስብ አንጀቴን በልቶኝ በልቶኝ የክራር መከርከሪያ የምታክል ቀጭን ጅማት ብቻ ከሚያስቀሩልኝ ታሪኮች ዉስጥ የጣሊያኖች ወታደሮች በአደዋ ጦርነት ወቅት እንደ ነጭ መጋዣ እየመሰለ በየዱሩ ሆዱን ገልብጦ ለመሞት መምጣቱ ፣ ምኒልክ ከአድዋ ድል በኋላ ከመረብ ማዶ ወዳሉት ጣሊያኖች ዘምተው ቢያባርሯቸው ትግረኛ ተናጋሪዎች አብረው ስልጣኑን ያቀናቀናሉ በማለት ወታደሮች የኢትዮጵያ ግዛት ነበር ወዳሉት ወደ ደቡብ ምስርቅና ምዕራብ ለማቅናት በሚል ዘምተው በየጫከውና ጢሻው የአሞራና የጅብ ሲሳይ የመሆናቸው እና በካፋና በቤንች ብሔረሰብ ዘንድ ተፈሪ ነበረውና ልጁን እንኳን በሚረግምበት ጊዜ << suri Ginona >> ወይም የሹሮ ጦር ይውጋህ የተባለለት የሹሮ ብሔረሰብ በአበላ ባይ አንገቱን መድፋቱን ጉድ ሳስብ ነው ፡፡ ስለ አድዋው ድል ከአገር ዉስጥ ጸሐፍት ዉስጥ አለቃ ተክለ ሥላሴ ስለ ጦርነቱ እንደ እሳት ላንቃ በሚንቀለቀለው ብዕራቸው ሲተርኩልን ጦርነቱ ላይ ዓይኔ የታዘበው ‹‹ ጣሊያኖች ወደ አድዋ የቀረቡት በጨረቃ ፣በጠጠር ፣ ባቀበት በቁልቁለት ፣ የጥይት ኮሮጇቸውን ፣ የዉሃ ታንካቸውን ፣ተሸክመው እንቅልፍ አጠው ሁለት ለሊትና አንድ መአልት ከራብና ከጥም ጋር ተጉዘው ስለነበር እንደ ደረሱ መድፋቸውን ጠምደው መተኮስ ሲጀምሩ እንደ እንዝርት የቀለለ የጁየ፣ከነብር የፈጠነ ቤጌምድሬ( ጎንደሬ)፣ከቋንጣ የደረቀ ትግሬ፣ከአሞራ የረበበ ሸዌ፣ከንብ የባሰ ጎጃሜ፣የጣሊያንን ጦር እየዘለሰው በየጎዳናው እየዘረረው አውሬ የነጨው ነጭ መጋዣ እየመሰለ በየዱሩ ሆዱን ተገልብጦ ወደቀና የአሞራ ሲሳይ ሆነ … ጣሊያን ያመጣው መድፍ ሁሉ ከነጥይቱ ከነ መንኮራኩሩ በየመንገዱ እየወደቀ ተማረከ … በየጫካው የቆሰለው የጠላት ጦር የሚያነሳው አጦ ሞት ሲያጣጥረው የወገን ጦር ከወዲህና ወዲያ አየት እያደረገ ለኩሶ ከሰል አድርጎ አሳርሮ ፈጃቸው ፡፡በሌላ የብዕር ቀለም ደግሞ ለጣሊያን አዳሪ ( ባሻ ባዙቅ) ነበር የተባለው ፕሮፌሰር አፈወርቅ ገብረ እየሱስ ሲጽፍ ‹‹ ጣሊያን ወታደር ለሊቱን በሙሉ በጀርባው ከባድ ኮሮጆዉን ፣በጫንቃው ጠብ መንጃዉን ፣በቀኝ ጎኑ የጥይት ከረጢቱን ፣ተግራ ገኑ የዉሃ ታንካውን ተሸክሞ የገረረ ከባድ ጫማውን አስከ ጉልበቱ ድረስ አጥልቆ ድልቅፍቅፍ እያለ በዚያ ጪንጫ በዚያ ሙቀት አቀበትና ቁልቁለት ፣ያ ሁሉ ፈረንጅ ፣ያሁሉ ጎበዝ ፣ያ ሁሉ ወጣት ልጅ በአገሩ እንዲያ ያማረበት በአድዋ ተራራ ላይ ግን እንደ ላሊበላ ሳሚ መስሎ ከርፈፍ ከርፈፍ እያለ ሲማስን ዉሎ ጦር ሲጀምር መናኝ መነኩሴ እንጂ ወታደር አይመሰልም ነበር ፡፡ ሆኖም የሸዋ ፈረሰኞች፣የጎጃም እግረኞች ፣የትግሬ ነፍጠኞች ፣የአማራ ስልተኞች ፣ከቦ ያናፋው ፣ይቀላው፣ያንደገድገው ጀመር ፤ ከእንዝርት የቀለለ የጁየ፣ከነብር የፈጠነ ቤጌምድሬ፣ተቋንጣ የደረቀ ትግሬ ጣሊያንን ፈጀው ፡፡አሰጣው፣ዘለሰው፡፡ ሲል የትዮጵያዊያንን ጀግንነት ከንፈሩን በማላቀቅ ፓፓፓ .. ብሎ ሲያደንቅ ለጣሊያንኑ ዕልቂት ከንፈሩን በመምጠጥ ጽጽጽ…የሚል የምፀት ድምፅ ያሰማበትን የቀለም ጠብታ ያረፈበትን ወረቀት አግኝቼ ያነበብከኝ ሲሆን ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ስላሴም ከሁለቱ የተለዬ በማይመስል የብዕር ወላፍን የጣሊያንን በሰሜን የአገራችን ክፍል መርገፍ በተመለከተ ያምበለበለውን ለዚህ ክታብ በተመሳሳይ ማስረጃነት ወስጄዋው ፡፡ከሁሉ የተለየው ግን እንቅልፍ የሚያንጎላጀው የጣሊያን ወታደር የሚተኩሰው የመድፍ አረር በሰማይ ሲሔድ የተወረወረ ኮኮብ ይመስላል ምድል ካረፈ በኋላ ፈንድቶ ቀለሃው ዋንጫ ያክላል ሲሆነም ሴቶች ለዉሃ መቅጃነት ሲሚጠቀሙት ቀለሃዉን ለማንሳት ሲሔዱ ሆዱ የገብርኤል ከበሮ መሰሎ ተነፍቶ የተኛዉን የጣሊያን ወታደር የተመለከቱት ወይዛዝርት በየመዝናኛ ቦታ ላይ አዝማሪ አንሶላ ለተጋፋ የከንፈር ወዳጃቸው ከሚሰነዝሩት ስንኞች ዉስጥ ፡፡ አንቺ የፈረንጅ እናት ባላቅም ስምሽ፣ ተንጋሎ ተኝቷል ያ ጀግና ልጅሽ፡፡›› እንደዚህ ዓይነት አባባል በእርግጥም