ቀይ ጤፍ የተጋገረ እንጀራ ዙሪያዉን ሲያሱት በሚልመጠመጥ መሃሉ ነጭ ዳሩ አሳ የመሰለ የማጂ ቆጮ ተፈርሾ የድፍን ምስር ወጥና የጮማ ሥጋ አጥንት ቅባት የነፈጠበት ጎመን ጋር ሲቀርብልን እኔ ከዛሬ ስንት ዓመት በፊት እየቆረሰ ከጎመን ጋር እያነሳው የለመደው ቀን እጄ ከእንጀራው ይልቅ የለመደውን ቆጮ በመመረጥ ቀይ ጤፍ የተጋገረ እንጀራ ዙሪያዉን ሲያሱት በሚልመጠመጥ መሃሉ ነጭ ዳሩ አሳ የመሰለ የማጂ ቆጮ ተፈርሾ የድፍን ምስር ወጥና የጮማ ሥጋ አጥንት ቅባት የነፈጠበት ጎመን ጋር ሲቀርብልን እኔ ከዛሬ ስንት ዓመት በፊት እየቆረሰ ከጎመን ጋር እያነሳው የለመደው ቀን እጄ ከእንጀራው ይልቅ የለመደውን ቆጮ በመመረጥ

እኔ አዲሱ ደምሴ የወ/ሮ ቦኒ በየነ 3ኛ ልጅ ስሆን ከልጆቿ ዉስጥ ብቸኛ ወንድ ልጇ ነኝ ስታየኝ ትሳሳለች ፡፡ ወ/ሮ ቦኒ በየነ አሁን የ60 ዓመት እናት ሲሆኑ እናቷ ወ/ሮ ጋሙዋ ነጋድረስ አሁን ዕድሚያቸው 100 ዓመት የሚሆናቸው ሲሆን ዛሬም የባቹማ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የአዛውንቶች መዘመራን አባል ሆና የምትዘምር በህይወት ያለች ናት ፡፡አባቷ አቶ በየነ ጋዎ የገራማንጆ ባህራዊ አገር በቀል ሐይማኖት ተወካይ ሆነው ሲኖሩ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ፡፡ እኔም የአቶ በየነ ጋዎ እና የወ/ሮ ጋሙዋ ልጅ ልጅ ስሆን የተወለድኩኝ በጎልዲያ ወረዳ ጨበራ ( ቢያጌሌች) ቀበሌ ዉስጥ በመሆኑ የተወለድኩበትን ቀንና ወር እንዲሁም ዓመተ ምህረት የማይታወቅ የባላገር ልጅ በመሆኔ እናቴ ባላት አቅም በዓመት አንድ ጊዜ የምትገዛልኝን ጥብቆ ቆጥራ በሽንት ጨርቅ ያሳለፍኩትን ጊዜ ስትቀንስ ድምሩን ነግራኝ አሁን እንደጠንቋይ የተወለድኩበትን ከመጠንቆል በቀር ከቆጠረችልኝ ላይ ጀምሬ ስቆጥር 40 መስከረሞችን አጥብቻለው ብዬ ጠነቆልኩኝ ፡፡ በዚህ ሁሉ ዘመኔ እናቴ ከእኔ የተሸለ ባለጸጋ በመሆኗ ከእኔ ሰባራ ሳንቲም ይልቅ ኪሴ ሲረጥብ እሷ ወደምትኖርበት ወደ ማጂ/ቱም ሔጄ ስጎበኛት ግን ደስታዋ ጥጉን ያገኛል፡፡ በትዳር የመጠላለፍ ነገር ሆኖ ስለማይሳካ በኣመት ባይሆንም በዓመታት ዉስጥ አንዳንድ ጊዜ ብቅ እያልኝ ጎበኛታለው ፡፡ ታዲያ ከጊዜ በኋላ ወደ እናቴ ቤት የሄድኩኝ በ2014 ዓ/ም ዳግመ ትንሳኤ ላይ ሲሆን አክፋኝ ይዤ ፆሙን ለማስፈታት ሳይሆን ደጇ ደርሼ እጇ ዳስሶን የደረቀውን መንፈሳዊ ሕይወቴን ለማለምለም(ለማጸበል ) በማሰብ ነው ፡፡ ቱም ገብቼ ሳር ሰፈር ወደሚባለው መንደር ሳቀና ዙሪያዉን በእንሰት ፣በአቦካዶ፣በማንጎ፣ በሸንኮራ አገዳ፣ በሙዝና በአናናስ ተከቦ ከጎጆው ጣራ ሳር ቡልልልል….. እያለ በሚወጣ ጢስ ጣሪያዉን የሸፈነው የሳር ክዳንን ሰንጥቆ ወጦ ከሰማዩ ጋር የዳመነውን ጪስ ዓይኔ ሲመለከተው እግሬ 200 ኪ/ሜ ኮሮኮንች መንገድ ተጉዞ ማጂ የገባ ሳይሆን ወደ ገነት እቀረብኩ ያለ ይመስል ፍጥነቱን ሲጨምር ልቤ ደግሞ ገነት ደረሶ ክርስቶስ ላዘጋጅላችሁ እሔዳለው ያለው ቤት ዕጣ ደርሶት የሚገባ ያህል ጮቤ እየረገጠ በደስታ ሲቃ እምቡር እምቡር ይላል ፡፡ የቤቱ በራፍ ላይ ሆኔ ጓዳ ዉስጥ ጉልቻዋን የምታሞቀው እናቴን ‹‹ እምዬ ›› ወይም በለመደረኩት መኤን ቋንቋ ‹‹ ሃዬ ›› ብዬ ስጣራት ከክርኗና ከአንቀልባዋ ጀምሮ ጡት ስሻ የማሰማውን ድምጽ እና የለመደችው ድምፅ ሳይደገም ወይ ልጄ በማለት ከጣሪያው ስር ብቅ በማለት አንገቴን እቅፍ አድርጋ ድምፄም ጠረኔም ያው መሆኑን በአፍንጫዋ ለማረጋገጥ አፏን አፌ ላይ ደቅና እያፈራረቀች ስማንኝ ቀኛ ብላ አይኔን እያየች እኔው መሆኔን ስታረጋግጥ ምሳ መላልሳ ስትስመኝ ማጂ(ቱም) ሆነ እንጂ ሌላ አገር ቢሆን ‹‹ ሹገር ማሚ ›› ጋር የፆታዊ ፍቅር የሆነው ዳቦ በሰለ አልበሰለም ጫዋታ የምንጫወት ያስመስል ነበር እንጂ ከእናቴ ጋር በእናትነት ፍቅር እና ናፍቆት ነው ብሎ የሚጠረጥር አይኖርም ደግሞም እኔም ገዝፌ የንሰሃ አባቷ ቤቷ በራፍ የቆሙና የምትሳለመው ይመስል እንጂ ልጇን እሳመችው አልመስልም ስለሆነም ቢጠረጥሩም አይፈረድባቸውም ፡፡ ማጂ ላይ ግን ደንግል ዉበት ያለበት አገር ነው ፡፡ ማጂ ሕይወት እንደወረደች ናት ፡፡ ሕይወት አትቀባባም ፣አትኳኳልም ፡፡ ሕይወት አታስመስልም ኩርፊያዋና ሳቋ ሀዘኗና ደስታዋ ( ፍቅሯ )ተፈጥሯዊ ነው ፡፡ የምትኳኳል ሕይወት ከማጂ ከ100 ኪ/ሜትሮች በላይ ከፊት ከኋላ ከቀኝና ከግራ ይርቃል ፡፡ እምዬ ቤት እንደገባው በአጎዛ የተፈረሸ መደብ ላይ ተቆርጦ እንዳለቀለት ሾላ ዛፍ ዘፍ ብዬ ወደቁበት እምዬም ከአልጋዋ ላይ በዳንቴል የተሸፈነ ትራስ አምጥታ አናቴን በእጆቿ ቀና አድርጋ አንተራሳኝ ያሰፋችውን እንጀራ ከምጣዱ ለማውጣት ሮጥ ብላ ወደ ጓዳ ስትገባ እኔ እምዬን በ40 ዓመት የምበልጣት አዛውንት የሆንኩን ያህል ተሰምቶኝ ወይ ከተማ መኖርና ከተማ ያፈራዉን መብላት ብዬ ተገረምኩኝ ፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ መምጣቴን የሰሙ ጎረቤቶች አንድ ባንድ እየመጡ እኔን መደቡ ላይ እየተሳለሙኝና ወደ ጓዳ ፊታቸውን አዙረው በዲዜና ቋንቋ‹‹ አዲሱ ኮይ ›› ወይም የአዲሱ እናት እንኳን ደስ አለሽ እያሉ እየተጣሯት ወደ ቤት ገብተው ቁጭ እያሉ እኔን በቋንቋቸው እያጫውቱን ሳለ እምዬ ያሰማቸው ምጣድ ላይ ያሰፋችው እንጀራ አስኪደርስ ከእምዬ ጓሮ የተፈራው ሙዝ ፣ አናናስ ፣ ማንጎና አቡካዶ በቁና/ በጸንዲ / እየቀረበ እየተቆረጠ እየተላጠ እየተበላ አርያእያም ድረስ የሚሰማ ሳቅ ከትንሷ የእምዬ ጎጆ ይስተጋባል ፡፡ ተልጦ የማያልቀው መዝ ና ቡርካን እየተላጠ አናናሱ ና ማንጎው እየተቆረጠ ቤቱን የሚያውደው የአታክልቱ ሽታ ከቤቱ ከሚምነሸነሸው ፍቅር ጋር ሲዋሃድ ኪሩቤኤል የዘጋው ገነት ተከፍቶ ለዕለቱ ገባው መሰለኝ፡፡ ከ ‹‹ ፀንዲው ›› ከበላን በኋላ የባለ አበባው ትሪ ከተሰቀለበት ሚስማር ላይ ወረዶ ከንጹህ ሰርገኛና ቀይ ጤፍ የተጋገረ እንጀራ ዙሪያዉን ሲያሱት በሚልመጠመጥ መሃሉ ነጭ ዳሩ አሳ የመሰለ የማጂ ቆጮ ተፈርሾ የድፍን ምስር ወጥና የጮማ ሥጋ አጥንት ቅባት የነፈጠበት ጎመን ጋር ሲቀርብልን እኔ ከዛሬ ስንት ዓመት በፊት እየቆረሰ ከጎመን ጋር እያነሳው የለመደው ቀን እጄ ከእንጀራው ይልቅ የለመደውን ቆጮ በመመረጥ እንጀራውን ንክች ሳያደርግ ቆጮዉን አንዴ በጎመን አንዴ በምስር ወጥ እያፈፈራረኩ ስጎርስ በእናቴ መሶብ ላይ የቀረቡ እጆችን ብዛት ስመለከት ያቺ ትንሽ ጎጆ አፄ ምኒሊክ ግብር የሚያወጡበት የሹም አዳራሽ መሰለኝ ፡፡ልዩነቱ የአፄ ግብር ፍራፍሬ የሚበላው ከእንጀራ በኋላ ሲሆን በእምዬ መሶብ ላይ ግን ይቀድማል ፡፡ ሆኖም ከፍቅር ጋር የሚበላ ማናቸውም ምግቦች ጤና እንጂ በሽታ እንደማሆኑ የገባኝ እዛች ጎጆ ሥር ሆኜ ነው ፡፡ እምዬ ጋ ቡና በባዶ ሆድ ይጠጣል ከምግብ በኋላም እንደሚጣ አውቃለው እምዬን ለ40 ዓመታት ሳውቃት እንደ መጸሀፍ ገጽ የማቀየር ባህሪዋ ሰው ብልቶ የጠገበ የማመስላት ነገሯ ነው ፡፡ ምግብ ከበላን በኋላ በዛች በማውቃት እሮኮቦት ላይ በተደረደሩ ከእኔ እድሜ በ10 ዓመት በሚያንሱ የፕላስቲክ ሲኒዎች የተቀዳ ቡና አንድ ሲኒ ፉት እንዳደረኩኝ በማጂ ቡና መረቀንኩኝ መሰለኝ ድሮ የማውቀው ነገር ሁሉ አሁን የሆኑ ያህል አዕምሮዬ ወደፊት መልሷው አንድ በአንድ አስታወስኳቸው፡፡ ለፈተና ስዘጋጅ ሰሌን አንጥፌ ደብተሬን አነብ የነበረበት መደብ ፣እናቴ ዉሃ ልትቀዳ ጓራችን ያለው ቱም ወንዝ ስትወርድ የተጣደው ላይ አሳት ቆስቁስ ያለችኝና እሳቱ ሲፈዝ ለማንደድ እፍፍፍ…. ስል አመዱ በዓይኔ ገብቶ የሚያስለቅሰኝና ከምወደው ምንባብ ትንሽ የሚገታኝን ትዝ ይለኛል ፡፡ ላሞቹ ወደ ጋጣ ገብተው ታልበው ጥጃዎች ከታሰሩ በኋላ በቤታችን ለሚደረገው የማታ ፀሎት ፕሮግራም የፕሮግራሙ መሪ ሆኔ ቆሜ የማዘምርበት፣ አልጋው አጠገብ እምዬ ሁሌ ተንበርክካ የምትጸልይበት ቦታን ተንጠራርቼ አየውት እዛው ነው እምዬ ቤት ያለው መሰዊያ አልፈረሰም ፡፡አይኔን ወደ አንድ ጥግ ሳማትር አንድ ባለ አራት ማዕዘኑ ሰማያዊ ጀረካን ለይ አይኔ ሲያርፍ እናቴ እኔን ለማስተማር ያየችው መከራ በህሊናዬ ታወሰኝና ለእናቴ ምን ከፈልኳት ስል ራሴን ሞገትኩኝ ፡፡እናቴ እኔና እህቶቼን ለማስተማር በዲዚየኛ ቋንቋ ‹‹ ያኑ ›› የሚባል የቦርዴ መጠጥ አንዴ በ‹‹ ኩቹ ሙግ›› አንዴ በ‹‹ ያኑ ሙግ ›› እያደረገች እንደ ገበያው መድራት እየጠመቀች በዛው ጀረካን ተሸክማ እኔ ደግሞ የቦርዴ መጠጫ ጣሳ ሸክፌ ወደ ገበያ ስንሔድ ቦርዴው ፈልቶ ጀረካኑን አሳብጦ ክዳኑ እየተፈታ ቦርዴው በለይዋ ላይ ሲፈስና የሆነችውን ሁሉ እዛው ቤት ውስጥ በድኔ ቁጭ ብሎ በምናቤ ማጂ/ቱም ገበያ ሜዳ ላይ የዋለ መሆኑን ያረጋገጥኩኝ እናቴ እዛው የተኛዉበት ላይ በማጂ አውቅ ፈታዮች ተፈትሎ በሸማ ተደውሮ፣ ተሸምኖ ከዛው ከማጂ ወዳጆቿ የመጣላትና ከሳጥን አልፎ አልፎ ካልሆነ የማይወጣዉን እንደ በዘቶ የነጣዉን ጋቢ ስትደርብልኝ ሁሉ አለማስተዋሌ ነው ፡፡ እምዬ የተኛው መስሏት ነበር በኃሳብ መነጎዴን ይበርድኃል ብዬ ነው የሚል ድምፅ እንደሰማው ከገበያ ሜዳ ተመልሼ ሰፈር ዉስጥ የደረስኩኝ መሰለኝ ለእኔ ለእሷ ደክሞን ደክሞን መሰላት ፡፡ ብነቃም ከትዝታ ፈረስ ግን አልወረድኩኝም አሁንም አጋልቦ ከቤታችን በስተግራ በኩል ያለችው ማርያሜ የምትባል ጠንቋይ ቤት ወሰደኝና ጠዋት ጠዋት ከአኩ፣ኪያዝና አቴነሽ ጋር ሆነን እየተዘረገፈልን የምንበላው ‹‹ ጋጁ ›› የተባለ የዲዚ ብሔረሰብ ባህላዊ ምግብ ሽታ ታወድኩኝ ፣ የጨርቅ ኳስ እየሰፋን የምንጫወትበትን ሜዳማ ማጂ ላይ ያለው ዛዝት ፣አኩና እና ኦፊስ ሜዳ ከቱሙ የፓርቲ ሰፈር ሜዳ ጋር በአንድነት በህሊናዬ ኳስ አንከባለሉብኝ ፡፡ የኦፊስ ሰፈር ጢባጢቤ ፣ የቄራ ሰፈር ቶሊማ ፣ ለታህሳስ ገብርኤል ስለት ሳይደርስ አይነካም የተባለው የአበሻ ኮክ ስርቆትና ከጥር በኋላ የሚደርሰው የፈረንጅ ኮክ ሽሚያ እንዲሁም የታህሳሱ ገብርኤል የስለት ኮክ ሽሚያ አይረሱ ትዝታዎች ነበሩኝና በዚሁ እለት ወረፋቸውን እየጠበቁ እኔ የአርባ ዓመት ጎልማሳን ወደ ኋላ መልሰው ህጻን ልጅ አደረጉኝ ፡፡በተለይ ከማጂ ትዝታዬ ዉስጥ ቅዳሜ ቅዳሜ ‹‹ ቼሪ ›› የምትባል ከሁለት ጣሳ በላይ የማትይዝ ቅል ይዘን እንሔድና በቆሎ ወይም ማሽላ የሚያርሙ በደቦ ያረሙና ‹‹ ያኑ ሙግ ›› ወይም ‹‹ ኩቹ ሙግ ›› የተባለ ቦርዴ ቁጭ ብለው የሚጠጡበት ጋ ስንደርስ ቦርዴ ቀጂዋ ጋ ብቻ ቅላችንን እናሳያትና በቦርዴ ሲሞሉልን እሱን እኔና መኮንን ከበደ ተባለ ጓደኛዬ የምንሰክረው ፡፡ አርሶ አደሮቹ እርሻቸውን አርመው ማታ ቤት ሲገቡ ሰብሰብ በለው በማር የተቀላቀለ ቦርዴ እየጠጡ በክራርና በከበሮ የተሟሸ ‹‹ ታሊ ›› የተበለ ባህላዊ ዘፈን ሲዘፍኑና ሲደንሱ እኛም አብረን ‹‹ ታሊን›› ይምጨፈረውና ጉብሎችና ኮረዳዎች ደግሞ አፋቸውን አሹለው አፋቸው በር ላይ በእጃቸው እያጨበጨቡ ‹‹ ታሳክን ታሳክን ታሳክን… ›› አሰልፈኝ አሳልፊኝ እያሉ ሲጨፍሩ ሁለቱ በጨረቃ ለመጥፋት ያሰቡ የፍቅር ዳንሰኞች ትዝታ አሱም በህሊና ደቅን ሲልብኝ እናቴ እቃ ሲወድቅባትም በእየሱስ ስም ማለት ስለምትወድ ዕቃ ወድቆባት በእየሱስ ስም ስትል የእኔ አዕምሮ የሚቀበጣጥለው ትዝታ ጤነኛ አለመሆኑን መንፈስ ቅዱስ ገልጦላት የገሰጸችኝ መሰሎኝ ደንግጬ ከዋኘዉበት የኃሳብ ባህር ቶሎ ብዬ ወጥቼ ቀልቤ ወደ ናፈቀችኝ እናቴ አዞርኩኝ ፡፡በእርግት ለእኔ ከማጂ/ቱም/ በለጠ ትዝታ የለኝም ፡፡ እናቴ የጓዳ ስራዋን ጨርሳ ፊት ለፊት ወጣ ቡና ስትቀዳ የምቀመጥበት በርጩማ ላይ ቁጭ ስትል እኔን ለማጫወት መስሎኝ ፊቴን ከጋቢው እንደ ቀንድ አውጣ ብቅ አድርጌ ገና እንዳንድ ነገር እየተጫወትን ሳለ የዛሬ 30 ዓመት መለትም በ1984 ዓ/ም በቤታችን ተጀምሮ የነበረው የቤት ዉስጥ የጸሎት ፕሮግራም እንደ የዛኔ ጊዜ ተጠናክሮ ቀጥሎ ነበርና ተሳታፊዎቸ የሆኑት የሰፈር ጎረቤቶች ሲመጡ የሚወመጡበትን መደብ ላይ ምንጣፍ ማስተካከልና አንዳንድ አግዳሚ መቀመጫዎችን ማስተካከል ስትጀምር ድሮ የኔ አገልግሎት ነበርና እኔ ስንት ነገር ጥያለው ብዬ በጋቢው እንደተጀቦንኩኝ እዛው መደብ ላይ ቁጢጥ ብዬ ራሴን እየታዘብኩኝ እያለው ሰዎች እየገቡ የሐሊና ጸሎት አይነት እያደረሱ ከተቀመጡበት ተነስተው በተዘጋጀላቸው የመንበርከኪያ ቦታ አየተንበረከኩ ለእየሱስ መስገድ ሲጀም የእኔ ጉልበትና ግንባር መሬት መንካት ያቆመው ከኮሌጅ ወጥቼ በራሴ የኑሮ ትዳር ከተተበተብኩኝ ጀምሮ መሆን አስቤ ዓመታቱን ስቆጥር ከብዶኝ ተውኩት ፡፡ይህንን ሳስብ ግን እንባ ተናነቀኝ ፡፡ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍ ( 2ኛ ጢሞ 2፡4 ሉቃ 21፡ 4 ) ያለው የጌታ ቃል ስለታወሰኝ ፡፡ ትንሽ ተንበርክከው ስለ ቀኑ ዉሏቸው የምስጋና ጸሎት ካደረጉ በኋላ የዕለቱ ፕሮግራም መሪ እንዲነሱ ለምኗቸው መግቢያ ጸሎት ካደረገ በኋላ ቅዱስ ቃሉ ከመደመጡ በፊት መዝሙር አስመርጦ ሊያዘምር ዕድል ሲሰጥ እምዬ ልክ እኔ ድሮ ክፍል ዉስጥ ጄን እንደማነሳው ሁሉ እጇን ቀድማ አነሳችና ዕድል እንዳገኘት እኔ በልጅነቴ ስወጣና ስገባ ከአፌ የማይለየውን ዛሬ በሕይወት የሌለውና ወደ ጌታ የሄደው የዘማሪ ታደሰ እሸቴን ‹‹ መሸሸጊያ ዋሻ መከታ ጋሻችን ፣ጦራችን አንተ ነህ ጠላትን መዉጊያችን ፡፡›› የሚለውን መዝሙር እንደመረጠች መዘመር ሲጀምር ዓይን እንባ ጨርሶ እዥ ማንቆርቆር ጀመረ ጋቢው ረዳኝ ከስር ከስሩ እየላሰ አደረቀው ፡፡ የዛሬ 30 ዓመት የጀመርኩትን አዲስ ሕይወት ግን መርሳት አልቻልኩም የመንግስተ ሰማይን ህይወት ነው ወይስ ለመንግስተ ሰማይ ቦታ ነው