በጦርነት ጀግና በድል ርህሩህ የሆነ ህዝብ ቅንጣት ታክል ደማቸው በደሜ ዉስጥ መኖሩ አንዳንዴም በአበሻ(አበሳ፣ድብልቅ) ልጅነቴ ጉራት ቢጤ ሸንቆጥ ታረገኝና የበዛው ኢ-አበሻዊነቴን ይረብሸዋል፡፡ የአድዋ ጦርነት ላይ በወቅቱ ለምኒልክ ከገቡት( ከገበሩት) ግዛቶች ብቻ ወደ 105,000 ጦረኞች የተሳተፉ ሲሆን ከጣሊያን በኩል የቀኝ ግዛቱ ጦረኞችን ሳይጨምር 17,000 ጦረኞች ሲሆኑ ምንም እንኳን የቁጥር ብልጫ ቢኖርም ያሸነፈው ግን የአልደፈር ባይነት ወኔ እንጂ ቁጥር አልነበረም ፡፡ በዚህ ጦርነት በትጥቅ ረገድ የጣሊያኖቹ ዘመናዊ ሲሆን የኢትዮጵያ ግን ባህራዊና በፈረሰኞች የታገዘ ጎራዴ እንዲሁም ጦር ጋሻና ቀስት ይበዛዋል ፡፡ ጣሊያን ግን በመድፍ ደረጃ 56 መድፎችን ያቀረቡ ሲሆን መድፎቹ ግን ገና አንድ ጥይት እንደተኮሱ በኢትዮጵያ ጀግኖች ሁሉም ጀነራሎችን ጨምሮ እንደተማረኩ ከጦርነቱ የተረፈው ጄኔራል ባራቲየሪ ይቅርታ ለምኖ አገሩ ከገባ በኋላ ለምርኮንነታቸው ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጧል ፡፡ ከአድዋ ድል ማግስት ግንቦት 3 ቀን 1888 ዓ/ም አፄ ምኒልክ የፈለሙትን ግዳይ ይዘው ወደ አዲስ አበባ ከድል አድራጊው ሠራዊታቸው ጋር እብስ ያሉ ሲሆን የሸከፉት ምርኮኞች የሆኑት የጣሊያን ወታደሮች ግን ከንጉስ ጦና እና ከቼኒቶ ጋሊቶ ጋር አፄ ምኒልክ ባደረኩት ጦርነቶች ምክንያት ያጋዙትን ምርኮኞች ያህል የጣሊያኖቹ ደህና ዋጋ ያወጡላቸው አልነበረም ማለትም በምንም የሚለውጣቸው አልተገኘም ይልቁኑም እህል ፈጅ ሆነዉም ነበር ፡፡ የኢትዮ-ጣሊያን ጦርነት ለኃያሉ የአውሮፓው ሮም መንግስት የ200 ሚሊዮን ሊሬ የቁስ ግምትና ለከፍተኛ የሰበዓዊ ኪሳራ የዳረገ ቢሆንም ለአፍሪካዊቷ ኢትዮጵያ ደግሞ በተቃራኒው በዓለም ሁሉ ተደራሽ የሆኑ ጋዜጦች ላይ በመጀመሪያው ገጻቸው ላይ የአፄ ምኒልክና የእቴጌ ጣይቱ ቡጡል ፎቶ ግራፎችን በማውጣቱ የተነሳ በጣሊያን መንግስት ላይ ከደረሰበት ቁሳዊና ሰበዓዊ ኪሳራ በተጨማሪ ከፍተኛ የሞራል መንኮታኮትን ጨምሮበታል፡፡በዚህ ምክንያት የአደዋ ጦርነት ላይ ጣሊያንን ድል የተቀዳጀችው ባለቤት ማንነትንና በተለይም ታላቁ ጥቁር ሰው የተባለለትን ምኒልክ ከዘመናዊ የዓለም ካርታ ላይ ለመፈለግ የማንበቢያ መነጽሩን ያላስተካከለ ፊደል የቆጠረ የዓለም ፍጡር አላነበረም ለማለት ያስደፍል፡፡ሆኖም ጦርነቱ ኢትዮጵያን በዘመናዊ የዓለም ካርታ ላይ ስሟን ያካተተ እና ኢትዮጵያ ከተዘጋችበት ዋሻ አውጥቶ ሥሟ ፀሐይ ባየው አገር ሁሉ በአደባባይ ያወጣ ታላቅ ድል ቢሆንም ለፀሀይ መሰጣቷ ግን ገበናዋንም ፍንትው አድርጎ ጸሐይ አስሞቃት ፡፡ ዓይኖች ሁሉ ያረፈባት ኢትዮጵያ ዳር ድንበሯ በወጉ ያልተሰመረ እና የግዛቷ ወሰን ያልተከበረ በመሆኑ ኢትዮጵያን የሚያዋስኑ ሌሎች የቀኝ ገዥዎች እኛ ጋ አልፋ ትገባለች በሚል ስጋት የጥቁሩን ብልህነት ፣ቆራጥነት እና ርህራሔ የተሞላበት አመራር አይቶና ሰምቶ ልቡ ያልደነገጠ ቀኝ ገዢ አላነበረም ፡፡የኢትዮጵያ የግዛት ወሰን አለመሰመር አፄ ምኒልክን ያሳሰበው ዛሬ ሳይሆን ከአድዋ ጦርነትም ቀደም ብሎ ቢሆንም ቅሉ እርሳስና ማስመሪያ ይዞ ለማስመር ግን ትክክለኛ ጊዜ ላይ መሆኑን የአድዋ ጀግኖችም ተስማምተውበታል ፡፡ የነጮቹን የመስፋፋ ህልም በአደዋ ሜዳ ጀግኖች ቅጅት ከማድረጋቸው ፊት የኢንዱስትሪ አብዮት ( በ1789- ጀምሮ እ.አ.አ) ባስከተለው ለውጥ ምክንያት የአውሮፓ ቀኝ ገዥዎች ጥሬ ሀብትና ርካሽ የሰው ጉልበትና የገበያ ቦታ ለማግኘት አፍሪካን ለመቀራመት እርስ በእርሳቸው ለሚያደርጉት ሽሚያ እንኳን ሌሎቹ ቀርቶ ጠንከራ የአስተዳደር መዋቅር የነበረው የሸዋው መንግስትም እንኳን እንደማይተርፍ የተረዱት ብልሁ ሰው የማሰባሰብ ሥራ ላይ ተጠምደው ሳሉ ነው የኢጣሊያና የኢትዮጵያ ጦርነት የምኒልክን አገርን አንድ አደርጎ የማጠናከር ዘመቻን ለሁለት ዓመታት ጊዜ እንዲቋረጥ ቢያስችልም በዐደዋ ደል የተሸመተው ተሞክሮ ግን እንኳን አስከ ነጫ አባና ሩዶልፍ ሐይቅ ይቅርና የምኒልክ ወታደሮች አስከ ቀይባህርና ህንድ ወቂያኖስ ቢገሰግሱም የሚያገኛቸው ምንኛዉም ምድራዊ ኃይል (ሰው) የዘንባባ ዝንጣፊ እያነጠፈላቸው ሆሳዕና ከማለት ዉጭ አማራጩን የጣሊያን መንግስት እኔን ያየ ይቀጣ ብላም ነበር ፡፡ ጃንሆይ ተሸናፊዉን ጣሊያን ከኤርትራ ያላስለቀቁትና ከመረብ ምላሽ ወንዱ ባት የለው ሴቷ ጡት የላትም ብለው ያስቀሩት ሁለቱ ትግረኛ ተናጋሪዎች የሆኑት ባህረ ነጋሽና የዮሓንስ 4ኛ ግዛት ሰዎች ካበሩ ኃይል ስለሚያገኙ ለመንግስቱ አደጋ ስለሚሆን ሚሊዮኖች ቢሆኑም ለዙፋን የማያሰጉት ግዛቶች አዘነበሉ ፡፡ ምኒልክ የመንግስቱን ግዛት ወደ ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ ማስፋፈቱ ቀጠለ ፡፡ወደ ደቡብ ምዕራብ እና ሌሎችም ያገቡት አውራጃዎች እንዲዘልቁ ያስገደዳቸው ምክንያቶች በርካቶች ናቸው ቢባልም የዘውዱ ስጋትን የሚስሰተካከለው ምክንያት የለም ፡፡ ምኒልክ የኦሞና የአባይ ተፋሰስ የሚያልፍባቸውን ለም መሬቶች ለጠላት አሳፎ ለመሰጠት ቀርቶ በአቁማዳ አፈር እንኳን አልሰጥም የሚል ፅኑ አቋሙ እና ጣሊያን ስለኢትጵያ ለዓለም ባስተላለፈችው መልዕክት ኢትዮጵያን ለመውረር ቀርቶ እሷ(ኢትዮጵያ) ትወረናለች የሚል ስጋት በዓለም ናኝቷል ወደ ደቡብ ምእራብም መቸኮሉ ለዙፋን፡፡ ዘመኑም የዓለም ጎበዛዝት ከንጉሱ ጎራዴ ከመሰየፍ ሸሽተዋል በአንፃሩ ከምኒልክ ጋር የተሸለ ወዳጅነት የነበረው የፈረንሳይ መንግስት በሸንበል ማርሻንድ የሚመራው የፈረንሳይ ክፍለ ጦር ከሴኔጋል ተነስቶ ወደ አባይ የላኛው ክፍል በመገስገስ ላይ እያለ ነጭ አበይ ላይ በሚገኘው የፋሾዳ ምሽግ ላይ ከደጃች ተሰማ ናደው ጋር እንዲገናኙና የወሰን ምልክት እንዲያኖሩ ቢመከርም የፈረንሳዩ ጋቡን ከሚባለው የባህር ጠረፍ ተነስቶ መካከለኛ አፍሪካን በማቋረጥ አስኪደርስ ድረስ የኢሉባቡሩ ደጃች ተሰማ ናደው ሰራዊት ቀድሞ ትልዕኮውን አጠናቆ ከተመለሰ ከወር በኋላ ደርሶ ከኢትዮጵያ የተረፈውን አካሎ የሔደውን መመልክት በቂ ነው ፡፡ አፄ ምኒልክ ከአደዋ ድል በኋላ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ያዘመተውና አውረጃዎችን የማቅናት በእርስ በርስ ጦርነቶች የተበታተኑትን አውራጃዎች መልሶ አንድ ለማድረግ ርስት የማስመለስ ዘመቻ መሆኑን ማሳያው በጋሞ ፣ በከፋ፣ በማጂ( ኪያፊ) እና በሌሎችም ስፍራዎች የተገኙት የጥንት የብራና ሌሎችም ታቦታትና ተለያዩ የታሪክና የሐይማት መፅሐፍቶችና ቅርሶች በአውራጃዎቹ በመካከለኛው ዘመን ከአቢሲኒያ ጋር ግንኑነትና ትውውቅ ያላቸውና እንደነበረ ማሳያ ነው ቢባልም ከባህረ ነጋሽ (ኤርትራ) ይልቅ ለኢትዮጵያ ቅርብ ርስት አልነበሩም ርስት ለማቅናት ብቻ አይደለም በሰው ደምና አጥንት ዘውዱን ለማጠንከር የተሸለው ከላይኛው ይልቅ ታችኛው በመሆኑም ጭምር ነው ፡፡ ምኒልክ አዲስ አገር ያቀኑ ሳይሆን ያሰባሰቡ ናቸው በሚለው ላይ እኔም ብዕሬኝ ላርመስምስ እና የዘመቻዉን ሙጃም ላውንሳ ፡፡ ኢጥዮጵያን ለማሰባሰብ ቢባልም ባህረ ነጋሽም የአበሻ አገር ሲሆን ጎልሲያ የአበሻ ጠረፍ ነው ጫፉ የካፋ ግዛት ነው እሱም አስከ ጊዲና ሻፓ ተራሮቸረ ደቡባዊ ክፍል ድረስ ይዘረጋል ፡፡ ጎልዲያ ከአበሻ ግዛት ዳር ነው ፡፡ በዚህ የአበሻ ጫፍ ድንበር ላይ ከካፋ ጋር የጫራ ፣ናኦ ፣ኩሻ፣ ጊሚራና ‹‹ሽሮ ፣ቲሻና፣ መኤን ›› የሚባሉ ነገዶች (ብሔረሰቦች ) በከፋ ክ/አገር ዉስጥ ጎባ ጫራ ተብሎ በሚጣራ አከባቢ ከጥንትም በቀበሌዎች ተደራጅተው ይኖራሉ ፡፡ ካፋ በአባይና በኦሞ መካከል ባለው ሰፊ አገር ዉስጥ ከሚገኙት ጎላ ጎላ ካሉት ትንንሽ መንግስታት መካከል በአንፃራዊነት ነፃነቱን በራሱ ሲጠብቅ የቆዬ እንደ ትግሬ ፣ጎንደር፣ሸዋና ወላይታ የንጉስ አገር ሲሆን ታዋቂ ንጉሰ ነገስታዊ መንግስት ያለው የጅማን ፣ የእናሪያን(የሊሙ )፣የኮንታንና የኩሎን ንጉሳዊ መንግስታትን ያቀፈ በአበሻ ታሪክ ዉስጥ ጎልቶ የሚታወቅ እና የአበሻ( ኢትዮጵያ) ጠረፍ የሆነ ማህበረሰቡ በእርሻ ፣በዉጊያና በእደ ጥበብ የተራቀቀ የመጨረሻው 18ኛ የሆነው አስረኛ ንጉሱ አድዮ(ታቶ) ጋል ሻርቾ የነበሩ እሱም ጋልቶ የተባለ ሲሆን የሽሮ ማህበረሰብ በንጉስ የሚተጋገር ሳይሆን በጎሳ መሪዎች የሚመራ በማጂ ፣ በደቡም ኦሞ ፣ በጉረፈርዳ በአውራጃዎች ተደራጅቶ ከሚኖሩት በተጨማሪ አዚህ የከፋ መንግስት ስር በቀበሌዎች ደረጃ የሚገን ሲሆን በኋላ በምንልክ አስከተደራጀ ድረስ በከፋ ንጉስ ያልተገዛ ነው ፡፡ ለኢትዮጵያ ( አበሻም) አልገበረም ፡፡ የትላንት ሹሮ(ቲሻና) :: የዛሬ መኤን ??? ሹሮዎች ለከፋዎች ቅርብ ስለሆኑ ‹‹ ሽሮ ›› ማለት ጥቁሮች ብለው የሚጠሯቸው ጎሳዎች ቢሆኑም እነዚህ ጎሳዎች ራሳቸውን እንዲህ ብለው የማይጠሩ ቢሆንም ለሁሉም አጠቃላይ የሆነ ስም ግን ለማግኘት እቻልኩም ›› በአፄ ምኒልክ ጦር በተለይም ከራስ ወልደ ጊዮርጊስ ጋር የዘመተው የሩሲያው ተወላጅና የጦር ኃኪምና የራስ አማካሪ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው አሌክሳንደር ቡላቶቪች፣ከምኒልክ ወታደር ጋር ትርጉም በዶ/ር አምባቸው ከበደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ 2007 ዓ/ም ፡፡አንድ ልጅ ሲወለድ ስም ለራሱ አያወጣም ለተወለደው ልጅ ስም የሚያወጡለት ወላጆቹ ወይም ቤተ ዘመዶቹ ናቸው፡፡ ልጁ ስሙን ከወደደው ዕድሜ ልኩን ይጠራበታል ፡፡ ካወደደው ደግሞ እንዳይጠራበት ይከላከላል፡፡ ሹሮ የሚለው ስም በከፈኛ የሁሉም ጥቁር ሕዝቦች መጠሪያ ሊሆን ይችላል ፡፡ አፍሪካ ጥቁር ህዝብ ስለሆነ ከፋም ጥቁር ነው ማለት ነው ፡፡ በመሆኑም ከፋም ሹሮ ይሰና ማት ነው ፡፡ ሹሮ የሚለው ሰስሰም ተለየ ክፋት ያለው ስም ባይሆንም ራሳቸው ሰየጥቁር ሕዝቦች የሆኑት ከፋዎች ሥሙን ለመኤን ሕዝብ የተጠቀሙበት መንፈስ ችግር ስላለበት ሹሮ ለተባለው እና አሌክሳንደር ቡላቶቪች አጠቃላይ የሆነ ስም አላገኘውም ላለው ህዝብ ግብር የሚመጥን ሥም ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ሰዎች የታዘቡትን ይጨምራል፡፡ ‹‹ የቲሻና ሕዝብ ደመ ቁጡና ጠላቱን ተበቃይ ወዳጁን አክባሪ ቀልጣፋና ንቁዎች የተፈጥሮ ወታደርነት ያላቸው ናቸው ›› ሲል ቲሻናን (ሹሮን ) ሲያስተዳደር የነበረው ሌተናል ኮ/ል ከበደ ተሰማ አዲስ አበባ ላይ በ1952 ዓ/ም ባሳተመው ማጂ ጎልዲያ ዉበት መድብላቸው ላይ ምስክርነቱን ሰጧል፡፡ ከሹሮዎች ጋር ታግዬ ነው ያደኩኝ ግን አላሸነፍኳቸውም ሲል ከባቹማ አስከ ቨርጂኒያ በሚለው የሕይወት ጉዞ ግለ ታሪክ ላይ ምስክርነቱን ያስቀመጠው አቶ አሰፋ አደፍርስ ‹‹ የሹሮ በህል የወንድነት ፣የጀግንነት እና የቆራጥነት ባህልን የሚመጥን እንጂ ‹‹ ምን እሆን ይሆን›› በሚል የመጠራጠር ስሜትን የሚያስተናግድ አይደለም … የቆራትነት ልምደ በአደኩበት የሹሮ ባህል ዋነኛው ተግባር ስለነበረ በሕይወት ዘመኔ ምንም ፍርሃት የሚባል ጉዳይ በአዕምሮዬ አልነበረም አውሮፕላን ተጠልፎ ‹ እጅ ወደ ላይ › ሲባል እጁን ወደላይ ያላነሳ በሰማይ ላይ የነበረ ሰው ብኖር እኔ የሹሮ ጀግንነት የተጣባኝ አቶ አሰፋ አደፍርስ ብቻ ነበርኩኝ ›› ሲል የመኤን ብሔረሰብ እጅ የመይሰጥና እጅ ወደ ላይ ወይም ድንጋይ በትከሻን የማይለምዱ መሆናቸውን በመፀሐፋቸውና በኋላ በኢሳት ቴሌቪዝን ቀርበው ስለ ሹሮ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጠዋል፡፡ አሁንም ህያው ስለሆኑ ከሳቸው መረዳት ያቻላል፡፡ የጎጃሙ ባላባት ተክለ ሐይማኖት ግዛትህ ላይ ከፋ ተጨምሮልሃል ተብሎ በጃንሆይ ‹‹ የከፋ ንጉስ›› በተሰኙ ጊዜ ነው ከፋን የማስገበር ዘመቻ ለማካሔድ በ1880 ዓ/ም ተንቀሳቀሶ የንጉስ ጋኪን አቅም ለመፈተሸ የዋተተው በበሽታ ማቅቆ የተመለሰው የጎጃሙ ተክለ ሐይማኖት ሲሆን በራስ ደረስ ሽፈራው በተመራ የጎጃም ጦር ታጅቦ ነው ፡፡ ተክለ ሐይማኖት ወደ ካፋ በዘመተበት ወቅት ለጎጃሞቹ ባላባቶች ፈታኝ የሆነ ርሀብ እየገነገነ በመጣበት ወቅት ነው ፡፡ በዚህ ምክንያት ወደ ከፋ የዘመተው ዘማች ባሪያ ለማስፈንገል አስቦ ከተሰለፈው ነፍጥ አንጋች ይልቅ በእራብ የታጠፈውን አንጀት የሚሞላ እህል መያዢያ ስልቻውን በጀርባው አቁፋዳውን በብብቱ ሸክፎ የምርኮ ቃርሚያ እህል ለመሰብሰብ አሰፍስፎ የመጣው ጀሌው ይበዛ ነበር ፡፡ ይህ ዘመቻ ከግዛት ማስፋፋት ይልቅ ጎጃምና ሸዋ ላይ ለተከሰተው ረሃብ ተ/ሐይማኖት ግዳዩን እህልና የእርሻ ከብት ለመበዝበዝ የታለመ መሆኑን መሰረቱ ኦሮሞ የነበረው አለቃ ተክለ እየሡስ ዋቅጅራ አልሸሸጉንም፡፡ ተክለ ሐይማኖት ከጎጃም ከመነሳቱ በፊት የዲማው ጊዮርጊስ እንዲከተለው አስቦ የታጠቀውንም ሰይፉ በዉሃ ላይ ሲደግሙ ዉሃ ቱግ አድርገው በሚያፈሉ የእምነት አባቶች በሆኑት እነ መምሬ ተርፌ፣አባ ወ/ጊዮርጊስ ፣ አለቃ ተጠምቶ፣አለቃ ለማ አስባርኮና ጊዮርጊስንም የተለማመነ ሲሆን ፡፡ የዋቆ ፈና እምነት ተከታይ ራስ ጎበና ዳጪም የፈረሱ ግንባር ላይ ደም ቀብቶና ለዋቆ አሳብቆም ይመስለኛ ፡፡ ተክለ ሐይማት ከፋን ወግቶ በአገሩ ጎጃም እርጥባን አግኝቶ ጎጃም ህዝብ ለማባላትና መሬቱንም ለማረስ ላለመው ህልም ተግባራዊነት በመንገዱ ጊዮርጊስ ብቻ ሳይሆን አባ ሌጣ የተባሉ የኦሮሞ ተወላጅና መንገድ አዋቂ ሰው ከፊት ለፊት ነበሩ ፡፡ በአባ ሌጣ መሪነት ጅማ የደረሱት ባላበቱ የጅማው አባጂፋር ቀድሞ ለጃንሆይ ገብቶ ስለነበር ደግሶ ተቀብሏቸውና ወደ ካፋ ሸኟቸውም ፡፡ ምክንያቱም በኦሮሞ ዉስጥ ነጉስ ሳይሆን አባገዳነት ስለሚታወቅ ከአባጅፋር ይልቅ የጎጃሙ ተክለ ሐይማኖትን ምኒልክ ‹‹ የከፋ ንጉስ›› በማለት ከጅማ ይልቅ በንግስና ወደሚያምነው የከፋ ሕዝብ ልኮትም ስለነበረ ነው ፡፡ተክለ ሐይማኖት በኦሮሞቹ አባ ዱላዎች በሆኑት እነ ኢብሳ ገርባ፣ የተባሉ ጀግኖች የተነሳባቸውን ተግዳድሮት በብልጠት አልፈው ተክለ ሐይማኖትና ጎበና ዳጪ የከፋ ዳርቻ የሆነውን የጎጀብን ወንዝ አስከሚሻገር ድረስ በጎማና በጌራ ምድር ሁሉ አባ ቆሮው ( ለነገሩ አባ ራጎ፣ ዮባ ቦጊቦ ፣አባ ሬሱ ፣ አባ ሞርኪ) የተባሉት የጎማ ስርወ መንግስታት ወደ ኦሮሞነት የተቀየሩ ከፋዎች ነበሩ በእነዚህ ድግስ እየተደገሰ መንገድ እየተመሩ የከፋ ግዛት በሆነው በተለምዶ የአበሻ ጠረፍ ነው የሚባለው ወደ ኮንታ፣ኩሎ ፣ጊሚራ፣ ኩሻ ( ሼ/ጊሚራ) እና ጫራ መሬት ደርሰውዋል ፡፡ በጉዞአቸው መንገዱ በጫካ ፣በቀርቀሃ፣ በእንሰት፣በኮርችና ደኑ ሰማይ አያሳይም ነበር ፡፡ ሆኖም ግን ርሃብ የሚባል ነገር በማይታወቅበት በዚህ አገር ሰራዊቱ ምንም ሳይሆን ወደ ዉስጥ ዘልቆ መግባቱ ተክለ ሐይማትን አስገረመው ፡፡ በከፈኛ ቋንቋ አዋቂዎቹ አባ ሌጣ እና አባ ቆሮው መሬነት ከፋ የገባው ነፍጠኞች ‹‹ የከፋ ንጉስ መጣ ›› እያሉ በየቦታው አዋጅ በማስነገር የከፋውን ንጉስ ጭንቶ ወደ ጫካ ገብቶ ባይገኝም በእዚህ አገር የተገኙ ሕዝቦች ፍሪዳዉን፣ ማሩንና ቅቤውን ተሸክሞ‹‹ ወኪሶ ወክሳ›› እያለ እየዘፈነ ወደ ንጉስ ተክለ ሐይማኖት እንደገባ አሁንም ተክለ እየሱስ ዋቅጅራ ( አለቃ ) አስነብበውናል ፡፡ በንጉስ የሚምነው የከፋ ሕዝብ ለንጉሱ መግባት ባያስገርምም ንጉስ ነው የተባለው ተክለ ሐይማኖት ለጦሩ አበጋዝ ራስ ደረስ ሽፈራው ትዕዛዝ በማስተላለፍ በንጉስ ወደማያምኑት እና በጎሳ መሪ ባቻ ወደሚያምኑት ጫራ ጎባ እና ጎልዲያ እንዲዘምት ያደረገው እንደ ከበርቴ ዘላን እንዲያፍጫጭበት ሳያስብ አልቀረም ፡፡ ለዚህም ይመስላል የኩሎው ፣የኮንታው፣ የገሚራው ፣የኩሻው ራስ ደርሶ (ራስ ደረሰ ሽፈራው)፣ ተብሎም ተሞሽሮበታል ፡፡ በጎባ- ጫራ ያሉትን ጫራ ፣ናኦ ፣ጊሚራና ‹‹ሽሮ ›› የሚባሉ ነገዶች (ብሔረሰቦችን) ዱባ ሳይቀር ሁሉንም እንዲሁም የሹሮ ማሽላን ከማሳውና ከጎተራ ወቅተው በስልቻቸው አድርገው አግዘዋል ከብቱንም ዘርፈዋል፡፡ከሰውም በኋላም ጎጃም ከገባ በኋላ ክርሰትና ተነስቶ ገብረ ማርያም በሚል የክርስትና ስም የተጠራ የ11 ዓመት የሹሮ ህፃን ልጅ ከብት ከሚያግድበት መስክ ላይ ማርከው ወደ ጎጃም እድርሰዋል ፡፡ ቢርቢርሳ ዋቅጅራ ሊሰኝ የሚገባውን ክርስትና አንስተው ቅኔ አዘርፈው ተክለ እየሱስ የሚል የክርስትና ስም ሸልመዉት ተክለ እየሱስ ዋቅጅራ ( አለቃ ) የተባለው ጎጃሜዎች ምናልባትም በመኤን አሰያየም ጎሮጌ የተባለውን ህፃን ወስደው ካጠመቁት በኋላ ገ/ማሪያም ሚል የክርስትና ሥም የሰጡት ገብሩ ይዘው እስከ ጎልዲያ ለመግፋት ያሰበው ቡድን ከፋ ላይ የቀረው የጎጃሙ ተክለ ሐይማኖትም አስከ ሞት ድረስ በሚያደርስ ሕመም ተጠቅተው ሲጠመቁ ጋኔኑ አባ ኪሮስ ያቆራኙኝ ጋኔን ነኝ ስላለ ፡፡ አባ ኪሮስ ሲመረመር አፄ ምኒልክ አንድ ወቅት ታማኝ አድርገው ለጎጃም የሾሙት ራስ በዛብህ ተ/ሐይማኖት አድርግልኝ ብሎ ነው ብሎ ስላለ ባቻ አባ ኪሮስ ለሹሮዎች በተዘጋጀው ሰይፍ ስለት ይግባኝ በሌለው ፍርድ ተሰይፎ ከፋ(አንድራቻ) ላይ ተቀበረ ፡፡ ተክለ ሐይማኖት በጦር አበጋዙ በሆነው ራስ ደረሰ ሽፈራው አማካኝት የተማረከው የብሔሩ ተወላጅ የሆነው ገብረማሪያም/ገብሩ/ ከዴቻ (ጫራ ጎባ ) እንደተወሰደ አዕምሮ ስሉ ገብሩ አፉን የፈታበት የመኤን ቋንቋ ጭምር አማረኛን ለመልመድ ወራት ስላላስፈለገው በአማረኛ ቅላፄው ድምፀ መርዋነቱ ተመሰከረለት ፡፡ ገብሩ በዚህ ለጋነት ዕድሜው ለጎጃሙ ዲማ ጊዮርጊስ ሳይሰጥ አልቀር በቤተክርስቲያን የትምህርት ደረጃና ሥርዓት መሰረት መዝሙረ ዳዊትን ፣ዉዳሴ ማርያምን፣ በጣም ፈታኝ ነው የሚባልለት የድጓን ትምህርት እና ሌሎችን በወቅቱ የማይታለፉ እንደነ መስተጋብዕ ፣ዓርባአት፣ክስተት፣አርያም፣ሠለስት፣የተባሉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነገረ መለኮት መፅሐፍት(ትም/ቶች) ጠንቅቆ ያወቀና የቀሰሰ ይመስላል አድጎና ጎልብቶ ለሁለተኛው ዙር ደርሶ በ1898 ዓ/ም የሹሮን ቋንቋ እየተረጎመ የአበሻ ጠረፍ የተባለው ጎልዲያ ላይ ሲደርስ አብሮት የተጓዘው ሩሲያዊው ኃኪም አሌክሳንደር ቡላቶቪች የተባለው በመጸሐፉ ገጽ ‹‹ የአበሻ ጠረፍ የሆነውን የሹሮን ወሰን አልፎ አልፎ ለመግባት ተወስኖ ነበር በቤንችና በሹሮዎች አገር መካከል ያለውን ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ አቋርጠው የሚያልፉ መንገዶች በጣም ጠባብና አስቸጋሪ በመሆኑ ጫካዉን እየመነጠሩ ሰፊ መንገድ የሚያወጡ ሰራተኞች በአስቸኳይ ከጦሩ ምልመላ እንዲሔዱ ከራስ ወ/ጊዮርጊስ ስለታዘዘ መቶ ሰዎች ተመደቡ ….አክለውም፡-ሹሮዎች ምን እንደሚጠብቃቸው ያውቃሉ አስቀድመው በጎረቤቶቻቸው በሆኑት ቤንቾች አማካኝነት እንዲገቡ( እንዲገብሩ) በመደጋገም መልዕክት ተልከውባቸው ስለነበረ ሹሮዎቹ ግን አበሾች ወደ ደንበራቸው እንደሚገቡ በማሰብ መግቢያ መንገዶችን በሙሉ ጦርና ጋሻ በያዙ ጀግኖች ዘግተው ጠረፋቸውን በጥንቃቄ ይጠብቁና መንገዱንም በዓይነቁራኛ ይከታተሉ እንነበርና ጅብ ያለበት ጫካ ዉስጥ ጥቋቁር ሰዎች ዉልብ ዉልብ ይሉ እንደነበርም በገጽ 95 አሳሹ ሩሲያዊው ጠቅሷል ፡፡የአደጋው ነጎድጓድ ማስገምገም ጀምሮም ቢሆን ሹሮዎቹ የተለመደ ተግባራቸውን መቀጠላቸውን ምን ይባላል? ልበ ሙሉዎች ካልሆኑ በቀር ሲል ሩሲያዊው ይጠይቃል ይመልሳል ፡፡ መልሱም ጀግንነት መሆኑን በዛው መጸሐፍ 131 ላይ ሲትርክ እንዲህ አለ ‹‹ አስር ሰዓት ላይ ወደ ሰፈራችን ተመለስን እንደተለመደው ብዙ ቁስለኞችና በሽተኖች ይጠብቁን የነበረ ሲሆን ከእነሱ መካከል በሹሮ ጦር ተወግተው በጣም የተጎዱና በቃሬዛ የመጡ ወታደሮች ነበሩ ፡፡…ሹሮዎቹ አድፍጠው ካጠቋቸው ዉስጥ ጦር በጀራባቸው ገብቶ ከዕንብርት አጠገብ ሆዱን ቦትርፎት የወጣ ቁስለኛ ያለ ሲሆን ቁስለኛው ወታደር ነፍሱን ለማዳን ነፍሱን ሳይሰስት ጦሩን መንጭቆ አውጥቶ ጓደኞቹ አስኪደርሱለት እያቃሰተ ሲከላከል ቆይቶ ቁስሉ በጣም ሰፊ ስለነበር አንጀቱ ተዘርግፎ በመኤን ምድር የሞተ ወታደር ብዙ ነው ›› ሲል ዘግቧል ፡፡ በራስ ወልደጊዮርጊስ የተማረኩ ጊሚሮች ( ቤንቾች) የሹሮን ወሰን ሲደርሱ ጉቶ ለመቁረጥ በቅድሚያ መጥረቢያ የጨበጡ መሆናቸውን አሌክሳንደር ቡላቶቪች የየካቲት 9ቀን 1898 ዓ/ም ክስተት ሲቃኝ አሳዉቆኛል ፡፡ በዚህ ዘመቻ ወቅት ከከፋ ደቡባዊ አቅጣጫ የሹሮ መሬት ከሚያዋስነው ከኩካ ወንዝ ማዶ ያለው አውራጃ ገዥ ዎታ-ራሻ የተባለ የኩሻ ባላባት በዘመቻው የተሳተፉ መደበኛ የራስ ወ/ጊዮርስ ጦር የሆነው በቁጥር ሰላሳ ሺ የሆኑት 1ኛ .ፊታውራሪ አትርሴ ጦር በቁጥር1000 ( ከቁጫ)፣2ኛ የፊታውራሪ የፊታውራሪ ገረማሪያም ጦር 800 (ከኮንታ)፣ 3ኛ ታውራሪ ጨቡዴ ጦር 800 (ከኮንታ)፣4ኛ ፊታውራሪ ዉቤ ጦር 600 ( ከጎፋ) ፣5ኛ የፊታውራሪ ኢማም ጦር በቁጥር 2000 (ከሜል እና ዲሜ )፣6ኛ የፊታውራሪ ዳምጤ ጦር በቁጥር 1000 ( ከባኮ፣ሻንጋማ እና አሪ ) ፣7ኛ የቀኛዝማች ዱቤ ጦር በቁጥር 500 ( ከኩሎ ) ፣8ኛ የቀኛዝማች አለምነህ ጦር በቁጥር 500 ( ከኩሎ)፣9ኛ የደጅ አዝማች እነዳርጌ ጦር በቁጥር 800( ከኩሎ)፣10ኛ የግራአዝማች ዘመድነህ ጦር በቁጥር 600 ( ከኩሎ ) ፣11ኛ ቀኛዝማች ወልደትንሳኤ ጦር በቁጥር 600( ከሊሙ)፣ 12ኛ ዘበኞች የራስ ወ/ጊዮርጊስ አንጋቾች በቁጥር 500 እና ሌሎችንም ስንቅና ትጥቅ( ሚስቶችንና ልጆችን ) የያዙ ጨምሮ ፣ቀዳሽና መዘመምራንን ሁሉ ደግሰው ያበሉና ያጠጡ ሲሆን ለዘመቻዉም 13ኛ . ተራ ቁጥር ላይ በፊታውራሪ ፋሪስ የሚመራ 800 ጦር ሠራዊትን የኩሻው ባላባት (ዎታ- ራሾ(ራሻ)) አበርክቶት አለው ፡፡የኩሻውና በፊታውራሪ ፋሪስ የሚመራው ጦር በዚህ ዘመቻ ግዳይ ሳይተልም አልቀረም በታሪክ እንደተረዳዉት በጦርነቱ ‹‹ ሉቡንኢት ›› ወይም በቀን የሚያንቀላፉ (Day dreamer ) የሆኑ የሹሮ ብሔረሰብ ተወላጆች በጦርነቱ የተማረኩ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ዛሬም ድረስ የአባታቸው አባት(አያቶቻቸው) የካፋዎቹ ከፍለ ግዛቶች (ዎራፊ ሻዎ) ገዥዎች የሆነው …-ራሾ(ራሻ) በሚል ስም የሚጠሩ በመኤን ብሔረሰብ ተወላጆች ዘንድ መገኘቱ ነው፡፡ በዚህ የክብር ሥም መጠራቱ ባይከፋም አያቱ ካንቀላፋበት ቦታ ላይ እጅ ወደ ላይ አንሳ ከተባሉበት ጊዜ ጀምሮ የልጅ ልጃቸው እጃቸውን ባለማስውረዱ የተነሳ ዛሬም ምርኮኛነቱ መቀጠሉ ግን የታሪክ አተላ ማትረፍ ሲሆን የጀግናውን ሕዝብ(ብሔረሰብ ) አንገት አስደፍቷል ፡፡ የምኒልክ አማሮች የአበሻ ጠረፍ የሖነው የመሔን ድንበር ላይ ሲደርሱ በቤንቾች መጥረቢያ በተጠረገ መንገድ፤በእነ ዎታ-ራሻ በተሰነቀ አገልግል የተቋጠረ ስንቅና የራስ ደረሰ ሽፈራው ክርስትና ልጅ የሆነው የብሔሩ ተወላጅ ገብረማርያም(ገብሩ) በአብሾ ናላቸውን ባዞሩ የጎጃም ቄሶች ‹‹ ከጋላና ከሻንቅላ የተጋባ ገሃነም ይወርዳል ›› የሚለውን የራዕየ ማርያም ክታብ ላይ በተመሰረተ የጥላቻ ወንጌል እሱም ጦዞ ቡላቶቪች እንደተረከው ‹‹ ገብሩ(ገብረማሪያም) የአማሮች ልማድና ባህል በደንብ የተዋሃደው በመሆኑ የአገሩን ሰዎች (ሹሮዎቹን) እንደ አረመኔ ይቆጥራቸው ይገልፅም ነበር ፡፡ ›› (ገጽ 113 ላይ ይመለከተዋል) ፡፡ሲል እትብቱ ከተቆረጠበት እጁን ወደ ላይ አድር አስከተማከበት ድረስ ለ11 ዓመት ብቻ ያውቅ የነበረውን የሹሮ ሕዝብ በአረመኔነት የሚወተውተው ገብሩ ምናልባት ሹሮዎች በተ/ሐይማኖች ወታደሮች ላይ አረመኒያዊ ድርጊት ሲፈጽሙ አይቶ የተማረከ ካልሆነ በቀር በዚህ እድሜው ሹሮዎቹ በሆኑት እናትና አባቱ በኩል የደረሰበት ግፍ ግን እንጃ ? የሆነ ሁኖ የምኒልክ አማሮች ገብሩን አምነውት እነዚህ አቢሲኒያዊያን ምንሊክ ከጣሊያን በማረከው ፈረንጅ ደም ለመድ መድፍ እና ከሐረሩ ባላባት መሐመድ አንፍሬ በራስ ወ/ጊርጊስ በማረከው የአበሻን ደም የለመደ መድፍ አረር የመኤን ሰማይ ሥር እየተመዘዙ ረጃጅም ተራሮች በሆኑት በካፊ፣በኤሌኬኒ፣ በጉሚ ፣በጉኝ …ወዘተ ጠርዝን በመያዝ ወደ ሸለቆ መቀመጫና ወደ ወንዝ ዳርቻ ቁልቁል እየወረዱ በልበ ሙሉውና ጀግናው የሹሮ ሕዝብ ላይ አከታትለው ሲያንገበግብ የሹሮዎቹ ጦርና ቀስት መቋቋም ስለዳገተው የሹሮዎቹ ኃይል ተዳክሞ ጀግንነቱን ተሸነፉ እንደ አበሾቹ ሌሎቹ ራስ ወ/ጊርጊስ ድንጋይ - በትከሻ አላሸክሟቸውም በጀግንነት ተዋግተው በጦር መሳሪያ ብልጫ መሸነፋቸውን ራስ አድንቀው ምንልክን ንጉሳችን ነው ብለው እንዲቀበሉ አድርገው አስገበሩ ፡፡ ሹሮዎች ለምኒልክ በራስ ወልደጊዮርጊስ በኩል ከገቡ በኋላ የአደዋ ድል ላይ ከፊት ለፊት ተሰልፎ የተዋጋውና ድል አቀናጅቷል ተብሎ የታሰበው ከጣሊያኖችም ይከፋሉ ተብሎ በተነገረላቸው በሹሮዎች ሰማይ ሥር በአባ ወልደ መድህን ክህነት እየተዘዋወረ አስከሩዶልፍ ሃይቅ የዘለቀው የወ/ጊዮርጊስ ስዕለት አባት የሆነው ቅ/ጊዮርጊስ ታቦት ከሩዶልፍ ሐይቅ ተመልሶ ኦሞ ወንዝ ላይ ከአዞ ጋር ታግሎ አሸንፎ በ1902 ዓ/ም ጎልዲያ (ባቹማ) ላይ ተተክሎ አርንጓዴ ቢጫና ቀይ ባንዲራዉም ከብሮ ሹሮዎቹ በአፄ ምኒልክና በወ/ጊዮርጊስ በጎነት አግንተው በሁለት አውረጃዎች ተደራጅተው እስከ 1967 ዓ/ም ድረስ ከነክብራቸው እና ጀግንታቸው እነፊታውራሪ ጋሊ ፣ ቀኛዝማች ሲቂዮ ጃውቶን በኋላም ፊታውራሪ ወዘተ ተሸመው ሸልመው በቦታቸው መቀጠላቸውና ከአበሻ(አቢሲኒያ) ጋር ተዋህደውና ተጋብተውም ከአበሻም የባሱ ስለመሆናቸው የተመሰከረላቸው ሹሮ/ቲሻና / መኤን ብሔረሰብ ታሪኩን ሳወጋላችው ኩራት ይሰማኛል ፡፡ ሹሮ ብሔረሰብ ምንም እንኳ በጀግንነት ከራስ ወ/ጊዮርጊስ ወታደሮች ጋር ከተዋጋ በኋላ ቢገባም የምኒልክ ወታደር አስከ ገለብ ድረስ በመጓዝ አፄ ምኒልክ በገለብ በኩል ናስማስር (ወጀግራ) ጠብመንጃ ከጋሻ ጋር አድርገው በሲሚንቶ የቀበሩበት የድንበር ምልክት ያኖሩት ዉስጥ እነ ደጃዝማች ካቲላ አብረው ነበሩ ፡፡ አፄዎቹ ከዛሬዎቹ በተሸለ ሁኔታ ለዚህ የመኤን(የሹሮ ) አከባቢ ቀልባቸውን ያልነሱበት አንዱ ማሰያ በኢትዮጵያ ዉስጥ የመጀመሪያ ስልክ የገባው ሐረር ሲሆን ቀጥሎ የገባው አዲስ አበባ ፣ገዳሚና ማጂ ነው ይህ የሚያሳየው አፄዎቹ ይህንን ሕዝብ በኢ-ፍትሐዊ መድፍ የማያደባዩ መሆኑን ነው ፡፡ ለዚህም ጣሊያን 2ኛ ዙር ኢትዮጵያን ሲወር እና ንጉሰ ነገስቱ ሱዳን ላይ በመጡ ጊዜ ከመኤን አከባቢ 3 ወር ሙሉ ተጉዘው ከሱዳን የጦር መሳሪያ ተሸክመው አምጥተው ጣሊያንን በአርበኝነት የወጉ የሹሮ ጎሳ መሪዎችን ከቆያውን ሌላ ጊዜ አሳውቃችዋለው ፡፡ ጣያንን ከአገራችን አስወጣ የተባለችው እንግሊዝ( ብሪታኒያ) ኤርትራንና ኦጋዴንን ከመያዝ በተጨማሪ በገለብ በኩል ናስማስር (ወጀግራ) ጠብመንጃ ከጋሻ ጋር አድርገው በሲሚንቶ የቀበሩበት የድንበር ምልክት ከተደረገበት ከብዙ ኪ/ሜትሮች ገብቶ ኢትዮጵያ በሩዶልፍ ሃይቅ እንዳትጠቀም ደረጉት አፄ ኃይለ ስላሴ በአንድ ወቅት የገለብን ህዝብ ሊጎበኙ ሲሔዱ ፊታውራሪ ነመርሙስ ከስከስ የተባለው ‹‹ ምነው አገራችንን ቆርህ ለእንግሊዝ ሰጠህ አሁን ደግሞ የቱን መሬት ቆርሰህ ልትሰጥ መጣህ ›› ብለው በጃሆይ ላይ የንቀት ንግግር ሲሰነዝሩ እነ ሹሮዎቹም የምኒልክ ግዛት በተፈሪ መኮንን መደፈሩን አልወደዱትም የፊታውራሪ ነመርሙስ ሃሳብን ተጋርተው ነበር የፖለቲካ ሸፍጡን ሳይረዱት ( የምኒልክ ስራ በተፈሪ መንኳስ ነበረበትና ) ድንበሩስ እንዲህ የሚደፈር ከሆነ ያ ሁሉ የምኒልክ አማራ እንደ ላሊበላ ሳሚ ተርመስምሶ የአሞራ ሲሳይ ሆነ ? ነው የምኒልክን ሥራ ተፈሪ አይሻም ? ፡፡ ምኒልክ ከነፍጡ ጋር ምን እንዳቀመሳቸው እንጃ ዛሬም ድረስ ሹሮዎቹ ዘንድ በአብይ የሚማለው ‹‹ምኒልክ ይሙት ነው ›› ፡፡ ቀጥሎ ስለ አሁናዊ የሹሮ/ቲሻና / መኤን ለመግለጽ ፣ለመናገር ለመጻፍ እንዲሁም የብሔሩን ነጋዴዎች ለመንቀፍናለመተቸት የሚያስገርፍ፣የሚያሳስር እንዲሁም አስከ ሞት የሚያደርስ ቢሆንም የብሔረሰቡን የጀግንነት የቆራጥነት ባህልን የሚመጥን ታሪክን ለመፃፍ ግን ዋጋ ቢያስከፍልም በቀጣዩ ብዕሬ እመጣበታለው ጠላቱን ተበቃይ ወዳጁን አክባሪ የሆነው የሹሮ / ቲሻና/ መኤን ሕዝብ ታሪክ እኔ ባልመሰክርም እነ አሰፋ አደፍርስን የመሳሰሉ ልጆች ስሉት ለታሪኩ እግዚአብሔር ፣ ህዝቡ እንዲሁም ሃቀኛ ልጆቹ ለፍርዱ ምስክር ይሆናሉ ፡፡ መስከረም 2015 ዓ/ም

Comments