የምኳትነው ስል እነሱ ቅልጥ ያለ ዜማ ዉስጥ ሆነው ሲያዜሙ የእኔ አዕምሮ የጥያቄ ምልክት የበዛበት ዐረፍተ ነገር እየመሰረተ አስቸገረኝ ፡፡ በስነ መለኮት መመረቄ ለእነደዚህ ዓይነት ህይወት ካላበቃን ለምኔ ነው ስልም ለተጨማሪ ለቅሶ የሚያበቃ ጥያቄ አነሳው ፡፡ መረሃ ግብሩ አልቆ ሁሉም በተለመደው የቅዱሳን አሳሳም ሰላም እየተባባሉ ሲወጡ እኔ ከረሳዉት የቆየዉትን የሓዋሪያት ሰላምታ እዛው የተጎለትኩበት መደብ ድረስ እየቀረቡ ሰላም ብለው ኮቲያቸው ኮሽ ሳይል ሁሉም ተግተልትለው ወደየቤታቸው ሔዱ ፡፡ የቀረነው እኔና እናቴ እንዲሁም የእኔ ታናሽ እህት ወልዳው ከእምዬ ዘንድ እንዲያድግ የተተው አብይ የሚባል ህፃን ልጅ ብቻ ብንሆንም እኔ ግን ብዙ ጋዜጠኖች የሚጠይቁኝ ይመስል አዕምሮዬ በጥያቄ እያጣድፈኝ ሳለ እምዬ እራት ይቅረብልህ ስትለኝ ቅድም የበላነውሳ ከማለቴ አንዳች የአስቆሮቱ ይሁዳ መንፈስ ሰፍሮብኝ እምዬ ቅድሙ ራሱ ገበያ በወጣና ቢሸጥ ስንት ብር እንደሚያወጣ ታውቂያለሽ ብዬ ከተማ ላይ በሺ ብር አይገኝም ልላት ስል የእምዬ ሃብት አንድ ቦታ ቢጣል እዛው የሚበሰብስ ደደብ ብር(ገንዘብ) እንዳልሆነ ስለገባን ብላትም ባልላትም ጉንጭ አልፋ ከመሆን ዉጭ ፋይዳ የለዉም ብዬ ጥያቄዬን መልሼ ስውጠው ጉሮሮዬን አንቆኝ ትን ትን ሲለኝ እናቴ ምን አስበህ ነው ልጄ ብላ ብትጠይቀኝም ስለአሰብኩት ነገር ሳልነግራት ጉሮሮዬ ደርቆ ምራቀተን ልውጥ ስል ነው ትን ያለኝ ብዬ ቀጠፍኳት በእርግትም ሕወይቴ ደርቆ መንፈሳዊውን ማሰብ አልችል ብሎኝ አንቆኛል ብል ዋሾ አልሆንም ነበር ፡፡ የእናቴን ጥያቄ ልክ እንደሚስቴ ጥያቄ በቁጣና በማጭበርበር አምታትቼ የማላልፈው ስለሆነ ዶሮ ሳይጮኽ ሶስት ጊዜ ከምዋሻት ብዬ እራት በቃኝ ብዬ ጥቅልል ብዬ በዛው ተኛው ፡፡ እምዬ ቤት የተኛዉት እንቅልፍ የእንቅልፍ መርፌ ተወግቼ የተኛው ይመስል ከተበተቡኝ ኃሳቦች ወዲያው ተላቅቄ ጧ ያለ እንቅልፍ ወሰደኝ ፡፡በእርግጥ መንፈሳዊ ክትባት ትከትባለች እናቴ ፡፡ ከለሊቱ 9 ፡00 እናቴ ድሮም ለፀሎት እንደምትነሳ አውቃለው ለ9 ሰዓቱ እንኳን ባይሆንም ለሊቱ 11፡00 ግን ስትነሳ ቀስቅሳኝ አብረን እንፀልይ ነበር ያኔ አሁን ግን እናቴ በአስራ አንድ ሰዓቱ ለፀሎት ስትነሳ እኔን ከመቀስቀስ ይልቅ በአሻግሪ ቁማ እጇን ወደ ተኛዉበት ወደ እኔ ዘርግታ ፀሎት ስታደርግልኝ እና እኔም በጋቢ ተሸፋፍኜና ተጋድሜ ለሚያይ ሰው አለማዊነት ገድሎኝ አስክሬኔ ወደ እናቴ ቤት መጦ ፀሎተ ፍትሐት እየተደረገልኝ ያለ ነው የሚመስለው ፡፡ለእናቴ ያለዉበትነ ሁኔታ መንፈስቅዱስ ገልጦላት መሰለኝ ረጅም ጸሎት ስለእኔ ብቻ ስታደርግ እኔ አሜን እንኳን ለማለት ጉልበት አጥቼ ዝም ብዬ አዳምጣት ነበር ፡፡ ከፀሎቱ በኋላ የተንበረከከችበት መፈረሻ ላይ ጋደም እንዳለች ምንም እንኳን ትዳር መስርቼ ልጆች ያሉኝ ቢሆንም ለሷ ገና ልጅ በመሆኔ በጨዋታ መሓል ልጄ ቤተስኪያን ትገባለህ ወይ ስትል ጠየቀችኝ ማለትም መንፈሳዊ ሕይወትህ እንዴት ነው ለማለት ፡፡ እናቴን መዋሸት ችሎት ፊት እንደመዋሸት ስላለቀለለኝ ‹‹ በእርግጥ ቤተስኪን እሔዳለው መንፈሳዊ ግን አይደለዉም ›› አልኳት እናቴን ብዋሸት ስራዬ ስለሚያሳብቅላት ግልጹን መናገር መረጥኩኝ ቤተክርስቲያ መሔድና መንፈሳዊ መሆን የተለያዩ መሆኑን ደፍሮ ያስተማረኝ መንፈሳዊ አባት የለም እኔ እየሔድኩኝ አስራቴን የምከፍል ከሆነ ባለሁበት ሁኔታ እንቀጥል ቡራኬ የሚቸረኝ የሐይማት አባት ባለበት መሔድና መንንፈሳዊ መሆን የተለያየ መሆኑን የለየልኝ የ11ኛ ክፍል የአማረኛ ቋንቋ መምህራችን የነበረው መ/ር ቃኘው ስንሻው ነው ስለልዩነቱ በምሳሌ ስለ ዉሻ ይነግረን ነበረ እንዲህ ሲል ‹‹ በዩኒቨርቲ ዉስጥ አትለፉ ዩኒቨርስው ግን በእናንተ ዉስጥ እንዲያልፍ ራሳችውን አዘጋጁ በዩኒቨርስቲ ግቢ ዉስጥ ዉሻም ያልፋል ዉሻው ካለፈ በኋላ ያው ዉሻ ነው ›› ስለዚህ ዩኒቨርስቲው በእናንተ ዉስጥ እንዲያልፍ ካላደረጋችው ከዉሻው ልዩነት የላችዉም ስለዚህ ዩኚቨርስቲ በእናንተ ዉስጥ ማለፍ ማለት ማጥናት ነው ›› ሲል የመከረኝ ምክር የመፀሐፍ ቀበኛ እንድሆን አስቻለኝ ፡፡ መ/ር ቃኘው ስንሻው የዶክትሬት ድግሪ ካገኘ በኋላ ከዚህ ዓለም ቢያርፍም ምክሩ በእኔ ሕይወት ዉስጥ ዘወትር ሕያው ሆኖ ይኖራል ፡፡ ከእናቴ ጋር ስለ መንፈሳዊ አዘቅቴ እያዋየዋት አሷም በግሩም መክሯ እየሞላችው ሶስት ቀን አድሬ ወደ ማይሞላው ጎዶሎው ዓለምና ትዳሬ ተመልሼ መጣው ፡፡የቀጣይ ሰው ይበለኝ በ2015 ዓ/ም በቸር ያድርሰን ፡፡

Comments